2013-01-24 12:47:09

የቨትናም ኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላይ ኮሚቴ ዋና ጽሐፊ ቫቲካን ጉብኝት፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የቨትናም የኮሚስት ፓርቲ ማእከላይ ኮሚቴ ዋና ጽሐፊ Nguyen phu Ttrong ወን ፉ ቻም በቤት ጽሕፈታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን የዜና ምንጭ አስታውቀዋል። አንድ የቨትናም የኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላይ ኮሚቴ ዋና ጽሐፊ ከርእሰ ሊቃነጳጳሳት ጋር ሲገናኙ ይህ በቤተ ክርስትያን ታሪክ የመጀመርያ ግዜ መሆኑ የቫቲካን የዜና አውታር አስገንዝበዋል።
ይሁን እና በዚሁ የዜና ምንጭ ዘገባ መሠረት ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና የቨትናም ኮሚስት ፓርቲ ማእከላይ ኮሚቴ ዋና ጽሐፊ Nguyen phu Ttrong ወን ዚ ንየን በቅድስት መንበር እና በትቨትናም መንግስት የጋራ ግንኙነት እንዲሁም በመካከላቸው መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት ተወያይተዋል።
እንደ ገርጎርዮስ ዘመን አቁጠጣጠር በ1992 የቨትናም መንግስት የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚስዮን ቫቲካን መጐብኘቱ እና ከዚህ ግዜ ጀምሮ በንዑስ ደረጃም ቢሆን በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል መመካከር ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
በ1999 እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር የቅድስት መንበር የልዑካን ቡድን ወደ ቨትናም ሃኖይ ከተማ በመጓዝ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ መወያየቱ የማይዘነጋ ነው።በመቀጠልም በ200 በጎርጎርዮስ ከአስራ ሶውስት ዓመታት በፊት የቨትናም ኮሚኒስት መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወን ዚ ንየን በቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከነበሩ ከብጹዕ አቡነ ጂን ሉዊስ ቱራን ጋር በመገናኘት በቅድስት መንበር እና የቨትናም መንግስት መካከል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ሰፋ ያላ ውይይት ማካሄዳቸው ያታወሳል።
የቨትናም መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫቲካን ጉብኝት ለግንኝነቱ አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ በግዜው ተዘግቦ ነበር ። ቅድስት መንበር እና የቨትናም መንግስት የዲፕሎማሲ ትስስር ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ መወያየት የተጀመረው ግን እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጠር በ2001 የቫቲካን የልዑካን ቡድን ወደ ቨትናም ሃኖይ ተጉዞ ከሀገሪቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋ ተገናኝቶ በተወያየበት ግዜ እንደሆነ ተገልጠዋል።
ክዚህ ግዜ ጀመሮ ቅድስት ሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በቨትናም ጳጳሳት ለመሰየም መቻልዋም የቫቲካን የዜና ምንጭ አስታውሰዋል።
ግንኘቱ በዚህም አልተቆጨም ወርሀ ሕዳር 27 ቀን 2002 እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጠር የቨትናም መንግስት ረዳት ጠቅላይ ሚንስትር እና በቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ የነበሩ ከብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ እና እንዲሁም በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከነበሩ ከብጹዕ ካርዲናል ጂን ሉዊስ ቱራን ጋር በመገናኘት በቨትናም እና ቅድስት መንበር መካከል ያለውን የወቅቱ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ሰፊ እና ትልቅ ውይይት ማካሄዳቸው የማይዘነጋ ነው ።
በዚሁ ግንኙነት የቨትናም መንግስት ረዳት ጠቅላይ ምኒስትር እና የቅድስት መንበር ከፍተኛ ባለስልጣናት ወቅታዊ የቨትናም የኤኮኖም እና ማሕበራዊ ሁኔታ
በቨትናም መንግስት እና የሀገሪቱ ቤተ ክርስትያን መኖር ያለበት ትብብር ዓለም አቀፍ ፖሊቲካ ትኩረት በሰጡ ጉዳዮች ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው ይታወሳል።
እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጣጠር በ1992 ለመጀመርያ ግዜ ቫቲካን የጐበኘው የቨትናም መንግስት የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚስዮን በ2005 ተመልሶ ቫቲካን መጐብኘት እና ከየቅድስት መንበር የበላይ ባለ ስልጣናት እንደገና መወያየት እጅግ ጠቃሚ መኖሩም ተዘግበዋል።
እንደ የቅድስት መንበር የዜና ምንጭ ዘገባ የቅድስት መንበር እና ለቨትናም ኮሚስት ፓርቲ መቀራረብ ወሳኝ ሚና የተጫወተው ወርሀ ጥር 2007 ኣንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር የቨትናም መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር nguyen Tan dung
ወን ታዱን ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ ጋር በተገናኙበት ግዜ መሆኑ የቫቲካን የዜና ምንጭ አስገንዝበዋል።በዚሁ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና የቨትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ወን ታን ዱን መካከል በተካሄደ ግንኙነት እና ውይይት በቅድስት መንበር እና ቨትናም መንግስት መካከል ያለውን ግኑኙነት የሚሻሻልበት ሁኔታ እና ቨትናም ውስጥ የሃይማኖት ነጻነት ማእከል ያደረገ መኖሩ አይዘነጋም።ቨትናም ውስጥ የሃይማኖት ነጻነት እንዲኖር ቅድስት መንበር የምትገፋበት ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል።
ይሁን እና በ2009 እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጠር የቨትናም ካቶሊካውያን ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድሊሚና ማካሀድ መቻላቸው የቨትናም ካሪታስ ከ30 ዓመታት እገደ በኃላ ስራ መጀመሩ መልካም ምልክቶች መሆናቸው በቅድስት መንበር በኩል የተሰጠ መግለጫ ያመለክታል። ከ350 ዓመታት በፊት ቨናም ውስጥ ሁለት ሀገረ ስብከቶች መመሥረታቸው ተያይዞ ተወሰተዋል።ጽሕፈት ቤታቸው ከቨትናም ውጭ ይሁን እንጂ ብፁዕ አቡነ ለኦፖልዶ ጂረሊ በ2009 በቭትናም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሆነው መሰየማቸውም የሚታወስ ነው። ይሁን እና ትናትና ረፋድ ላይ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ጋ የተገናኙ የቨትናም ኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላይ ኮሚቴ ዋና ጽሐፊ ወን ፉ ቻም ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከየውጭ ጉዳይ ዋና ጠጠሪ ከሊቀ ጳጳስ ከብጹዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋ ተገናኝተው በተመሰሳይ መወያየታቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.