2013-01-09 15:11:02

የቫቲካን ጉባኤዎችና የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርቶች አይሁዳውያን የቤተ ክርስቲያን ጠላት አለ መሆናቸው ይናገራሉ።


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በቅርቡ የቅዱስ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አስረኛ ማኅበረሰብ ጠቅላይ አለቃ ብፁዕ አቡነ ፈላይ በቅርቡ ስለ ሰጡት መግለጫ ርእስ በማድረግ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው መጠቅይ በብፅዕ አቡነ ፈላይ መግለጫ ላይ ሳይታጠሩ ሆኖም ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድ እንዲሁም ከሌሎች የተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የምታከናውነው የጋራ ውይይት ብሎም በጽናትና በሥልጣናዊ መርህ መሠረትም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን” በተሰኘው ውሳኔውና እንዲሁም ያለፉት ብፁዓን አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛም ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር የጋራው ውይይት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ በማመልከት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቀጥለውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ የሚገኘውን ያካተተው በተለያዩ አገሮች ባካሄዱዋቸው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ኡደቶች ወቅት የጎበኙዋቸው የአይሁድ ምኩራቦች በእምንባ ግንብ ዙሪያ በመገኘት ያሳረጉት ጸሎት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2005 በኮሎን በ 2008 ዓ.ም. በኒው ዮርክ በ 2010 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው የአሁድ ምኩራብ የፈጸሙት ሓዋርያዊ ጉብኝት የቅርብ ትውስት መሆኑ ገልጠው የአይሁድ ሃይማኖትም ሆነ ተከታዮች በጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን ጠላት እንዳልሆኑ የቤተ ክርስቲያን ባህል የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ያረጋግጥልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.