2013-01-09 15:08:02

ሰው ከኤኮኖሚ መዋቅርና ሥርዓት እጅግ የላቀ ነው


በገንዘብና በገበያ መካከል ያለው ግኑኝነት የሚያዛባው እርሱም የተስተካከለ ተነጻጻሪነታቸውን የሚያዛበው የኤኮኖሚ ስልት የኅብረተሰብ የተስተካከለ ምቹ ኖር ላይ ግሽበት እያስከተለ ላለው ለኤክኖሚ መዋቅርና ሥርዓት እጅ መስጠት ሳይሆን፣ ወቅታዊው የኤክኖሚው ቀውስ በገንዘብ ሃብት ላይ ያተኮረው፣ ኤኮኖሚ ቅጥ የለሽ መንገድ መከተል ያመጣው መዘዝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታትን ለአዲስ ዓመት ምክንያት ተቀብለው ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ የሰው ልጅ ከኤኮኖሚ መዋቅርና ሥርዓት እጅግ የላቀ RealAudioMP3 መሆኑ እንዳይዘነጋ ማሳሰባቸው ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ “Caritas in Veritate-ፍቅር በሐቅ” የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረሱት አዋዲ መልእክት ላይ ያተኮረው የምርምር ማእከል አስተዳዳሪ የኤኮኖሚ ሊቅ ፕሮፈሰር ፍላቪዮ ፈሊቸ ባቀረቡላቸው ቃለ መጠይቅ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የደረሱት ፍቅር በሐቅ የተሰየመው አዋዲ መልእክት የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ቀውስ መነሻ የገንዘብ ሃብት ላይ ያነጣጠረው የኤኮኖሚ ስልት መሆኑ ለይተው ያስቀመጡት ትንታኔ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኤኮኖሚ ሊቃውንትና ማእከሎች መናብርተ ጥበብ ዘንድ የተረጋገጠ እና አቢይ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ ገልጠው፣ የገንዘብ ሃብት ኤኮኖሚ አስፈላጊ ነው ሆኖም ግን በአንድ የኤኮኖሚ ሥርዓት ሥር መቀመጥ ይኖርበታል፣ ስለዚህ መገልገያ መሣሪያ እንጂ ፍጻሜ ወይንም ግብ መሆን የለበትም ብለዋል።
የገንዘብ ይዞታ ኤኮኖሚ የኤኮኖሚ ምርት እድገት ደጋፊ አንቀሳቃሽ መሆን አለበት፣ የምርት እድገት ብቻ ነው አዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚችለው። በገዛ እራሱ ላይ የታጠረ የገንዘብ ይዞታ ኤኮኖሚ ለብቻው ለሥራ ዕድል ዋስትና ሊሆን አይችልም። የኤኮኖሚ ዋነኛው ዓላማ የሥራ እድል መፍጠር የሚል መሆን አለበት፣ ከዚህ ውጭ የሆነ ኤኮኖሚ እድገት ሊሆን አይችልም። በዚህ ተከስቶ ባለው በገንዘብና በገበያ መካከል ያለው ግኑኝነት መዛባት ካለ መሸነፍ ወይንም እጅ ካለ መስጠት የገንዘብ ይዞታ ኤኮኖሚ ማስተካከልና በድኻውና በሃብታሙ መካከል ያለው የግኑኝነት ግሽበት የኑሮ ደረጃ መዛባት የሚያስተካከል አዲስ ኤኮኖሚ እሳቤ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ፍቅር በሐቅ በተሰኘው አዋዲው መልእክታቸው የገለጡት ጥልቅ ሃሳብ ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመላቀል ቀዳሚው መንገድ ምን መሆኑ ያመለክታሉ። ይህ ያመለከቱት መንገድ በሕንጸት ዘርፍ መስተጋባትና መተንተን ያስፈልገዋል፣ በቅድሚያ ፍትህ ላይ ያተኮረ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር በማረጋገጥ ሰው ከኤኮኖሚ በላይ የላቀ መሆኑ በመታመን፣ እንዲህ ባለ መንገድ ዓለም የሚከተለው የኤኮኖሚ ሥርዓት ማረም የሚል አዲስ አስተሳሰብ አስፈላጊ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.