2013-01-28 13:38:22

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ በውህደት ጎዳና ጸንቶ መጓዝ


RealAudioMP3 ባለፈው ዓርብ ለክርስቲያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት ማጠቃለያ ምክንያት ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሮማ ፎሪ ለ ሙራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ ዓመታዊ በዓል ሁለተኛ ጸሎት ዘሠርክ መርተው በሰጡት መሪ ቃል፦ “ወቅታዊው ኅብረተሰብ ወንጌልን ዘንግቶ መኖር የተለማመደ እንደሚመስልና ይኽ ኅብረተሰብ መላ ማኅበረ ክርስቲያን መከፋፈልን የሚያሸንፍ የጋራ ምስክርነታዊ አብነት ያሻዋል፣ ትውስትና ግኑኝነትን ወደ በለጠ እንዲያቀና የሚያደረግ የእግዚአብሔር ጸጋ የሚያንጸባርቅ ተጨባጭ ምልከት አስፈላጊ ነውካሉ በኋላ በህንድ ያለው ማኅበረ ክርስቲያንን በማሰብም፦ “ማኅበረ ክርስትያን ችግር በሚታይበት ሁነት የእምነት ምስክርነት ለማቅረብ ተጠርተዋል” እንዳሉ የተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
የክርስቲያን ውህደት ክርስቶስን ለማያውቅ ሁሉ እንዲሁም ወንጌል ተቀብሎ ነገር ግን የተቀበለውን ወንጌል ዘንግቶ ለሚኖረውም ጭምር እምነትን ለማወጅ ተቀዳሚና ምቹ ቅድመ ሁነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሁሉም ለጸሎተ ዘሠርክ የቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ አጽም ባረፈበት ባሲሊካ ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰበሰቡት ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለተወጣጡ ምእመናንና መንፈሳው መሪዎች በማስታወስ ጸሎት ለአቢያተ ክርስቲያን ውህደት ማእከል መሆኑና አለ እምነት ለውህደት የሚደረገው ጉዞ ተራና ልማዳዊ ሰብአዊ ግኑኝነት ሆኖ እንደሚቀር ሲያሳስቡ፦ “ለውህደት የሚደረገው የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ጥረት በእውነትና በፍቅር የሚፈለግና ለውህደት የሚደረገው ጥረት የሰው ልጅ ግላዊ ጥረት ሳይሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። የጋራው ውይይት ለእግዚአብሔር ተግባር ክፍት የሚያደርግ በእርሱ ላይ እማኔ የሚጠይቅ ምሉእ ውህደት በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ያለው መንፈሳዊ ሃብት ለመቀበል የሚያበቃው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መሆኑና ይኸም በእምነት ቀዳሚነት ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት” እንዳሉ ኦንዳርዛ አመለከቱ።
በዚህ ወንጌል ቸል በማለት በሚኖረው ኅብረሰብ ዘንድ የአቢያተ ክርስቲያን ዕርቅ ውይይትና የጋራው መቀራረብ ያለው አስፈላጊነት የሚያመለክት ብሎም አቢያተ ክርስትያን በጋራ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማበሰር የተጠሩ መሆናቸውም ሲያስረዱ፦ “ወደ ምሉእ ውህደት በመጓዝ ላይ ነን። ስለዚህ እምነት ለምንኖርበት ወቅታዊው ዓለም ለማስስተላለፍ ዓላማ በክርስቶስ ሐዋርያት መካከል ተጨባጭ ትብብር ይጠይቃል” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አያይዘውም፦ የሚለያየን አንቀጸ እምነት በምንም ተአምር ችላ ማለት ወይን አሳንሶ መመልከት እንደሌለብን ሆኖም በጽናት የሚለያየው አንቀጸ እምነት በወንድማማችነት መንፈስ ቀርቦ በማጤን የሚለያየንን ጭምር ማወቅ ለመቀራረብ መሠረት መሆኑና ውህደት መለኰታዊ ስጦታ ነው፦ በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ ማለት በእምነት ላይ ጸንቶ መጓዝ በእግዚአብሔር መተማመን መላው ተስፋችንንና የምንጠባበቀው ሁሉ በእርሱ ላይ በማኖር አለ ምንም ጎሳዊ ሃይማናኖታዊ ማኅበራዊ አድልዎ በጠቅላላ የሚለያየውንና መላ ኅበረሰብ የሚጎዳውን በማግለል በጋራ መጓዝን ይጠይቃል” እንዳሉም ገልጠው፣ በዚህ በተካሄደው ሁለተኛው ጸሎተ ሠርክ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ልኡክ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ርክስቲያን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን ልኡካንና ለተሳተፉት ሁሉ ልኡካን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፊት ሰላምታ በማቅረብ ያስተዋወቁት የክርስቲያኖች ውህደት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ መሆናቸው ኦንዳርዛ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.