2013-01-21 15:06:45

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለግብጽ አዲስ ካቶሊካዊቲ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ የማበረታታቻ መልእክት አስተላለፉ


RealAudioMP3 በግብጽ አለክሳንድሪያ የካቶሊኪ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ እንዲሆኑ የተሰየሙት ብፁዕ ወቅዱስ ኢብራሂም ይስሓቅ ሲድራክ “Ecclesiastica communio-ቤተ ክርስትያናዊ ውኅደት” በተሰየመውሓዋርያዊ መልእክት መሠረት ያቀረቡት የውኅደት ጥያቄ የተቀበሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በበኩላቸው የእኚህ በግብጽ በበኒ ቾከይር የተወለዱት በቆኖናዊ ደንብ በይፋ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በካይሮ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የተመረጡት ፓትሪያርክ ብፁዕ ኢብራሂም ይስሓቅ ሲድራክ ለመላ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እጅግ መልካም ሁነት ማረጋገጫ መሆኑ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፥ “በክፋት ላይ በትንሣዌው ድል በነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና በመላ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ አበው ትብብርና ከብፁዓን የቤተ ክርስትያኒቱ ጳጳሳት ውህደት እርግጠኛ ነኝ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የመምራቱ ኃይል የተሞላችሁ ናችሁ። በጥንታዊው የቤተ ክርስትያን መንፈሳዊነትና ሊጡርጊያ መሠረት የእግዚአብሔር ቃል በሚኖር ሕይወት እንዲታወጅና እንዲከበር የሚያበቃው የእግዚአብሔር ኃይል በመጸለይ እንዲሁም መላ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምእመናን በእርሷ እንዲበራቱና እንዲጸኑ በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ብርታት እንዲሰጣቸው እጸልያለሁ” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኢብራሂም ይስሓቅ ሲድራክ ከፊደስ የዜና አገልግሎት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በግብጽ ያለው የክርስቲያን ምእመናን ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና አሳዛኝ ጭንቀት የተሞላው ላለ መረጋገጥ ለፍርሃት አደጋ በሚያጋልጥ ሁሉም ነገ ወይንም በግብጽ የክርስቲያን ምእመናን መጻኢ ምን ይሆን የሚል ጥያቄ ለማቅረብ ያስገደደ ሆነዋል። ስለዚህ የግብጽ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚው ተግባር የክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ለማስተንተንና ለመኖር በሚያግዝ አስተምህሮና መሪነት ማረጋገጥ መሆኑ አብራርተው፣ በግብጽ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለመምራት የተሾሙት አዲሱ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋዶሮስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምልክት እርሱም ማኅበረ ክርስትያን ለውህደት የሚጠራ ነው ብለዋል።
ግብጽ ለማኅበረ ክርስቲያን የማይሆን አገር ነው ተብሎ የሚነዛው ወሬ ሓሰትና ከእውነት የራቀ መሆኑ አዲሱ ፓትሪያርክ ገልጠው፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ ለማኅበረ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የምስልምና ምእመናንም ጭምር አስጊ ነው። ስለዚህ ፍርሃቱ ቀለም ሃይማኖት የማይለይ ነው ብለዋል። በቅርቡ ተከበረው በዓለ ልደት ዘእግዚእነ ከሙስሊሞች ለማኅበረ ክርስቲያን የቀርበው የመልካም በዓል መግለጫ ምኞት በእውነቱ የሁለቱም ሃይማኖቶች ምእመናን መካከል ያለው መቀራረብ የሚያረጋግጥ ነው። በዚህ ዓይነቱ የመልካም ምኞች መግለጫ ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለሚያውኩ ጠንካራ ምላሽ ተሰጥተዋል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
አዲሱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በበኩላቸውም በግብጽ ባለፉት የመጨረሻ ዓመታት የታየው ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውከው ከፋፋዩ መንፈስ በማኅበረሰቡ ዘንድ ሲጋባ የታየ ቢመስልም ቅሉ፣ የክርስቶስ ተከታዮ ሊኖሩት የተጠሩት መቀራረብና ለሌላው ክፍት የመሆን ጥሪ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው የእግዚአብሔር መንፈስ ባለበት ሁሉ ነጻነተ አለ ነውና በሃይማኖቶች መካከልና እንዲሁም በምእመናን መካከል መቀራረብ እንዲኖር አስፈላጊ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.