2013-01-14 15:43:47

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ በጽናትና በትህትና በበላይነት ጫና የሆነውን አስተሳሰብ በትክክል መተቸትና መቃወም


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ሁሌ በሳምት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ከትላትና በስትያ በጽናትና በትህትና በበላይነት ጫና የሆነውን የዓለም አስተሳሰብ በትክክል ለመተቸትና ለመቃወም መትጋት በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዓለምና ወቅቱ የሚሰብከው የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚጻረር መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ እጅግ በበላይነት ጫና የሆኑት አስተሳሰቦች እጅግ በጎላበት ዓለም በትህትና በጽናት የእምነትን አመክንዮ ለመኖር ማኅበረ ክርስትያን እንዲበረታ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበዓለ አስተርእዮ ባሰሙት ስብከት እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ ለአዲሶች ብፁዓን ጳጳሳት ለየት ባለ መልኩ ይኸንኑ በማሳሰብም፣ የእምነት ትህትና ከማመንና ከቤተ ክርስቲያን እምነት ጋር የተሳሰረ መሆኑ ይኽ ደግሞ እየተስፋፋ ያለው የዓለም አመለካከት የሚጻረር መንገድ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እጅግ ተስፋፍቶ ያለው እግዚአብሔርና ዘለዓለማዊ ሕይወት መኖሩ ለማወቅ የሚቻል አይደለም የሚል አስተሳሰብ ጠቅሰው፣ የዚህ ዓይነቱ ማወቅ አይቻልም የሚለው ባህል የሚያስፋፋው አስተሳሰብ ለመቃወም ቤተ ክርስቲያን በእምነት የበረቱ ትሁታንና ብርቱዎች ልጆች ሊኖሩዋት አስፈላጊ ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ያሰመሩበት ሃሳብ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማበከር፣ ማኅበረ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እነዚህ ጫና የሚሆኑትን የወቅቱ አስተሳሰቦች ቀርቦ ለመዋጋትና ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የምክትከተለው ዘርፈ ብዙ መንገዶችን ለይተው መከተል አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን እውነትን እንጂ አስተሳሰብና አመለካከትን የምታቀርብ አለ መሆንዋ ለሁሉም ለማሳወቅ የሚደረገው ጥረት እግዚአብሔር ሁሉን የሚያፈቅር መሆኑ የሚያረጋግጥ ለሁሉም በሙላት ቅርብ ለመሆን የሚሻ መሆኑ የሚመሰክር ነው። ይኸንን አለ ምንም ፍርሃት ለማወጅ እግዚአብሔርን መፍራን ሰዎችን ከመፍራት ነጻ የሚዋጣ መሆኑ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ነው እውነተኛው ነጻነታችን በማለት ያቀረቡትን ርእሰ አንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.