2013-01-23 18:27:24

ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ የር.ሊ.ጳ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ውንድሞችና እኅቶች፧ በዚሁ የእምነት ዓመት ከእናንተ ጋር አብሬ የእምነት ሕይወታችን መሪ በሆነውና እምነታችን በሚገባ ስለ ምናታመንበት ስለ ጸሎተ ሃይማኖት ለማስተንትን እወዳለሁ፣ የጸሎተ ሃይማኖት መክፈቻ ሓረግ “በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ” ይላል፣ ይህ አገላለጥ ገረኛ በሆነ መንገድ መሠረታዊ ይዘት እንኳ ቢኖረው ከእግዚአብሔር እና ከምሥጢሩ ጋር ለሚደረገው ግኑኝነት ለዘለዓለማዊው ዓለም በር ይፈትልናል፣ በእግዚአብሔር ማመን ቃሉን በመቀበልና ለገለጠልን በደስታ በመታዘዝ ለእርሱ መገዛትን ያስከትላል፣ አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ሃይማኖት በቍጥር 166 ላይ “እምነት ራሱን ከሚገልጠው እግዚአብሔር ለሚመጣ አንሳሽነት የሰብ አዊ ፍጡር ነጻ ምላሽ የሆነ ግላዊ ድርጊት ነው” ብሎ እንደሚያስተምረው፤ በእግዚአብሔር አምናለሁ ብሎ መግለጥ ሁለቱን ነገሮች ያካታተ ማለት እምነት እግዚአብሔር ራሱን በመግለጥ ሊገናኘን የሚመጣበት የእርሱ ስጦታ መሆኑና የሰው ልጅ ምላሽ መሆኑን ያመለክታል፣ መለኮታዊ ጸጋና የሰው ልጅ ኃላፊነታዊ ተግባር ነው፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር በሚለው ሰነድ ቍጥር ሁለት ላይ እግዚአብሔር በፍቅር “ከሰው ልጆች ጋር እንደ ጓደኛ ይናገራል” ብሎ እንደሚገልጠው እምነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ውይይት ነው፣ እኛ በእምነት ከእርሱ ጋር ሱታፌ እስኪኖረን ድረስ ይናገረናል፣
የእርሱን ቃል የት ልንሰማው እንችላለን፧ ብለን የጠየቅን እንደሆነ መሠረታዊው ምንጭ ቃለ እግዚአብሔር ሊሰማ የሚችልና ሕይወታችንን በእግዚብሔር ጓደኛነት የሚመግብ ቅዱስ መጽሐፍ ነው፣ ጠቅላላ የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች መገለጥ ነው ሆኖ በአጠቅላይ ስለ እምነት እየተናገረ እምነትን ያስተምረናል፣ እግዚአብሔር የድኅነት ዕቅዱን እንዴት አድርጎ እንደሚያራምደው እና ወደ እኛ የሰው ልጆች እንዴት ቅርብ እንደሚሆን በሚገልጥ አንድ ታሪክ በጌታ ኢየሱስ በሙላት እስኪገለጥ ድረስ በእርሱ በማመንና ሁሉንም በእጁ በመተው ምሳሌ ሊሆኑ በሚችሉ በተለያዩ ማብራርያዎች እየተነተነ ይናገራል፣
ይህንን በሚመለከት በዕብራውያን መል እክት ም ዕራፍ 11 እጅግ በጣም ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፣ በዚሁ ምዕራፍ ስለ እምነት እና በእምነት የኖሩ ታላላቅ የቅዱስ መጽሐፍ ሰዎች ለሁሉም አማኝ ምሳሌ በመሆን ይቀርባሉ፣ በተጠቀሰው ም ዕራፍ ቍጥር አንድ ላይ “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” ይላል፣ ስለዚህ የእምነት ዓይኖች የማይታየውን ነገር ለማየት ይችላሉ፤ የአማኝ ልብም እንደ አባታችን አብርሃም ከማንኛው ተስፋ ባሻገር ተስፋ ሊያደርግ ይችላል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መል እክቱ “ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።” (4፤18) ይላል፣
በዛሬው ትምህርት ስለ አብርሃም ለማስተንተን እወዳለሁ፣ ይህን በማስተዋል እንመልከተው ምክንያቱም አብርሃም ታላቅ የእምነት ምሳሌና አስተማሪ ነው፣ ወደ ሮማ ሰዎች በተጻፈው መልእክት ም ዕራፍ 4፤11-12 በተመለክተው አብርሃም ከአበው አንዱና ታላቅ ሆኖ በእግዚአብሔር የነበረው እምነት ለአማኞች ሁሉ ምሳሌ እንደሆነ ይናገራል፣ በዕብራውያን መል እክት ደግሞ ስለ አብርሃም የሚከተለውን እናነባለን “አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።(11፤8-10)፣
የዕብራውያን መል እክት ደራሲ እዚህ ላይ በብሉይ ኪዳን አንደኛ መጽሓፍ በኦሪት ዘፍጥረት የተጻፈውን ታሪክ በመጥቀስ ስለ አብርሃም ጥሪ ይናገራል፣ ለዚሁ አባት እግዚአብሔር ምን ይጠይቀዋል፧ ብለን የጠየቅን እንደሆነ አገሩን ትቶ እርሱ ወደሚያሰው አገር እንዲሄድ ይጠይቀዋል፣ “ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።” (ዘፍ 12፤1) ይለዋል፣ እንዲህ ዓይነት ጥሪ ለእኛ ቢቀርብልን እንዴት በመለስን ነበር፧ እግዚአብሔር የት እንደሚመራው ሳያውቅ እንዲያው እንደ በጨለማ ዓይንን ጨፍኖ እንደ መጓዝ ነው፣ ሥር ነቀል እምነትና መታዘዝን የሚጠይቅ ነው፣ ይህንን ለመቀበል የሚያስችል እምነት ብቻ ነው፣ ነገር ግን ያ አብርሃም መሄድ የነበረበት እንደ ጨለማ የገለጥነው ያልታወቀው ቦታ በእግዚአብሔር በተሰጠው ተስፋ ይበራል፤ በት እዛዙ ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም አንድ ተስፋ ይሰጠዋል ይህም ተስፋ አብርሃም መጻኢና ሙላት ያለው ኑሮ አንደሚጠብቀው ያረጋግጥለታል፣ “ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ … የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።” (ዘፍ 12.2.3) ይለዋል፣በቅዱስ መጽሓፍ ቡራኬ ከሁሉ በላይ ከሕይወት ስጦታ ጋር የተሳሰረ ነው፣ ይህ ሕይወት ከእግዚአብሄር ይመጣል፤ በዘር መብዛትም ይገለጣል፣ በዚህም ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ይባዛል፣ የአንድ ርስት መሬት መኖርም ከቡራኬ ጋር ይያያዛል፣ ጽኑ የሆነ መሬት ለመኖርና በነጻነትና በደህንነት ለማደግ የሚቻልበት እና እግዚአብሔር እየፈሩና ኪዳኑን በእምነት እየጠበቁ የሚኖሩ የሰው ልጅ ማኅበር እያቋቋሙ “የካህናት መንግሥትና ቅድስት ሃገር” (ዘጸ 19፡6) የሚመሰርቱበት ነው፣ ለዚህም ነው አብርሃም “የብዙ ሕዝብ አባት” (ዘፍ 17፤5 ሮማ 4፤17) እንዲሆን በመለኮታዊው ዕቅድ መሠረት ሊኖርበት ወደ ተሰጠው አዲስ የሚገባው፣ እንዲሁም ሳራ ሚስቱም መኻን በመሆንዋ ልጆች ሊኖርዋት አልቻሉም፤ እግዚአብሔር የሚያሳያቸው ቦታም እጅግ ሩቅ ነው ከአገራቸው የማይገናኝና ሌሎች የሚኖሩበት እንዲሁም አገራቸውን ተመልሰው እንደማያገኙት ተመልክተዋል፣ የቅዱስ መጽሓፉ ተራኪ ሁሉን አንድ በአንድ ጥርት ባለ መንገድ ያቀርብልናል፣ አብርሃም እግዚአብሔር ወዳሳየው መሬት ሲደርስ “በቦታው ከነአናውያን” (ዘፍ 12፤6) ይገኙ እንደነበር ይገልጣል፣ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው መሬት ለእርሱ የሚገባ አልነበረም ስለሆነም አብርሃም እንግዳ ሆኖ ይቀራል፣ ይህንም የሚያመለክተው የርስት አሳብ ልቡን እንዳይከፋፍለውና ድህነቱን ሁሉ እንደ ስጦታ መመልከት እንዳለበት ነው፣ ይህ መንፈሳዊ ሁኔታ የጌታን ጥሪ በመቀበል ምንም በማይይበት ሆኖም ግን በኃይሉ ቡራኬ ተሸኝቶ ጌታን ለመከተል ጉዞውን የሚጀምር ሁሉ ሊኖረው ያለበት ነው፣ የዚህ ዓይነት መንፈሳዊ ሁኔታ የግድ ያስፈልገዋል፣ የአማኞች አባት የሆነው አብርሃም ይህንን ጥሪ በእምነት ይቀበለዋል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮማውያን በጻፈው መል እክት “ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። (4፤18-21) ይላል፣እንግዲህ እምነት፤ አብርሃም ግራ የሚያጋባ ጉዞውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፣ እርሱ ይባረካል የሚታዩ የቡራኬ ምልክቶች ግን የሉም፣ ታላቅ ሕዝብ የመሆን ተስፋ ያገኛል ሆኖም ግን ባለቤቱ ሳራ መሆንዋን ያውቃል፣ በማያውቀው አገር ይወሰዳል ነገር ግን እንደ መጻእተኛ እንደ ስደተኛ ይቀመጣል፣ የኔ ነው የሚለው ትንሽ መሬት የሚያገኘው ሣራን ለመቅበር የተጠቀመበት ቦታ ነው (ዘፍ 23፤1-20)፣ አብርሃም ይባረካል፣ ይህንን ቡራኬ የሚያስገኝለት ደግሞ ምሥጢራዊ በሆኑ ነገሮችም ሳይቀር በእግዚአብሔር በመተባመን ከሚታዩ ነገሮች ወዲያ በእምነት በመሻገር ነው፣
ይህ ክስተት ለእኛ ምን ያስተምረናል፧ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ ብለን ጸሎተ ሃይማኖት በምንደግምበት ጊዜ እንደ አብርሃም “ጌታ ሆይ በአንተ እተማመናለሁ፤ አንተን አምናለሁ” እንላለን ሆኖም ግን እንደ በችግር ጊዜ ብቻ ወይንም በሚመቸን ጊዜ ብቻ ማለት በቀን ወይንም በሳምንት ትንሽ ጊዜ በመወሰን የምናደርገው አይደለም፣ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ ማለት ሕይወቴን በእርሱ እመሠርታለሁ፤ በየዕለቱ በማደርገው የሕይወት ምርጫዎች ቃሉ እንዲመራኝ እፈቅዳለሁ፤ እንዲህ በማድረጌ ደግሞ የሆነ ነገር ወይንም ዕድል አጠፋለሁ ብዬ መፍራት የለብኝም፣ በምሥጢረ ጥምቀት ሥርዓት ውስጥ ሶስቴ በእግዚአብሔር አብ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ፤ በመንፈስ ቅዱስ፤ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና በሌሎች የእምነት እውነቶች ታምናላችሁ የሚል ጥያቄ በጋራ ሲቀርብልን በየግላችን “አምናለሁ” ብለን እንመልሳለን፤ ምክንያቱም የግል ሕይወቴ በእምነት ስጦታ አዲስ ኑሮ ያገኛል ሕይወቴ ይለወጣል ይቀየራልም፣ ሁሌ በምሥጢረ ጥምቀት ሥር ዓት ስንሳተፍ የዚሁ ምሥጢር ታላቅ ስጦታ የሆነውን እምነት በየቀኑ በሚገባ እኖረዋለሁ ወይ ብለን ገዛ ራሳችንን መጠየቅ ያስፈልጋል፧
አማኙ አብርሃም እምነት ያስተምረናል፤ በዓለም ላይ እንደ እንግዳ ሲኖር እውነተኛውን አገር ያሳየናል፣ እምነት በዚህ ዓለም እንደ ነጋድያንና እንግዶች ሆነን ከሌሎች ጋርና በታሪክ እንድንቀላቀል ያደርገናል ሆኖም ግን ጉዞ አችን ወደ ሰማያዊ አገራችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፣ ስለዚህ በእግዚአብሔር ማመን ከዚህ ዓለምና ከጊዜው ጋር የማይስማሙ ዕሴቶች ይዘን እንድንጓዝ ያደርገናል፣ ለዘመኑ አስተሳሰቦች የማይገቡ ሚዛኖችና ጠባይዮች እንድናዘውትር ይጠይቀናል፣ ክርስትያን ሁሉ እምነቱን በሚገባ ለመኖር ካለው አስተሳሰብ ተጻራሪ መንገድ ለመያዝ መፍራት የለበትም የአድርባይነት ተመሳስሎ የመኖር ፈተናን መቃወም አልበት፣ በአብዘኛዎቹ የዘመናችን ኅብረተሰቦች እግዚአብሔር አልባ ኑሮ ገኖ አለው፣ በእግዚአብሔር ምትክ የተለያዩ ጣኦቶች አምልኮ እያገኙ ናቸው በተለይ ደግሞ የሃብት እና የእኔነት ጣኦቶች ሰፊ ቦታ ይዘው ይገኛሉ፣ እዚህ ላይ ሳይንስና ተክኖሎጂ የሚሰጡንን ሥልጣኔ መዘንጋት የለብንም ሆኖም ግን የሰው ልጅ ሁሉ እንደሚችልና ራሱን ችሎ የመጓዝ ቅዥት ውስጥ እንዳይጥሉን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ ይህ የእኔነት ዝንባሌ በሰው ልጆች በሚደረጉ ግላዊ እና ማኅበረ ሰባዊ ግኑኝነቶ ችግር እየፈጠረ ነው፣
ዘማሪው እንደሚለው ለእግዚአብሔር ያለን ጥማት (መዝ 63፤2) በዚሁ የሥልጣኔ ግኝቶች አይረካም፣ የወንጌል መል እክት ሁሌ በብዙ ሴት ልጆችና ወንዶች የእምነት ቃላትና ተግባሮች እያስተጋባ ነው፣ የአማኞች አባት አብርሃም ለመለኮታዊው ጥሪ በመታዘዝና በጌታ መልካም ጥበቃ በመተማመን እንዲሁም ለሁሉም ቡራኬ ለመሆን እርሱ የሚሰጠው ቡራኬን በመቀበል እርሱን ለሚከተሉ ብዙ ሰዎች አባት በመሆን ይቀጥላል፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አለምንም ፍራቻ እየተከተለች ለመራመድ ዓለማችን በተጠራነው እምነት ተባረካለች፣ ይህ ጉዞ አንዳንዴ ፈተናና ሞትን ሳይቀር የሚያስከትል ከባድ ጉዞ ነው ሆኖም ግን የእምነት ዓይኖች ብቻ ሊያይዋችውና በሙሉ ለመጣጣም የሚችልዋቸው ሥር ነቀል የነገሮች ለውጥ በማስከተል ለሕይወት ይከፍትልናል፣
በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ ብሎ እምነታችን መግለጥ እንደ አብርሃም በቀጣይ ከገዛ ራሳችን በመለየት በዕለታዊ ኑሮአችን ከእምነት የምናገኘውን እርግጠኝነትን ለማምጣት ይገፋፋናል፣ ይህ እርግጠኝነት የእግዚአብሔር በታሪካችን የመኖር እርግጠኝነት ነው፣ ዛሬም ሕይወትና ድኅነት በማምጣት ከእርሱ ጋር መጨረሻ የሌለው ሕይወት በሙላት ለመኖር የሚያስችለን የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር መኖር እርገጠኝነትን ከእምነት እናገኛለን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.