2013-01-02 16:09:18

ሰላም በእግዚአብሔር ዘንድ ይገኛል ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ትናትና አዲስ ዓመት ጥር አንድ ቀን 20013 የቅድስት ደንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ክብረ በዓል 46ኛ ዓለም አቀፍ የሰላም ዕለት ምክንያት በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል በበርካታ ካርዲናሎች ጳጳሳት እና ካህናት ተሸኝተው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።
በነዲክት 16ኛ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜና ባሰሙት ስብከት በዚች መረጋጋት እና ሁነኛ ሰላም በምይታይባት ዓለመችን እግዚአብሔር ሰላም ስለሆነ
ሰላም የሚገኘው በእግዚአብሔር መሆኑ ጠቅሰው ማሕበራዊ ኢ ፍትሐውነት ተግባረ ሽበራ የወንጀል ተግባር ሰላም ከሚነሱ ጉዳዮች መሆናቸው አመልክተዋል።በማያያዝም ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ ሰላም ለማነጽ እና ማበልጸግ እንደሚቻል ጠቁመው ሰላም ከሌለ ሁሉም ከንቱ ውእቱ መሆኑ አስታውቀዋል።
በዚች ዓለም ላይ ሃብት ባካበቱ እና ድሃ ማሕበረ ሰቦች መካከል ያለውን ልዩነት ቅጥ ያጣ መሆኑ ስስትእና አሳሪ የሌለው መዋእለ ንዋይ ሰላም እንዳይከሰት እንቅፋት መሆናቸው በነዲክት 16ኛ አመልክተው ማሕበራዊ ፍትሕ እንዲከስተ በአጽንኦት ጠይቀዋል።
ዓለም አቀፍ 46ኛ የሰላም ዕለት አስታውሰውም የሰው ዘር ከራሱ እና ከውጭው ዓለም በሰላም እንዲኖር የተፈጠረ መሆኑ ቢሆንም ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነ እየተዘነጋ መምጣቱ አስገንዝበዋል።ቅድስት ደንግልማርያም ወላዲተ አምላክ የሰላም ምንጭ እና ባለቤት መሆንዋ እና ሰላም ይሰፍን ደንዳ ርሕርሕት ቅድስት ድንግል ማርያምን እንለምን ብለዋል።
ከቅድስት ድንግል ማርያም እና ልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ ሰላም እና እርጋታ እና እርካታ ይገኛል የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተከትሎ ዛሬ አሀዱ ብለን የምንጀምረው አዲስ ዓመት 20013 እንደ ጎርግርዮስ ዘመን አቁጣጠር ዓመተ ሕይወት እና ብልጽግና ይሁን ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በክርስቶስ ልደት አመካይነት ጨለማ የነበረው ብርሃን ሁነዋል ብለዋል።
እግዚአብሔር የዓለም ህዝቦች ይባርካቸው ይጠበቃቸው በዚች ዓለም ላይ ሰላም ይሁን ፍትህ እና ዕርቅ እንዲከሰት እግዚአብሔርን እንለምን ብለዋል በነዲክት አስራ ስድተኛ ትናትና ጥዋት በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል በሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እና ስብከት።
ከቅዳሴ በኃላም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነክት በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኘ ህዝበ ክርስትያን በጋራ እሁዳዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት የደገሙ ሲሆን ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቃል እና ፍላጎት ስጋ ሆነ ለመላ ዓለም ሰላም እና ብርሃን ይዞ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ብለዋል። በዚሁ የአዲስ ዓመት መጀመርያ ቀን መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በመላ ዓለም ሰላም ይሰፍን ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምልክን እንለምን በማለት ማርያናዊ ጸሎት መርተው ደግመዋል ። በቅዱስ ጵጥሮስ አደባባይ ለተገኘ ህዝብ በተለያዩ ቋንቋዎች መልካም አዲስ ዓመት ተመኝተው እና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.