2013-01-25 14:40:28

የሐዘን መግለጫ መልእክት
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ፣ በቀውጢው ግዜ የሰው ልጅ የሰብአዊ መብትና ክብር ጠበቃ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. መጋቢት ወር ባደረባቸው ከባድ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ምክንያት ቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸው በቫርሳቪያ ሕክምና ቤት ሲረዱ የቆዩት የቫርሳቪያ ልኂቅ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ግለምፕ ከትላትና በስትያ በ 83 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ በቀውጢው የፖላንድ ጊዜ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጠበቃ በመሆን ካለ መታከት ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔርን ያገለገሉ የቤተ ክርስቲያን ልጅ በማለት የገለጡበት የሐዘን መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ የቀብር ሥነ ሥርዓት እፊታችን ሰኞ ከጠዋቱ 11 ሰዓት በቫርሳቪያ ካቴድራል የሚፈጸም መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው ለቫርሳቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ካዚርነርዝ ንይችዝ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት የተሰማቸው መሪርና ልጥቅ ሐዘን በመግለጥ፣ በፖላንድ ቤተ ክርስቲያን በደረሰው ሐዘን ተካፋይ መሆናቸው በማረጋገጥም፦ “እግዚአብሔር በብፁዕ ነፍሰ ኄር ካርዲናል ግለምፕ ሕይወትና ሐዋራያዊ አገልግሎት አማካኝነት ለመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በፖላንድ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ የለገሰው ጸጋ ከፓላንድ ቤት ክርስቲያን ጋር በመሆን የምስጋና ጸሎት አቀርባለሁኝ፣ ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ የተገቡ የወንጌል አገልጋይ” በማለት እንደገለጡዋቸው ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።
“በነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ የሐዋርያዊ ግብረ ኖውሎ አርማቸው ‘Caritati in iustitia-ፍቅር በፍትሕ’ የተሰየመ እንደነበርና ህኽ አርማ በመላ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው የሸኛቸው በፖላንድ ቤተ ክርስቲያን ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ውህደት በመኖር ባስተላለፉት ውሳኔናና ሐዋርያዊ መርህነታቸው የሸኛቸው ቃልና ተግባር ነበር” እንዳሉና፣ “ቃል እግዚአብሔር በቅንነትና በፍትህ በመስካሪ ሕይወት በመኖር ትሁት የእግዚአብሔር ፈቃድ መሣሪያ ይኽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለእግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የነበራቸው ጥልቅ ፍቅርና እንዲሁም ለአስተንፍሶ መሠረት ያደረጉ፣ ኤውሮጳንና ፖላንድን ለማደስ በተደረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ ናቸው” በማለት ቅዱስ አባታችን እንዳስታወሱዋቸው ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አመለከቱ።
“ለእግዚአብሔርና ለቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለሕይወትና ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የነበራቸው ፍቅር መከፋፈልን የሚቃወም የውህደት ሓዋርያ በመሆን፣ ለጋር ብልጽግናና ለብሩህ መጻኢ የቤተ ክርስቲያንና የሕዝባቸው ዕለታዊ ገጠመኝ በመኖር የገለጡ፣ ከር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር የነበራቸው መንፈሳዊ ቅርበት፣ ለእግዚአብሔር አሳቢነት ገዛ እራሳቸውን በእማኔ በመስጠት የፖላንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔር ወደ ሁለተ ሺሕኛው የእዮቤል ዓመት ያሸጋገሩ” በማለት አስታውሰው፣ በመጨረሻ የሕይወታቸው ዘመን የኖሩት ስቃይ በእግዚአብሔር ፍቅር በመኖር ላሳዩት ክርስቲያናዊ ጽናት በስቃይና በችግር ለሚገኙት ሁሉ ከዚህ ዓለም በሞት አስከ ተለዩበት ሰዓትና ቀን አብነት በመሆን ቅን መልካምነት አለ ውስብስብ ቸር ሁሉንም ተቀባይ በመሆን የሰጡት የላቀ ምስክርነት ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ በቤተ ክስቲያንና በሕዝበ እግዚአብሔር ኅሊና ዘወትር ሕያው ናቸው። እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው እጸልያለሁ በማለት ያስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት እንዳጠቃለሉ የቫቲክካ ረዲዮ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 1929 ዓ.ም. ከአንዲት በማእድን ሃብት ቁፋሮ ሙያ ከሚተዳደረው ቤተ ሰብ ተወልደው፣ ገና በሕፃንነታቸው በናዚ ወረራ ወቅት ወደ ሥራ ዓለም ተገደው ከዛም የዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት በ 26 ዓመት ዕድሚያቸው ማዕርገ ክህነት ተቀብለው፣ የብፁዕ ካርዲናል ስተፋን ውንዝይንስኪ ረዳት ሆነው ሲያገልገሉ፣ እ.ኤ.አ. በ 1979 ዓ.ም. በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሰይመው እ.ኤ.አ. በ1981 ማዕርገ ጵጵስና ተቀብለው የግኔዝኖን ቫርሳቪያ ሊቀ ጳጳስ የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ቀዳሜ በመሆ እስከ 2009 ዓ.ም. ይኸንን ስያሜ ያቀቡ፣ እ.ኤ.አ. በፖላንድ አምባ ገነናዊ ሥርዓት በነበረበት ወቅት የፖላንድ ሕዝብ በፍቅር እንጂ አለ ምንም ብቀላ የፍቅር መስካሪ እንዲሆን በመምራት፣ እ.ኤ.አ. በ 1989 ዓ.ም. በፖላንድ ለተረጋገጠው የዴሞክራሲ ሥርዓት አቢይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. በአገረ ፖላንድና በቅድስት መንበር መካከል ለተደረሰው ስምምነትና ቤተ ክርስትያን የአገሪቱ ማኅበራዊ ሕይወት ክፍል መሆንዋ በተካሄደው ጥረት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የቤተ ክርስትያን ልጅ መሆናቸው የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማኅደር ያወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአገረ ፖላንድ የርዝምይስል ሊቀ ጳጳስ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ሚካሊክ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ግለምፕ ጥበብ የተካናቸው በሳል በሁሉም የሚወደዱና የሚደነቁ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሁሉም አባት መላ ሕይወታቸው በቤተ ክርቲያን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ለሰው ልጅ መብትና ክብር የሰዉ ሐዋርያ ናቸው በማለት ከገለጡዋቸው በኋላ ከሳቸው ጋር ሆኖ ማገልገል የቅርብ ተባባሪያቸው ሆኖ ማገልገል በእውነቱ እድል ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ የሚያንጽ ገጠመኝ ነው። ውይይት ወዳጅ መፍትሔ በማፈላለጉ ረገድ የሚደነቁ አገረ ፖላንድ በናዚው ፈላጭ ቆራጭ ከዛም አምባ ገነናዊ ሥርዓት ባመጣው ሁሉ ታሪክ በሕይወት በመካፈል ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት በተደረገው የለውጥ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ ታማኝ የቤተ ክርስቲያን ልጅ በጤንነትና በስቃይ የእግዚአብሔር ፈቃድ የኖሩ ተስፋ የተሞላቸው የፖላንድ ቤተ ክርስቲያን አባት ናቸው በማለት ገልጠዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.