2013-01-21 15:13:11

ብፁዕ አቡነ ቶሶ፦ ከሰላም በምድር ዓዋዲ መልእክት 50 ዓመት በኋላ የሰላም ሂደት


RealAudioMP3 ዝክረ 50ኛው ዓመት “Pacem in terris-ሰላም በምድር የተሰየመው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ 23ኛ ዓዋዲ መልእክት ምክንያት በቦሎኛ ሰላም ዛሬ፣ ከ 50 ዓመት ሰላም በምድር ዓዋዲ መልእክት በኋላ” በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት በመሳተፍ አስተምህሮ ያቀረቡት ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ፦ በዚህ ዓዋዲ መልእክት ዘንድ የተለያየው የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ተጠቃሎ እንደሚገኝና በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ሥነ ሰብአዊ እና ቲዮሎጊያዊ አድማሱን በማተኮር ያብራራና ያስገነዘበ ነው እንዳሉ የተካሄደው ዓውደ ጥናት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ተንቶሪ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ብፁዕነታቸው ከአውደ ጥናቱ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የዓለም ታሪካዊ ክንዋኔ የርእዮተ ዓለም መለዋወጥና ፍጻሜም በዓለም መልክዓ ምድራዊ ቅርጽ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚያዊ የዓለም ሥርዓትና ማኅበራዊ ጉዳይ ጭምር እንዲቀየር አርገዋል። የማኅበራዊ ኑሮ መሠረት የሰው ልጅ ሰብአዊነት እንጂ ምንም’ኳ አስፈላጊ ቢሆኑም ቅሉ፣ መንግሥታት ሃይማኖቶች ጎሳዎች ወይንም ርእዮተ ዓለም የሕግ ሥርዓቶች አይደሉም። ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ በአዋዲ መልክእታቸው ሰላም የአንድ የጋራ የሰብአዊ ማኅበርሰብ እግዚአብሔር የማያገል ቅን ሰላማዊ ከእርሱ ጋር ውኅደት እንዲኖር የሚያግዝ የማኅበራዊ ሥርዓት ጥረት ውጤት መሆኑ ያዝገነዝባሉ።
ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ ጦርነት ቅን የሰላም መሣሪያ ሊሆን አይችልም የሚል የማያማታው ያሰፈሩት ሃሳብ፣ የቅን ጦርነት አመክንዮ አለ መኖሩ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር ሆኖም እራስን ከተለያዩ የወረራ ጥቃቶች የመከላከል ቅን ውሳኔ አሚክድ አይደለም። ጦርነት አማራጭ እንዳይሆን ኅብተረሰብ በሰላም ባህል ማነጽ ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት። እኩልነት የሰፈነበት ብልጽግና ለሁሉም የሚባልበት ሥልጣኔ ማረጋገጥ የሰላም መሠረት ነው። እርሃብ እስካለ አድረስ በምድር ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው ብለዋል።
ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሓንስ 23ኛ ማኅበራዊ ጥያቄ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ ነው። የጋራ ጥቅም አንገብጋቢ ዓላማ መሆኑና በዚህ መሠረትም የጊዜ ምልክቶችን በመለየት የሰላም ክዋኔ በእግዚአብሔር ፈቃድ በሰው ልጅ ልብ የተኖረ ዘር መሆኑና በእያንዳንዱ ሰው ልብ ያለና የሁሉም ሰው ዘር ጥልቅ ሓሳብ መሆኑ ያረጋገጠ ዓዋዲ መልእክት ነው ካሉ በኋላ ዓለማዊነት ትሥሥር አወንታዊ ጎን አለው ሆኖም ግን ዓለም አቀፋዊ መዋቅሮች በዚህ ክስተት መሠረት የታደሰ ሆኖ አልቀረበም። ጳጳሳዊ የፍትህና የሰላም ምክር ቤት የማኅበራዊ ጥቅምና የማኅበራዊ ሰላምና ፍትህ አመክንዮ በማመልከት ይኸንን ለመተግበር የሚያግዘው የእያንዳንዱ አገር ተጨባጭ ሁነትና ኃላፊነት የማይጥስ ኵላዊ ስልት በማቅረቡ ረገድ አቢይ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.