2013-01-14 15:41:39

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከአገረ ቫቲካን የጸጥታ ኃይል አባላት ጋር ተገናኙ
አጅግ አስጀጋሪ በሆነበት ወቅትም የመተማመን መንፈስ ማጎልበት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፈው ቅዳሜ የአገረ ቫቲካን የጸጥታ ኃይል እና የእሳት አደጋ የመከላክያ ኃይል አባላት በቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ በመግለጥ፦ ‘የአገረ ቫቲካን የጸጥታ ኃይል አባላት እያንዳንዱ መንፈሳዊ ነጋዲ እግዚአብሔር በመንገዳችሁ የሚያኖረው ሁሉ ወንድም መሆኑ ለይታችሁ በመመልከት” በምትፈጽሙት አገልግሎት እግዚአብሔር እንዲደግፋቸው ተማጽነው፣ የመከላከያ ኃይልና የእሳት አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላትን በቅዱስነታቸው ፊት ላቀረቡት ለቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ለብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነና እንዲሁም ለአገረ ቫቲካን የጸጥታ ኃይል አባላት የበላይ አዛዥ ዶመኒኮ ጃኒን የምስጋና ሰላምታ እንዳቀረቡ አስታውቀዋል።
የመከላከያ ኃይል አባላት አገልግሎት ፍጹም ታዛዥነት የሚጠይቅ መሆኑ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪም አገረ ቫቲካን ጎብኚዎችና መንፈሳውያን ነጋድያን በወንድማማችነት መንፈስ የማስተናገድ ኃላፊነት ያስከተለ መሆኑ ማብራራታቸው የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘውም፣ በሚሰጡት አገልግሎት ለጸጥታ ኃይሉ ለአዛዦች ጭምር ቅርብ በመሆን ዝጉጅነት በተሞላው መሥዋዕት የመተማመን መንፈስ የታከለበት መሆኑ አብራርተው፣ የጸጥታ ኃይል አባላት በመካከላቸው አስቸጋሪ ሁኔታ በተፈጠረበት ወቅት ጭምር የሚያሳዩት መተማመን መቼም ቢሆን እንዳይጎድል አደራ በማለት ለሚሰጡት ፍጽሙ አገልግሎት ማመስገናቸው አስታውቀዋል።
በዚህ የእምነት ዓመት የአገረ ቫቲካን የጸጥታ ኃይል አባላት፦ “ለየት ባለ መልኩ ለቤተ ክርስትያን ቅርብ በመሆን የሚኖሩት ሕይወት በእውነት እድል ነው። በእምነትና እምነት በመቀበል ያለው ደስታ ምንኛ ኅያው መሆኑና ይኸንን በእያንዳንዱ ሰው ልጅ መሆን ዘንድ በኑባሬ የተሰጠው የመዳን ምኞት፣ ሰላም ወድማማችንነት፣ ፍቅር፣ የድህነቱን ጸጋ በመቀበል በመኖር ያለው ደስታ ለሌሎች ለማበሰር የተጠራችሁ ናችሁ” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገልጠው፣ እግዚአብሔር ቀን በቀን በታሪክ የሚሠራውን እጹብ ድንቅ ነገር ሁሉ እንደ ማርያም በልባችን አቅበን በእለታዊ ሕይወታችን በሚደቀንብን መከራ ሁሉ ጸኑና ቀጣይ የአብ መለኰታዊ አሳቢነት ቅርባችን በመሆን በጥበቡና በፍቅሩ የሚመራን መሆኑ እንድናስተውል አደራ በማለት፣ እግዚአብሔር በአገልግሎታችሁ ይባርካችሁ ካሉ በኋላ ሓዋርያዊ ቡራኬ ለጸጥታ ኃይል አባላትና ለቤተሰቦቻቸው ጭምር እንደሰጡ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.