2013-01-09 15:04:37

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ርኅሩኅ ሳምራዊው ለህሙማን ለሚሰጠው እንክብካቤ አብነት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “...እንግዲያውስ ሂድ፣ አንተም እንዲሁ አድርግ…(ሉቃ. 10. 25-37)” የተሰኘው የኢየሱስ ቃል ማእከል ያደረገ ባስተላለፉት ዓለም አቀፍ መልእክት፣ ዕለተ ህሙማን ከብፅዕት ድንግል ማርያም ዘ ሉርድ አመታዊ በዓል ጋር ተያይዞ የሚታሰብ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር በስቃይ ላይ ለሚገኘው ያለው ጥልቅ ቅርበትና ፍቅር ባስተላላፉት መልእክት አበክረው፣ “ስቃይ ስለ ቤተ ክርስቲያን መልካም መሥዋዕት በማድረግና በሚሰቃየው ወንድም ሕይወት ስለ እኛ በጠቅላላ የሰውን ልጅ ለማዳን ሞቶ የተነሳውን የክርስቶስ ቅዱስ ምስል እንድናውቅ” በማሳሰብ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለድኾችና ለህሙማን ያስተላለፈው መልእክት፦ “ለብቻችሁ የተተዋችሁ፣ እርባና አልቦ አይደላችሁም፣ በክርስቶስ የተጠራችሁ የእርሱ ምስል ግልጸት ናችሁ” የሚለውን ቃል በመድገም፣ ሁሉም ወደ ማርያማዊ ቅዱስ ስፍራ ዘሉርድ መንፈሳዊ ንግገድ ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ የሚገኙትን፣ መጋብያን (ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን) ዓለማውያን ምእመናን የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች እንዲሁም ኅሙማን ሁሉ ርኅሩኅ ሳምራዊ አብነቱን አንግበው እንዲጓዙ አሳስበዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሉቃስ ወንጌል ላይ ያለውን የርኅሩኅ ሳምራዊ ምሳሌ የሚያብራራ ባስተላለፉት መልእክት፦ “ኢየሱስ ለእያንዳንዱ ሰው፣ ማንም የማያገለውን የአብ ጥልቅ ፍቅር ያስተማረበት በተለይ ደግሞ በስቃይ በጣረ ሞት ለሚገኙት የሚመለከት መሆኑ በማረጋገጥ፣ አንተም የሳምራዊው አብነት ተከተል፣ ‘እንግዲያውስ ሂድ፣ አንተም እንዲሁ አድርግ…’ በማለት ኢየሱስ የሚከተለው ሁሉ ለታመመው ሊኖረው ሊያሳየው የሚገባው ቃልና ተግባር ይገልጥልናል፣ ኢየሱስ አለ ምንም የድንበር አጥር እራሱን ዝቅ በማድረግ በገዛ ኃጢአቱ ለጠፋው ሰው ሁሉ እጅግ ቅርብ በመሆን ወደ ተስፋና ብርሃን ይመራል፣ ስለዚህ ከዚህ ገደብ የሌለው የአብ ፍቅር በእያናንዷ ቀን ነቅቶ በተጨባጭ አተኩሮ ለመኖር ለሚሰቃየው እርዳታ ለሚጠይቀው ሁሉ ቅርብ ለመሆን የሚያበቃ ኃይል ከጸሎት ይገኛል፣ ይኽ ደግሞ ለካህናት ገዳማውያን ለጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች የሚመለከት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ለህሙማንም ጭምር የሚመለከት ነው። ከእውነተኛው ፈዋሽ በመሸሽ ህመምን ለማስታገስ መራወጥ ሳይሆን ትርጉሙ ለሆነው ከክርስቶስ ጋር ውህደት ማረጋግጥ የላቀው ብስለትና እውነተኛ ፈውስ ነው” ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማኅደረር የተዘገበው ለዚህ ሁሉም አብነት የሆኑትን በማሰብ፣ በዚህ በእምነተ ዓመት የርኅሩኅ ሳምራዊው አብነት ማስፋፋት አንዱ እምነትን ለመኖር አንዱ ተገቢው መንፈሳዊነት ምን መሆኑ ቅዱስት ተረዛ ዘሕፃነት ኢየሱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ ልዊጂ ኖቫረሰ፣ ራውል ፎለሩ፣ እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘካልኩታ፣ ቅድስት ሃና ሻፈር ዘሚንደስተተን ኅሙማን በመርዳት የሰጡት ወንጌላዊ አገልግሎት በተለይ ደግሞ የአብን አንድያ ልጁን በመከተል ሕይወት የላቀ አብነት የሆነቸው ድንግል ማርያም በጎልጎታ ቢሆንም ካለ ምንም ማመንታትና ቀቢጸ ተስፋነት በጌታ ላይ ያላት እማኔ ሳታጎድል ሳትጠራጠር የኖረቸው ጥልቅ አብነት በማብራራት፣ ለሁሉም ኅሙማን በመንከባከብ አገልግሎት የሚሰጡትን ለተለያዩ ማከሚያ ቤቶች መንፈሳዊ መሪዎች ካህናት የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጤና ጠበቃ አገልግሎት መስጫ ማእከሎች ተራ ዜጎች ማኅበረ ክርስቲያን ገዳማውያን መንፈሳውያን ማኅበራት ጭምር፦ “ርኅሩኅ አፍቃሪ ደግ በተለይ ደግሞ እጅግ ለሚሰቃዩትና ለህሙማን ቅርብ መሆን የሚለውን የቤት ርክስቲያን ተልእኮ በጥልቀት እንዲኖሩ” ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.