2013-01-16 16:40:53

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር በሚለው ስለ መለኮታዊ ግልጠት የሚናገር ሰነድ ላይ የመላው የእግዚአብሔር መገለጥ በሚያመለክተው ተገልጾ ያለው እውነት “አማላጅና የሁሉ መገለጥ ሙላት በሆነው በክርስቶስ” እኛ ላይ እንደሚያንጸባርቅ አረጋግጠዋል (ቍ.፪)፣ በብሉይ ኪዳን ከፍጥረት በኋላ ምንም እንኳ የሰው ልጅ በትዕቢት ተሸንፎ የእግዚአብሔር ቦታን ለመያዝ ቢሞክርና ኃጢአት ቢወድቅም እግዚአብሔር ግን እንደገና ለጓደኛነቱ መጥራትን አላቋረጠም፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በኪዳኑ አማካኝነት ማለትም ከአባታችን አብርሃም እና በምድራዊ ችሎታ ሳይሆን በፍቅሩ ከመረጠው ታናሹ መንጋ የተባለው ሕዝበ እስራኤል የነጻነት ጉዞ ባካሄደው ኪዳን ነው፣ ይህ የእስራኤላውያን ጥሪና ምርጫ ገና ምሥጢር ሲሆን የሚገልጥልን ነገር ደግሞ እግዚአብሔር በጥበቡ አንዱን ሲመርጥ ሌሎችን ለመወሰን ሳይሆን ወደ እርሱ የሚያደርሱ ድልድይ እንዲሆኑ ነው፣ ምርጫ ሁሌ ለሌላ ነውና፣ በሕዝበ እስራኤል ታሪክ እግዚአብሔር ገዛ ራሱን እንዲያሳውቅ በሰዎች ታሪክ በመግባት በቃሉና በተግባሩ እንደሚገለጥ ለመረዳት እንችላለን፣ ለዚህ ዓይነት ተግባር እግዚአብሔር ሁሌ እንደ ሙሴ ነቢያትና መሳፍንት የመሳሰሉትን አማላጆች በመጠቀም የእርሱን ፈቃድ ለሕዝብ ያደርሳል፣ ሁሌ ደግሞ ለኪዳኑ ታማኝ መሆን እንደሚያስፈልግ እያሳሰበ የመለኮታዊው ተስፋ በሙላት ላንዴና ለመጨረሻ እውን እንደሚሆን እንዲጠባበቁ ያሳስባል፣
በበዓለ ልደት ያስተንተነው ደግሞ የዚሁ ተስፋ እውን መሆን ነበር፣ የእግዚአብሔር መገለጥ ፍጻሜው ላይ ደርሰዋል በሙሉ እውን ሆነዋል፣ ከመጠባበቅ ሁሉ በላይ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ራሱ ሰው በመሆን በናዝሬቱ ኢየሱስ ሕዝቡን ጐበኘ፣ ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር አይደለም የሚነገረን ነገር ግን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር በመሆኑ እና የእግዚአብሔር ገጽታ በማሳየት እርሱ ራሱ የእግዚአብሔር መገለጥ ነው፣ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በወንጌሉ መግቢያ ላይ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው ከቶ ማንም የለም፤ ይሁን እንጂ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ገለጦታል (ዮሐ 1፤18)።
በዚሁ በእግዚአብሔር መገለጥ በሚለው ሓረግ ለማስተንተን ያህል ቅዱስ ዮሐንስ ጥልቅ ትርጉም ያለው ክንዋኔ ይገልጥልናል፣ በወንጌለ ዮሐንስ ም ዕራፍ 14 ላይ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሕማማቱ በቀረበበት ወቅት ሐዋርያትን እንዳይፈሩና እምነት እንዲኖራቸው እርግጠኛ በሆነ መንገድ ጥሪ ያቀርብላቸዋል ከዛም ስለ አባቱ ያነጋግራቸውል፣ ከዛ ወዲያውኑ ፊሊጶስ ሐዋርያ “ጌታ ሆይ! አብን አሳየንና ይበቃናል” ይለዋል፣ ፊሊጶስ ተግባራዊ ተጨባጭ ነገር ስለፈለገ ይህንን እኛም ለመጠየቅ የምንሻው አብን ለማየት እንፈልጋለን የሚለውን ጥያቄ ያቀርባል፣ እዚህ ላይ ለፊሊጶስ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ሳይቀር የተሰጠው የኢየሱስ መልስ በሥነ ክርስቶስ ወይም ክሪስቶሎጂ ትምህርቲ እምብርት የሆነውን ሐረግ እናገኛለን፣ጌታም “እኔን ያየ አብን አይⶆአል” በማለት ይመልሳል፣ በዚሁ መግለጫ የአዲስ ኪዳን ሕዳሴ በአጠቃላይ ይገለጣል፤ ይህ አዲስ ነገር በቤተልሔም ግርግም እውን ስለሆነ እግዚአብሔርን ማየት ይቻላል፤ እግዚአብሔር ፊቱን አሳየን፤ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለማየት የምንችለው ሆነ፣
በመላው ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ፊት ፍለጋ ማለትም ይህንን ፊት ማየትና ማወቅ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ለማየት የነበረን ፍላጎት ያመለክታል፣ በዕብራስጡ ቋንቋ ፊትን ወይም ገጽታን የሚገልጥ ቃል ፓኒም ይላል፣ ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን 400 ጊዜ ተጽፎ እናገኘዋለን፣ ከዚሁ አንድ መቶ የሚሆኑ እግዚአብሔርን ያመልካታሉ፣ አንድ መቶ ጊዜ ስለእግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር ተናግሮ ያንን ያህል ፊቱን የማየት ፍላጎትን ያመለክታል፣ በኦሪት እግዚአብሔር የሚያመልክት ማንኛው ምስል እንዳይሰራ በሕግ የተከለከለበት ምክንያትም ያኔ ሌሎች ያደርጉት እንደነበር እግዚአብሔር በማንኛው ነገር መግለጥ ማመልከት ስለማይቻል ነበር፣ በዚህ ት እዛዝ መሠረት በዕብራውያኑ ሥርዓተ አምልኮ ማየት የሚለው ቃል የለም፣ ማየት የሚል ቃል በሌለበት እና ምንም ዓይነት ምስል ለማቆም በማይቻልበት ሥርዓተ አምልኮ የእግዚአብሔር ፊትን መፈለግ ምን ይሆን፧ ጥያቄው አስፈላጊ ነው፤ ባንዱ በኩል እግዚአብሔርን በምንም ዓይነት ሰው ሰራሽ ነገር ማመልከት አይቻልም፤ እንዲሁም በእርሱ ምትክ ሌላ ነገር ማስቀመጥ አይቻልም፤ በሌላው በኩል ደግሞ እግዚአብሔር ግጽታ እንዳለው ያመለክታል፣ ማለትም አንቱ ለማለት የሚቻልና በሰማይ ላይ ተቀምጦ በገዛ ራሱ ብቻ የተወሰነና ከላይ ሆነ የሰው ልጆችን የሚመለከት ሳይሆን ከእርሱ ጋር ግኑኝነት መፍጠር የሚቻል አካል፤ መሆኑን ያሳያል፣ እርግጥ ነው እግዚአብሔር ከሁሉምበላይ ነው ሆኖም ግን ፊቱን ወደ እኛ ይመልሳል፤ ይሰማናል፤ ያየናል፤ ይናገረናል፤ ኪዳን ይገባል፤ ለማፍቀር የሚችልም ነው፣ የድኅነት ታሪክ ይህ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ዘር የሚያደርገርው የግኑኝነት ታሪክ ነው፣ ይህ ታሪክ እግዚአብሔር ቀስ በቀስ ለሰው ልጆች እየተገለጠ እርሱ ራሱንና ገጽታውን እንዲያውቁት ይገለጣል፣
በዚሁ ዓመት መጀመርያ በርእሰ ዓመት ለሕዝብ የሚቀርበውን ጸሎተ ቡራኬ ሰምተናል፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።” (ዘኁል 6፡24-26) ይላል፣ የመለኮታዊው ፊት ነጸብራቅ የሕይወት ምንጭ ነው፣ ነገሮችን ጥርት ባለ መንገድ ለማየት የሚያስችል ነው፣ የፊቱ ብርሃን የሕይወት መሪ ነው፣ በብሉይ ኪዳን ይህ ቃል ልዩ በሆነ መንገድ ከሌሎች ጋር የሚተሳሰርበት ሁኔታ አለ፣ ይህ ሁኔታ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ነጻ ለማውጣት በተመረጠው እና የኪዳኑ ሕግን በመስጠን ለምድረ ተስፋ እንዲመራ የተመረጠው የሙሴን ጉዳይ ይመለከታል፣ በኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 33 ላይ እግዚብሔር ከሙሴ ጋር ቅርበትና መተማመን የመላበት ግኑኘት እንደነበረው እንዲህ ሲል ይገልጣል “እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር።” (ኍ 11) በዚሁ መተማመንና ቅርበት ምክንያቱም ሙሴ እግዚአብሔርን “እባክህ ክብርህን አሳየኝ አለ። እግዚአብሔርም። እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ አውጃለሁ፤ … ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ። … እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዓለቱም ላይ ትቆማለህ፤ ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዓለት አኖርሃለሁ፥ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤ እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፥ ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።” (ከቍ 18-23) እንዳለው እናነባለን፣ በዚሁ ውይይት ባንድ በኩል በጓደኛሞች መካከል እንደሚደረገው ፊት ለፊት ሆኖ መነጋገርን ሲያመለከት በሌላው በኩል ደግሞ በዚሁ ዓለም እያሉ የእግዚአብሔር ፊት ለማየት እንደማይቻል ይገልጣል፣ ሊቃውንት አበው “ጀርባየን ብቻ ማየት ትችላለህ” የሚለውን ሲተረጉሙ፤ ክርስቶስን ብቻ መከተል እንዳለብህ እና ክርስቶስን በስተጀርባው እየተከተሉ የእግዚአብሔር ምሥጢርን ማየት ይቻላል፣ ጀርባውን እያዩ እግዚአብሔርን መከተል ይቻላል፣
ሆኖም ግን ከምሥጢረ ሥጋዌ ጋር አዲስ ነገር ይከሰታል፣ አንዴ ልታየውና በምንም ምድራዊ ነገር ምስሉን ማስቀመጥ የማይቻለው የእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ሆነ ይህም ሥጋ የለበሰው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ነው፣ በአባታችን አብርሃም ጥሪ የጀመረው የእግዚአብሔር መገለጥ ጉዞ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜ ያገኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ አማላጅና የሁሉ መገለጥ ሙላት ስለሆነ (2ኛ የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር ቍ 2)፣
ሆኖም ግን ከምሥጢረ ሥጋዌ ጋር አዲስ ነገር ይከሰታል፣ አንዴ ልታየውና በምንም ምድራዊ ነገር ምስሉን ማስቀመጥ የማይቻለው የእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ሆነ ይህም ሥጋ የለበሰው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ነው፣ በአባታችን አብርሃም ጥሪ የጀመረው የእግዚአብሔር መገለጥ ጉዞ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜ ያገኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ አማላጅና የሁሉ መገለጥ ሙላት ስለሆነ (2ኛ የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር ቍ 2)፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የግልጠቱ ይዘትና ራሱ ገላጩ ይገናኛሉ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፊትን ያሳየናል የእግዚአብሔር ስምንም ያሳውቀናል፣ የመጨረሻውን ራት ከሐዋርያት በበላበት ጊዜ ባሳረገው ክህነታዊ ጸሎቱ ለእግዚአብሔር አብ እንዲህ ይለዋል፣ “ከዓለም ውስጥ መርጠህ ለሰጠኸኝ ሰዎች የአንተን ማንነት ገለጥሁላቸው .. እነርሱ ስምህን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ” (ዮሐ 17፤6፡26)፣ የእግዚአብሔር ስም የሚለው መግለጫ በሰው ልጆች መካከል ያለው እግዚአብሔር ማለት ነው፣ በሚነደው ዕፀ ጳጦስ እግዚአብሔር ስሙን ለሙሴ ገለጠለት፤ ሊማጠኑት እንደሚቻል አረጋገጠለት በሰው ልጆች መካከል እንደሚኖርም ተጨባጭ ምልክት ሰጣቸው፣ ይህ ሁሉ በኢየሱስ ሙላትና ፍጽምና ያገኛል፣ በታሪክ ውስጥ አዲስ የእግዚአብሔር በሰው መሃከል መኖር ይጀምራል፤ ምክንያቱም ለፊሊጶስ እንዳለው “እርሱን ያየ አባትን ያያልና” (ዮሐ 14፡9)፣ ቅዱስ በርናርዶስ እንድሚለው፤ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቃል ሃይማኖት ነው፤ ሆኖም ግን ይህ ቃል በጽሑፍ ብቻ የሚቀር ደረቅ ነገር ሳይሆን ሥጋ የለበሰው ሕያው ቃል ነው፣ ይላል፣ በትምህርተ አበውና በመሀከለኛው ክፍለ ዘመን ይህንን እውነት ለመግለጥ ልዩ ሓረግ ይጠቀሙ ነበር፤ በሮሜ 9፤28 እና በትንቢተ ኢሳይያስ 10፤23 ተመርኵዘው ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ ማጠቃለያ ቃል አድርገው በመውሰት ቨርቡም አብረቭያቱም አጠር ያለ ቃል በሚል ሓረግ ስለ እግዚአብሔር አብ ሁሉን የነገረን ኢየሱስ ነው፣ በኢየሱስ ጠቅላላው ዓለም እንዳለ ያመለክታሉ፣
በእግዚአብሔር በሰው ልጅ መካከል የሚደረገው የዕርቅ ግኑኝነት በኢየሱስ ሙላት ያገኛል፣ በብሉይ ኪዳን የኢየሱስ አምሳል የሆነ ይህንን ጉዳይ የሚፈጽም አስተናጋጅ ነበር፤ በተለይ ደግሞ ሙሴ የኪዳኑ አማላጅ መሪ እና ወደ ሰው ልጆች የሚያመጣ ነበር፤ በአዲስ ኪዳንም ይህንን እንደ አስታራቂ ተጠቅሶ እናገኘዋለን (ገላ3፤19፣ የሐዋ ሥራ 7፤35 ዮሐ 1፤17)፣ የአዲሱና የዘለዓለሙ ኪዳን አስታራቂ እውነተኛ አምላክና እውነተኝ ሰው የሆነ ኢየሱስ ነው (ዕብ 8፤6፣ 9፤15፣ 12፤24)፣ ቅዱስ ጳውሎስ በ1ጢሞ 2፡5 ላይ “እግዚአብሔር አንድ ነው፤ በመካከል ሆኖ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቀውም አንድ ነው፣ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ይላል፣ በገላ 3፤19 እንደትመለከተው ደግሞ በእርሱ እግዚአብሔር አብን ለማየትና ለማግኘት እንችላለን፣ በእርሱ እግዚአብሔር አብን “አባ! አባታችን” ብለን መጥራት እንችላለን፣ በእርሱ እኛ ሁላችን ድኅነት ተቀብለናል፣
እግዚአብሔር በእውነት የማወቅ ፍላጎት ማለት የእግዚአብሔር ፊትን የማየት ፍላቶ በማያምኑም ሳይቀር በእያንዳንዳችን አለ፣ እኛም ምናልባት ሳይታወቀን እግዚአብሔር ማንና ምን መሆኑን ለማወቅ ከእኛስ ምን ግኑኝነት እንዳለው ለመገንዘብ እንፈልጋለን፣ ሆኖም ግን ይህ ፍላጎት በኢየሱስ ክርስቶስ ነው እውን የሚሆነው፤ የክርስቶስን ጀርባ መመልከት አለብን ማለትም ልንከተለው ያስፈልጋል በዚህም እግዚአብሔርን እንደጓደኛ ለመመልከትና ፊቱንም በክርስቶስ ፊት ማየት እንችላለን፣
እዚህ ላይ አስፈላጊው ነገር ክርስቶስን የምንከተለው ስንጨነቅና ሲቸግረን እንዲሁም በዕለታዊ ኑⶂአችን ጥቂት ጊዜ ባገኘንበት ብቻ አይደለም ነገር ግን እንዳለ በሕይወታችን ልንቀበለው ያስፈልጋል፣ መላው ሕይወታችን እርሱን በማግኘትና እርሱን በማፍቀር እንዲሁም ጓደኛህን እንደገዛ ራስህ ውደድ የሚለውን ትእዛዙን መካከለኛ ቦታ በመስጠት ልንከተለው ያስፈልጋል፣ እንዲህ ያደረግን እንደሆነ በተሰቀለው ብርሃን የክርስቶስን ፊት በድሆች በደካሞችና በሚሰቃዩ ፊት ልናውቀው እንችላለን፣ ይህ እተግባር ላይ የሚውለው የኢየሱስን ፊት ቃሉን በማዳመጥ እና በኅልናችን ቃሉን በማስተንተን በዚሁ ቃል እንርሱን በእውነት እንደምናገኛ በመተማመንና ከሁሉም በላይ ደግሞ በምሥጢረ ቅዱስ ቁርባን የተለማመድነው እንደሆነ ነው፣ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል በኤማሁስ መንገድ ስለተፈጸመው የሁለቱ ሐዋርያት ጉዳይ የተመለከትን እንደሆነ ኢየሱስን እንጀራ በተቆረሰበት ጊዜ ሊያውቁት የቻሉት፣ እዚህ ደረጃ የደረሱት ግን ለረጅም ከእርሱ ጋር በተጓዙበት ጊዜ ያዘጋጃቸው እንደነበረ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከእርሳቸው ጋር እንዲያድር ባቀረቡት ግብዣና በመንገድ ሲጓዙ ልባቸውን ያነድ በነበረ ውይይት በመሆኑ በመጨረሻ ኢየሱስን ማየት ኢየሱስን ማወቅ ችለዋል፣ ዛሬም ለእኛ ቅዱስ ቍርባን የእግዚአብሔር ገጽን ለማየት የምንማርበት ታላቅ ትምህርት ቤት ነው፣ እንዲህ በማድረግም ፊታችን ወደ የመጨረሻው ፍርድ በማዞር ያኔ በፊቱ ብርሃን ሁላችንንም ሊያስደስት መሆኑ መዘንጋት የለብንም፣ በዚሁ ዓለም እያለን ለዚሁ ሙላት ማለት አቅጣችንን ወድ የእግዚአብሔር መንግሥት ፍጽምና አድርገን እንጓዛለን፣









All the contents on this site are copyrighted ©.