2013-01-04 14:28:44

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 46ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት
እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም.
ሰላም፦ የእግዚአብሔር ስጦታና የሰው ልጅ ጥረት (ተግባር)


RealAudioMP3 3. ሰላም የሰውን ልጅ ምሉእነት የሚመለከት መላውን የሰው ዘር የሚያካትት ነው። እንደ የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኖር ሰላም ከእርሱ ጋር። ውስጣዊ ሰላም ከእራስ ጋርና ውጫዊ ሰላም ከጎረቤት ወይንም ከባለንጀራ ጋር እንዲሁም ከሁሉም ፍጥረት ጋር። ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ “Pacem in terris-ሰላም በምድር” በተሰየመው በቅርቡ 50ኛው ዓመት ሊዘከርለት የተቃረበው ዓዋዲ መልእኽታቸው ዘንድ ፦ ሰላም በመሠረቱ በእውነት በነጻነት በፍቅርና በፍትህ ላይ የተገነባ ማኅበራዊ ኑሮ (የጋራ ኑሮ) ሁነት የሚጠይቅ መሆኑ ተመልክቶ ይገኛል። እውነተኛው ሰብአዊ መሆን እርሱም እጅግ አስፈላጊ የሆነውን አድማስ በውስጡ ከሚያጠቃልለው እውነትን መልካም በመጨረሻ ትንታኔውም ለገዛ እራሱ እግዚአብሔርን የማወቅ ብቃት የሚያጸናው ባህርይ እጅግ አስፈላጊ የሆነው አፍድማሱን መካድ የሰላም ግንባታ ለከፋ አደጋ ያጋልጣል። በፈጣሪ በሰው ልብ ውስጥ የተቀረጸው ስለ የሰው ልጅ እውነታ ማግለል ነጻነትና ፍቅርን ያመክናል ፍትህ መሠረታዊ ትግባሬውንም ያጣል።
እውነተኞች የሰላም መገልገያ መሣሪያ ለመሆን ለዳር ማዶነት አድማስ መሃሪ አባት ከሆነው በአንድያ ልጁ የተጨበጠው ድህነት አማካኝነት ከሚጸለየው እግዚአብሔር ጋር ቀዋሚ ግኑኝነት ወይም ውይይት ትኩረት መስጠት እጅግ ወሳኝ ነው። በዚህ አኳያ የሰው ልጅ ሰላምን የሚያጨልምና የሚክድ በጠቅላላ የኃጢአት የተለያየ መልኩ እርሱም ራስ ወዳድነት አመጽ ስግብግብነት የሥልጣን ሌላው የመጨቆን ሌላው ያለ መቀበል የጥላቻ የኢፍትሃዊነት ቅርጽ ፍላጎት ሁሉ ለማሸነፍ ይችላል።
የሰላም መረጋገጥ በእግዚአብሔር ልዩ አንድ ቤተሰብ መሆናችን ከሚሰጠው እውቅና ጋር የተቆራኘ ነው። “Pacem in terris-ሰላም በምድር” የተሰየመው ዓዋዲ መልእክት እንደሚያስተምረን ሰላም የእርስ በእርስ ውስጠ ሰብአዊ ግኑኝነት ‘እኛ’ በሚል የማኅበራዊ መንፈስ የሚመራው ውስጣዊና ውጫዊ ሁሉም በቅንነት በእውነትና በፍትህ የሁሉም ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲሁም ግዴታ የሚያመለክት ግብረ ገባዊ ሥርዓት መሠረት የሚጸናው የሚነቃቃው ተቋም አማካኝነት ቅርጽ ይይዛል። ሰላም ኅያው ሥርዓትና ፍቅርን የሚያካትት የሌሎች ፍላጎትና መሠረታዊ ጥያቄ የገዛ እራስ እንደሆነ አድርጎ ማሰብ፣ ሌሎችን በገዛ እራስ ግላዊ ሃብት በማሳተፍ መንፈሳዊ እሴቶች በዓለም ዘወትር እጅግ እንዲስፋፋ ያደርጋል። በነጻነት በዓለም ማለትም ከሰብአዊ ክብር እርሱም በግል ለሚፈጸመው ተግባር ኃላፊነት መውሰድ ከሚለው የማስተዋል ባርህይ ጋር የሚስማማ ነው።
ሰላም ህልም፣ ጦቢያ ሳይሆን የሚቻል ነው። የዓይኖቻችንና የአእምሮአችን እይታ ከሚታየው ውጫዊነትና ክስተት በላይ ልቆ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር በእርሱ አርአያና አምሳያ የተፈጠረ፣ ለማደግ የተፈጠረ በአዲስ ዓለም ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የተጠራ መሆኑ የሚገልጡ በልብ ውስጥ ያሉትን አወንታዊ ተጨባጭ በጥልቀት የሚያተኩር መሆን አለበት። እግዚአብሔር በልጁ ትስብእትና በእርሱ የተፈጸመው ድህነት አማካኝነት አዲስ ፍጥረትና በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል አዲስ ቃል ኪዳን (ኤርም. 31, 31-34 ተመልክት) እንዲመነጭ በማድረግ በታሪክ በመግባት አዲስ ነገር ሁሉ እንዲኖረን በማድረግ ‘አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ’ (እዝቀ. 36, 26) ይሰጠናል።
ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያን የሕዝቦች ምሉእ እድገትና የሰላም ጭምር ምክንያት እርሱም መጀመሪያና ፍጻሜ የሆነው ኢየሱስ ክርቶስን በአዲስ የማወጅ አንገብጋቢነቱ የታመነችበት። በርግጥ ኢየሱስ ሰላማችን የእኛ ፍትህና መታረቃችንም ነው (ኤፍ. 2, 14፣ 2ቆር. 5, 18 ተመልከት)። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ባርኮት የሰላም ሠራተኞች የሌሎች እርሱም ምሉእ አካላዊና መንፍሳዊ መልካምነት ዛሬም ነገም የሚሹ ማለት ነው።
ከዚህ አስተምህሮ እያንዳንዱ ሰው፣ ማኅበረሰብ ገዳማዊም ተራም ሕንጸተም ባህልም ለሰላም እንዲጠመድ መጠራቱ እንገነዘባለን። በመሠረቱ ሰላም የተለያየ ማኅበረሰብ ቀዳሚውና ሌላው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ አስፈላጊ የሆነውን ለጋራ ጥቅም መረጋገጥ ማለት ነው። ስለዚህም የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መንገዶች ሰላም ለማረጋገጥ የሚንከተለው መንገድ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.