2013-01-02 15:32:06

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 46ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት
እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም.


RealAudioMP3 ወንጌላዊ ብፅዕና (ባርኮት)
2 በኢየሱስ የታወጀው (ባርኮት) ብፅዕና (ማቴ. 5፣ 3-12 እና ሉቃ. 6፣ 20-23 ተመልከት) ብፅዓት ቃል ኪዳን ናቸው። ባርኮት ወይንም ብፅዕና በርግጥ በቅዱስ መጽሐፍ ባህል በሥን ጽሑፋዊ አገላለጥ በውስጡ አዲስ ዜና ወይም ወንጌል ያስከተለ በቃል ኪዳን የሚጠቃለል ነው። ስለዚህ ባርኮት ወይም ብፅዕና ለሚመጣው ሕይወት ካሳ ላይ ያተኮረ መጻኢ ደስታ የሚመለከት በተወሰነ ጊዜ ዕዳህን ለማካካስ ከወዲሁ የሚከበር ወይንም የሚፈጸም የግብረ ገባዊ መላከት (አደራ-ትእዛዝ) አይደለም። የባርኮት ወይንም የብፅዕና ለሁሉም ፈጣን ድርጊት በሚጠይቅ እውነት ፍትህና ፍቅር ለመመራት ገዛ እራሳቸውን ለሚፈቅዱ የሚመለከት ቃል ኪዳን (ብፅዓት) ላይ የጸና ነው። በዚያ በዓለም ፊት የዋሆች ወይንም ሞኞች አሊያም ከተጨባጩ ሁነት ጋር የማይገናኙ ሆነው ለሚታዩት እማኔያቸው በእግዚአብሔርና በቃል ኪዳኑ ላይ ለሚያኖሩት በርግጥ ኢየሱስ ባርኮት ወይንም ብፅዓት በሚመጣው ሕይወት ሳይሆን በአሁኑ ተጨባጩ ሁነት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚረጋግጥበት ከመጀመሪያ ለሁሉ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ለሚታመንባቸው የሚመለከት ነው። ስለዚህ ለብቻቸው እንዳልሆኑ ምክንያቱ እግዚአብሔር ስለ እውነት ፍትሕና ፍቅር ለሚጠመዱት ከጎናቸው መሆኑ እንረዳለን። ኢየሱስ ገዛ እራሱንም መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ለማያመነታበት የአብ ፍቅር ግልጸት ነው። ማንም ኢየሱስ-ክርስቶስ፣ ሰው-እግዚአብሔር የሚያስተናግድ ወይንም የሚቀበል በትክክል የእግዚአብሔር ሕይወት እርሱም የጸጋ የምሉእ ባርኮት ህላዌ ዋስትና የሆነውን በመቋደስ የደስታ ጸጋ ገጠመኝ ይኖራል። ኢየሱስ ክርስቶስ ለየት ባለ መልኩ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ከሚፈጽመው ታማኝ ግኑኝነት የሚወለድ እውነተኛ ሰላም ይሰጠናል።
የኢየሱስ ባርኮት ሰላም መሲሐዊ ስጦታና ከጊዜ በኋላ የሰው ልጅ ተግባር መሆኑ ይገልጥልናል። ስለዚህ ሰላም ለዳር ማዶነት (ነገር ሰገር) ክፍት የሆነ ሰብአዊነት እንደ ቅድመ ሁነት ይጠይቃል። የእርስ በእርስ የጋራ ስጦታ የእርስ በእርስ የጋራ ብልጽግና ውጤት ነው። ከእግዚአብሔር ለሚመነጭ ጸጋ ምስጋና ይሁንና ከሌሎች ጋርና ለሌሎች ለመኖር እንዲቻል የሚያበቃ ነው። የሰላም ሥነ ምግባር የሱታፌና የመቋደስ ሥነ ምግባር ነው። ስለዚህ የተለያዩ ወቅታዊ ባህሎች የገበያው ግላዊ (ባለ ቤታዊነት)ና ግብረአዊ ውጤት እርሱም የአብሮ የመኖር የጋራው ግኑኝነት በኃይለ-ሥልጣንና ትርፍ የሚል የመገልግገያ መሣሪያ ግብ እንዲሁም ግቡ የመገልገያ መሣሪያ የሚያደርግ ባህልና ሕንጸት በመገልገያ መሣሪያ በግብረአዊነትና በሚሰጠው ፍጡንነት (ውጤታማነት) ከሚለው ግብረአዊ-ኅልዮ ባነቃቃው ላይ ከሚጸናው ስነ ሰብእ በላይ ሆነው እንዲገኙ ግዴታ ነው።
ሰላም በሰው ልጅ ኅሊና በእግዚአብሔር የተጻፈው ከማይጣሰው በኑባሬ ካለው ባህርያዊ ግብረ ገብ ውጭና ይኸንን ባህርያዊ ግብረ ገብ እውቅና የማይሰጥና የሚያገል ገለልተኛ ራስ ገዝ የሆነው አምባገነናዊ የተዛማጅ ባህል ፈጽሞ ማስወገድ የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች ያስቀምጣል። ሰላም በግብረ ገብና በስነ አመክንዮአዊ ረገድ በሰው ልጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር በተፈጠረ መመዘኛ ላይ የሚመሠረት ማኅበራዊ ሕይወት ግንባታ ማለት ነው። “እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል በሰላም ይባርካቸዋል” (መዝ. 29፣ 11)።








All the contents on this site are copyrighted ©.