2012-12-28 16:01:50

ር ሊ ጳ በነዲክት ከየታይዘ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች ጋ በጋራ ጸልየዋል፡


የኤውሮጳ የታይዘ ወጣቶች ማሕበረ ሰብ ዛሬ ሮም ውስጥ 35ኛ ግንኙነት መጀመራቸው እና ጉባኤው እስከ ፊታችን ወርሀ ጥር ሁለት ቀን 2013 እንደሚዘልቅ ተመልክተዋል።
የታይዘ ሀገራት አቀፍ የወጣቶች ግንኙነት የጸሎት እና የአስተንትኖ ግንኙነት እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ፡ እዚህ ሮም ውስጥ የሚገናኙ ወጣቶች ከ40ሺ በላይ መሆናቸው ተገልጠዋል።
በዚሁ ለጸሎት እና አስተንትኖ እዚህ ሮም ውስጥ የሚገኙ ኤውሮጳዊ የታይዘ ወጣቶች ነገ ቅዳሜ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ጋር እንደሚገናኙ እና በጋራ እንደሚጠልዩ የቫቲካን የዜና ምንጭ አስታውቀዋል።
በ40 ሺ የሚገመቱ የታይዘ ማሕበረ ሰብ አባላት ሮም ውስጥ በምያደርጉት ቆይታ በየሮም ሀገረ ስብከት ቁምስናዎች እና ባላ በጎ ፈቃድ ሰዎች በምያደርጉላቸው መስተንግዶ እንደሚሰነብቱ ተገልጠዋል።
የታይዘ ወጣቶች ማሕበረ ሰብ መሪ አኀው አሎይስ እንዳመለከቱት 35ኛው የታይዘ ወጣቶች ግንኙነት እዚህ ሮም ውስጥ በመሆኑ እና ከቅዱስ አባታችን ጋር በጋራ መጸለዩ ዓቢይ ደስታ የሚፈጥር መልካም አጋጣሚ ነው ።
የታይዘ የወጣቶች ማሕበረ ሰብ የካቶሊካዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና አንገሊካዊት አብያተ ክርስትያናት ተከታዮች አቀፍ እንደሆነ ይታወቃል።
የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት አማንያን የታይዘ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና ምልክት በጋራ የሚጓዙ በጸሎት እና አስተንትኖ ታቅፈው ሰላም እና እድገት ፈላጊዎች መሆናቸው የማሕበረ ሰቡ መሪ አኀው አሎይስ የሰጡት መግለጫ አስገንዝበዋል።
አኀው አሎይስ እንዳመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ለታይዘ ወጣቶች የሚሰጡት አባታዊ ምክር እና መምርያ በጉጉት የሚጠበቅ ጉዳይ ነው ።
የታይዘ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች በየዓመቱ በተለያዩ የኤውሮጳ ሀገራት በመገናኘት ለጸሎት እና አስተንትኖ እንደሚገናኙ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ ዓመት የዓመቱ መለወጫ ሮም ውስጥ በመሆን በዚች ዓለም ላይ ሰላም እና ፍትሕ ይከሰት ዘንድ በጋራ ለጸሎት እንደሚቀመጡ አኀው አሎይስ መግለጣቸው ተዘግበዋል።
ሥርዓተ ጸሎቱ በግጭት እና ጦርነት ጠንቅ ለምሳሌ በሶርያ ለስቃይ የተጋለጠው ህዝብ ሥቃዩ እንድያበቃ በተለያዩ ሀገራት የሚሳደዱ ክርስትያን ማሕበረ ሰብ ማሳደድ እንዲገታ ትኩረት በማድረግ ሥርዓተ ጸሎቱ እንደሚከናወንም አኀው አሎይስ በተቸማሪ መግለጣቸው ተነግረዋል።
በዚሁ እየተገባደደ የሚገኘው 2012 እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቁጣጠር በዓለም ዙርያ በሃይማኖታቸው ምክንያት 105 ሺ ክርስትያኖች ለሕልፈት መዳረጋቸው የተለያዩ ሪፖርቶች ያመልከታሉ ።
ይሁን እና ነገ ቅዳሜ ከቀትር በኃላ በሮም ሰዓት አቁጣጠር ስድስት ሰዓት ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ከየታይዘ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች አብረው በሚደግሙትጸሎት የሮም ነዋሪዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚጠበቁም ተወስተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.