2012-12-28 15:22:54

የእስያ ብፁዓን ጳጳሳት፦ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል አለ ምንም ፍርሃት በታደሰ ስሜት ማነቃቃት


RealAudioMP3 “በእስያ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማኅበርሰብ የቤተሰብ መረጋጋት የክርስቲያን ማኅበረሰብ የእምነት ራዕይ ለሥጋት የሚያጋልጠው አበይት ተጋርጦዎች ለሆኑት ፍርሃት ድንዛዜና ጨለምተኝነት ዕድል ካለ መስጠት በዓለም በጥልቅ መሆናችን በጊዜ ምልከቶች በጠቅላላ እውነተኛና ቅን ሰብአዊነት በሆነው ዘንድ ሁሉ በሚሠራው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለመመራት ገዛ እራስን በማቅረብ በታደሰ ስሜት በአዲስ መንፈስ ማወንጨፍ” የሚል ጥልቅ ሃሳብ የሠፈረበት የእስያ ፈደራላዊ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በቪየትናም፣ “የእስያ ፈደራላዊ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት አርባኛው ዓመት ምሥረታና ተጋርጦዎች በእስያ” በሚል ርእስ ሥር ለአስር ቀናት 100 የክፍለ ዓለሟ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ፈደራላዊ ኅብረት ተጠሪዎች በማሳተፍ ባካሄደው ይፋዊ ጉባኤ ፍጻሜ ባወጣው መግለጫ በማበከር፣ በእስያ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መንፈሳዊነት ለማረጋገጥ በእስያ ባህሎችና በወቅታዊ ሁነት የመፈስ ቅዱስ ጸጋዎች በእያንዳዱ ሰው ውስጥ ያለው የአዲስ ሰብአዊነት ዘር እርሱም በኢየሱስ የተገለጠው የሙሉ ሕይወት ጥማት በመለየት በእስያ አገሮች ለአዲስ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚጋረጠው እክል ቀርቦ ገዛ እራስ በማነጻጻር አግሎ ትሥሥርና ከተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች ጋር የሃይማኖች ነጻነት መረጋገጥ የሚለው የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት የሆነውን ብሎም ድኽነትን ለመዋጋት የክፍለ አለሟ ቀደምት ተወላጆች ዜጎችና ስደተኞችም እንዲሁም ሥነ ምኅዳር የሚያጋጥመው ችግር ለመቀረፍ ዓላማ ቅድሚያ የሚሰጥ የጋራ ውይይት በማነቃቃት ሙሉ መፍትሔ ማቅረብ የሚያስችል መንገድ ለመቀየት የተካሄደ ጉባኤ እንደነበርም ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ የጠቀሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት፦ “በእስያ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማረጋገጥ፣ ከኢየሱስ ጋር ግላዊ ግኑኝነት የቅዱሳኖችና የእምነት ሰማእታት ብቸኛው አዳኝ የሆነው ፍቅር ለሌሎች ለማሳወቅ የኖሩት እምነት አብነት በመከተል ለወንጌላዊ አገልግሎት ትጉ ስሜት ማነቃቃት” ወሳኝ መሆኑ የሚያመለክትና፣ “አስፍሆተ ወንጌል ስኬታማ እንዲሆን እይታው በተጨባጭ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ በማኖር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ተፈጥሮና ማኅበራዊ ኑሮ የሚነካ መሆኑ በሚያረጋግጥ እማኔ መሠረት ማቅረብ” አስፈላጊ ነው የሚል መሆኑ አስታውቀዋል።
“የጋራው ውይይት በድኾች ዘንድ የሚገለጠው እግዚአብሔርን በመለየት፣ በእያንዳንዱ ባህልና ሃይማኖት ያለው ባህላዊ ሃብት በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ዘንድ ያለው ሰብአዊ ክብር አቢይ ግምት በመስጠት ማከናወን ለተቃና ማኅበረሰብአዊ ውህደት መሠረት ነው” ስለዚህ “ጫጫታ ያልተሞላው ግሩም ማራኪ በቃልና በተግባር የሚኖር ትሁት ጸላይ አስተንታኝ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚያስቀድም ምስክርነት ወንጌላዊ ተልእኮ እርሱን የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ፣ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሚል የሕይወት ባህል ጥበቃ የሚለው ክብር በመከተል ይኸንን የሚያረጋግጥ ነቢያዊ አድማሱን የማይስት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማነቃቃት በእስያ የምተግኘ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነት ምእመናን ገዳማውያን ኃላፊነት” መሆኑ የእስያ ብፁዓን ጳጳሳት የጉባኤ ፍጻሜ ሰነድ እንዳሰመረበት የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ “ይኸንን መንገድ የሚከተል አዲስ አስፍሆተ ወንጌል አክራሪነት ጸንፈኛነትን በሰው ልጅና በተፈጥሮ ላይ የሚሰነዘረው የሽበራ ድርጊት የሚቃወም ነው” የሚል ሃሳብ የታከለበት ሰነድ መሆኑ አስታውቀዋል።
በመጨረሻውም፦ “በእስያ የሚገኘው ትንሹ የኢየሱስ መንጋ አለ ምንም ፍርሃትና መደናገጥ ከዓለም ሕዝብ ብዛት ውስጥ 60% ለሚሸፍነው የእስያ ሕዝብ ወንጌል በቃልና በሕይወት የሚል በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይና እግዚአብሔር አንድ ብቸኛ የሁሉም አባት መሆኑ የሚያረጋግጥ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እንዲነቃቃ” ምዕዳን በሚያቀርብ ሃሳብ ብፁዓን ጳጳሳቱ የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ ማጠቃለላቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.