2013-01-16 13:49:35

የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ የተመራ የሚያቀርበው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል፣ ትላትና የምእመናን ሁሉ የተገለጠው የእምነት እውነት የመገንዘብና የማስተላለፍ ሚና ላይ በማተኮር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ይኸንን የምእመናን ሚና ሰፋ በማድረግ በሰጠው ትንታኔ ላይ በማተኮር፦ “ቅዱስ መጽሐፍና ቅዱስ ትውፊት የመተንተኑና የመተርጎሙ ሥልጣን የቤተ ክርስትያን ኃላፊነት ማለትም ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ሱታፌ ላላቸው ብፁዓን ጳጳሳት የተሰጠ” መሆኑ በማብራራት፦ “የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ከሕዝበ እግዚአብሔር ውጭ የሚፈጸም አይደለም። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለመገንዘብ የሚያስችል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው” ይኸንን ሃሳብ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቍ. 91፦ “ምእመናን ሁሉ የተገለጠው እውነት በመገንዘብና በማስተላለፍ ይሳተፋሉ፣ የሚያስተምራቸውና ወደ እውነት ሁሉ የሚመራቸው የመንፈስ ቅዱስ ቅብዓትም ተቀብለዋል” የሚለውን በመጥቀስ አረጋግጠው፣ ሁሉ ሕዝበ እግዚአብሔር (ብፁዓን ጳጳሳት እስከ ተራ ምእመን የሚያጠቃልል መሆኑ በማሳሰብም) የእምነት መለኮታዊ ትርጉም ጸጋ የጨበጡ ናቸው፣ ለዚህ ዓይነት የእምነት ትርጉም ምስጋና ይሁንና በእውነት መንፈስ ተነቃቅተው ሕዝበ እግዚአብሔር በሙላት በሕይወት በመተርጎም በጥልቅ ተግባር እምነትን ይከተላል (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 93 ተመልከት)። ይህ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ “Dei Verbum-ቃለ እግዚአብሔር” በተሰኘው ውሳኔው ዘንድ ባለው ንኡስ ርእስ “ቅዱስ ትውፊት በቤተ ክርስቲያን” በተሰየመው ሥር ቍ. 8 እንደሚያስታውሰውም፣ “ቤተ ክርስቲያን በምእመናን የነገሮች መንፈሳዊነት ጥልቅ ገጠመኝ የእምነት ጥበብና እምነትን በማስተንተንና በማጥናት ረገድ ታድጋለች፣ በዚህ ረገድም መንፈስ ቅዱስ ምእመናን ወደ ሙሉ እውነት ይመራቸዋል ይኽ ደግሞ አለ ቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ መርህነት የሚሆን አይደለም።” የምእመናን በእምነት ጥበብ እድገት አርአያ እ.ኤ.አ. በ 1854 ዓ.ም. የማይሻር የእምነት አንቀጽ ተብሎ የታወጀው የማርያም ካለ አዳም ሓጢኣት የመጸነስ እውነት መሆኑ ገልጠው። የተገለጠው ጥልቅ የቅድስት ድንግል ማርያም የግልጸተ ምሥጢር አለ ምእመናን ገጠመኝና አስተንትኖ ማለትም አለ የምእመናን ጥልቅ የእምነት መንፈስ ግንዛቤ ባላገኘ ነበር ብለዋል። እያንዳንዳችን ምእመናን፦ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተገለጠው እምነት የግንዛቤና የማስተላለፍ ተገዥነት አለው የሚለው ኃላፊነት ሊሰማን ይገባል በማለት ያቀረቡትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.