2013-01-28 17:47:37

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እሁድ እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱ ቃለ ወንጌል በመመርኰዝና ትናንትና ተስታውሶ የዋለው በጀርመን ናዚዎች የተደረገው ዕሊቅት እንዳይደገም አደራ በማለትና ማንኛው የጥላቻና የዘረኝነት በደል እንዲሸነፍ ጥሪ አቅርበዋል፣
እንዲሁም ሌላ በትናንትና ዕለት ተስታውሶ የዋለው ዓለም አቀፍ የለምጽ ደዌ ዕለትንና የቅድስት መሬት የሰላም ቀንን በሚመለክት ለሁሉም ቅርበታቸው ገልጠዋል፣ በመጨረሻም በተለያዩ ቋንቋዎች ለምእመናኑና ለነጋድያኑ ባቀረቡት ሰላምቲ ከኢጣልያ ካቶሊካዊ ተግባር ሁለት ወጣቶች ጋር በመሆን የሰላም ምልክት በመሆን ሰላምን ለሁሉ እንዲያዳርሱ በሚል መንፈስ ሁለት ነጭ እርግቦች ወደ ሰማይ እንዲበሩ ለቀዋል፣
የአይሁዳውያን እልቂት ማስታወሻ ቀንን በሚመለከት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ እንዲህ ዓይነት እልቂት እንዳይደገም ሲሉ ማንኛው ጥላቻና ዘረኝነት እንዲወገድ ጥሪ አቅርበዋል፣
“በተለይ አይሁዳውያንን የጐዳው የዚሁ አሰቃቂ ትራጀዲ ዝክር ያለፈው ሰቆቃው እንዳይደገም ለሁሉም የማይረሳ ትምህርት መስጠት አለበት፤ ማንኛ ጥላቻና ዘረኝነት ይሸነፍ፤ በዚሁ ምትክ የሰው ልጅ ክብረትና መብት ጥበቃ ይንገሥ ብለዋል፣
ይህንን ከማለታቸው በፊት ግን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ኢየሱስ በቃሉ የድኅነት ሙላት በእርሱ ስለመጣ የድኅነት ታሪክ እንደተፈጸመ ያበስራል፣ ስለዚህ ክርስትያኖች እሁድን ያክብሩ ምክንያቱም ይህ ዕለት የዕረፍትና የቤተ ሰብ ቀን በመሆኑ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቅዱስ ቍርባን እየተሳተፉ ለጌታ የሚሰጥ ዕለት ነው፣ ከሁሉም አስቀድሞ እሁድ የጌታ ዕለት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፣
“ባለነው የመዘንጋትና ሃሳብን የሚበትን ዘመን የዛሬው ወንጌል የመስማት ችሎታችንን እንድንመረምር ይጋብዘናል፣ ከእግዚአብሔርና ስለ እግዚአብሔር ከመናግል በፊት እርሱን ጸጥ ብሎ ማድመጥ ያስፈልጋል፣ የቤተ ክርስትያን ሥር ዓተ አምልኮም የዚሁ የሚናገረን ጌታን ለማዳመጥ የምንማርበት ትምህርት ቤት ነው፣
ለክርስትያን እያንዳንዱ ደቂቃ የሕይወት ለውጥ ለማድረግ ምርጥ ቀን ምርጥ ዛሬ መሆን አለበት፣ ድኅነት ሊሰጠኝ የሚጠራኝን እግዚአብሔር የምቀበልበት ዕለት ዛሬ ነው የሚለው ክርስትያናዊ አስተሳሰብ ይህንን ያመለክታል፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ ዓለም አቀፍ የለምጽ ደዌ ዕለትን በማስታወስ እንዲህ ብለዋል፣
“በለምጽ ደዌ ለሚሰቃዩ ሰዎች ቅርበቴን ለመግለጥ እወዳለሁ፣ ለዚህ መድኅኒት ለመፈለግ ለሚጥሩ ሊቃውንትንና የጤና ሠራተኞች እንዲሁም በካቶሊካውያን ተቅዋሞችና በራውል ፎልሮ ጓደኞች ማኅበር አማካኝነት ለበሽተኞቹ በማገልገል የሚገኙ ባለ በጎ ፈቃድ ሆነው በነጻ የሚያገለግሉት ግለሰቦችን ማበረታታት እወዳለሁ ሲሉ ለሁሉም እነኚህን ሕመምተኞች ለማገልገል ሕይወታቸውን ለሰው ቅዱስ ዳምያኖ ዘቨስተርና ቅድስት ማርያና ኮፐ እርዳታ እንዳይለያቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጠዋል፣
በተለያዩ ቋንቋዎች ባቀረቡት ሰላምታና አስተንትኖም የቅድስት መሬት ሰላም እውን እንዲሆን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በዚሁ ቀን ለሚጸልዩና የተለያዩ አስተዋጽ ኦ እያደረጉ ያሉትን አመስግነዋል፣ እንዲሁም ባለፉት ቀናት ወደ ሰማያዊ አባትቻን ስለተጓዙ ነፍሰኄ ብጹዕ ካርዲናል ጆሰፍ ግለምፕ በፖላንድ ቤተ ክርስትያን በሚደረገው ጸሎትም በመንፈስ እንደሚሳተፉ ግለጠዋል፣
በመጨረሻም በጣልያን ካቶሊካዊ ተግባር ስም ለዓለም ሰላም ነጻ እንዲለቅዋቸው የተሰጥዋቸውን ሁለት እርግቦች ላቀረቡላቸው ሲያመሰግኑም፤ “ውድ ልጆች የሰላም ጉዞ አችሁ ቆንጆ ምስክርነት ነው፣ በምትኖሩበት አከባቢ ሰላም ለማንገሥ የምታደርጉት ዕለታዊ ግዳጅ ምልክትም ይሁኑ” ሲሉ አሳስበዋል፣
ከሕጻናቱ አንዷ ደግሞ ቅዱስነታቸውን እንዲህ ስትል አመሰገነች፣ “ውድ ር.ሊ.ጳ እውነት የሰላም አንጋሾች ለመሆን እየታገልን ነው፣ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ሰላም ተባባሪዎች እንድንሆንም ጥረት እያደርግን ነው፣ ውድ ር.ሊ.ጳ የሮማ የጣልያን ካቶሊካዊ ተግባር ሁሌ እርስዎን እንደሚያስታውስ ለማሳሰብ እንወዳለን፣” ካለች በኋላ ቅዱስነታቸው ሁለቱን እርግቦች ከሕጻናቱ ጋር አብረው ነጻ ለቀቅዋቸው፣ ምልክቱም የእግዚአብሔር መንፈስ ሆኖ፡ ፍቅሩን ለሚቀበሉ ሁሉ ሰላም የሚሰጥ መንፈስ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.