2013-01-16 13:45:57

አዲስ ሢመተ ሓዋርያዊ መስተዳድር በታንዛኒያ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በታንዛኒያ የቡኮባ ሰበካ ሐዋርያዊ መስተዳድር ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ነስቶሪዩስ ቲማንያዋ በሕገ ቀኖና ደንብ መሠረት በእድሜ መግፋት ምክንያት ሐዋርያዊ ሓላፊነታቸውን ካስረከቡ በኋላ ቅዱስነታቸው ጥያቄውን በመቀበል እወንታዊ ምላሽ በመስጠት በምትካቸው ብፁዕ አቡነ ደሲደሪዩስ ሮዎማ ከሲንጂዳ ከሰበካ ሲንጂዳ በማዛወር የቡኮባ ሰበካ ጳጳስ እንዲሆኑ መሾማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ርዎማ እ.ኤ.አ. ግንቦት 8 ቀን 1947 ዓ.ም. በቡኮባ ሰበካ በሚጠቃለለው በኢሎጀሮ ቁምስና ተወልደው እ.ኤ.አ. ከ 1962 እስከ 1963 ዓ.ም. የዘርአ ክህንተ ተማሪዎች የማሰናጃ ተቋም በመግባት ቀጥለው እስከ 1967 ዓ.ም. በንኡስ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ሩብያ ከዛም በቡኮባ አቢያ የቡኮባ ሰበካ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት የፍልስፍና ትምህርታቸውን አጠናቀው እ.ኤ.አ. ከ 1970 እስከ 1974 ዓ.ም. በኪፓላፓላ አቢይ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው እ.ኤ.አ. ዓ.ም. ሓምሌ 28 ቀን 1974 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት ተቀብለው፣ እ.ኤ.አ. ከ 1974 ዓ.ም. እስክ 1975 ዓ.ም. በሃሻምብያ ሰበካ ረዳት ጳጳስ ቀጥለውም በሩብያ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት እ.ኤ.አ. ከ 1978 እስከ 1980 ዓ.ም. መምህር እ.ኤ.አ ከ 1980 እስከ 1984 ዓ.ም. የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ሩብያ ምክትል ርእሰ መምህር እንዲሁም ከ 1984 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. በቡኮባ የተረሲያን ደናግል ማኅበር ቤተ ጸሎት ቆሞስ እ.ኤ.አ. ከ 1987 እስከ 1997 ዓ.ም. የሩብያ ንእሱ ዘርአ ክህነት አለቃ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. ለሰበካ ሲንጂዳ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 11 ቀን 1999 ዓ.ም. ሢመተ ጵጵስና መቀበላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.