2012-12-26 16:20:15

የኢየሱስ ክርስቶስ የሕጻንነት ግዜ ትኩረት የሰጠ የር.ሊ.ጳ በነዲክት መጽሐፍ።።


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የኢየሱስ ክርስቶስ የሕጻንነት ግዜ የተሰየመ መጽሐፍ መድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን። መጽሐፉ በጣልያን እና በሀገርታ አቀፍ ደረጃ በብዛት እየተሸጠ መሆኑ ቫቲካን አስታውቀዋል።።
ቅድስነታቸው ከአሁን በፊት የደረስዋቸው መጽሐፍት እና ያስተላለፍዋቸው ሐዋርያዊ መልእክቶችም እንዲሁ በብዛት መሸጣቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በቫቲካን የአንቀጸ ሃይማኖት ወይም ተአምኖተ ሃይማኖት ማሕበር አማካሪ እና የሥነ መልከኦት ጠቢብ ዶን ኒኮላ ቡክስ እንዳመለከቱት በነዲክት 16ኛ ለንባብ ያበቁት የኢየሱስ ክርስቶስ የሕጻንነት ግዜ የተሰየመ መጽሐፉ ውሉደ ክህነት ጨምሮ ምእመናን እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ብሎም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋ የሚያስተዋውቅ እና የሚያቀራርብ ነው።።
ከዚህ ባሻገርም ይህ በበነዲክት 16ኛ የተደረሰው መጽሐፍ የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ ባሕርይ የሆነውን እና እስከ ዛሬም ድረስ በምድር ላይ የቤተ ክርትያን ወንዶች እና ሴቶች ልጆች በአዲስ ሕይወት እንዲወለዱ እና እንድያድጉ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር እንዲሆን እግዚአብሔር የፈልገውን ልጅ ወላጅ እንደመሆንኗ መጠን በእናታዊ ፍቅር የለገሰችውን መቀበልዋ የሚያስረዳ እንደሆነ ዶን ኒኮላ ያመከታሉ።።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በምስራቁ ዓለም ቤተ ክርስትያን ሆነ በምዕራቡ ዓለም ቤተ ክርስትያን ሥርዓተ አምልኮ ሥነ ሥርዓት ለማርያም ከፍተኛ ክብር ስለሚሰጥ በክርስትያን ቤተ ሰቦች ዘንዳ ቅድስት ድንግል ማርያም እጂግ በጣም የምትወደድ እና የምትወደስ በመሆንዋ በስምዋ በተቋቋሙ አብያተ ክርስትያናት ሁሉ በመንፈሳዊ ሥን ሥርዓት ማለትም በመሥዋዕተ ቅዳሴ የምእመናን የወጣት ምእመናን ጭምር ተሳታፊነት ቁጥር እጅግ የበዛ ነው።። ይህም የመድኅኔ ዓለም እናት በመሆንዋ ነው ። ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የደረሱት መጽሐፍ የእምነተ ሃይማኖት ጥልቅ ሚስጢር እና ይዘታው የሚያስረዳ እና የሚያብራራ እንደሆነ ዶን ኒኮላስ ቡክስ በተጨማሪ ገልጠዋል።።
የሥነ መለኮት ጠቢቡ በማያያዝ እንደገለጡት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በቅርቡ በጀመሩት የማሕበራዊ መገናኛ በትዊተር በኩል መጽሐፍ ቅዱስን ለማስታዋወቅ እና ስብከተ ወንጌልን ለማሰራጨት በማሰብ በስራ ተጠምደው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።።
ቅዱስ ወንጌል ለማሰራጨት ውይይት ማድረግ እንደሚጠይቅ እና ለመወያየት አቅም የሌለው ሰው ቅዱስ መጽሐፍን ለመንገርም ሆነ ለመስበክ እንደሚቸገር ዶን ኒኮላ ቡክስ አመልክተዋል።።
የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘታ እና ሐሳብ በሚገባ መነገር እና መሰበክ ስላለበት ቅድስነታቸው ይህንኑ ለማብራራት ያለሰለሰ ጥረት በማካሄድ ላይ እንደሚገኙም በተጨማሪ ገልጠዋል።እውነትን ተንተርሶ የሚወያይ እና የሚናገር ድል እንደሚጐናጸፍም ነው ዶን ኒኮላ ቡክስ ያመለከቱት።።








All the contents on this site are copyrighted ©.