2012-12-26 15:41:44

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ “Urbi et Orbi-ለከተማይቱና ዓለም አቀፍ” ሓዋርያዊ ቡራኬ
የተስፋ ሕያውነት፦ በሶሪያ በቅድስት መሬትና በአፍሪቃ ሰላም እንዲሰፍን


RealAudioMP3 ምንም’ኳ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች አሁንም ግጭትና ለጥቃት የሚያጋልጡ ችግሮች የሚታዩ ቢሆንም ቅሉ “የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በምድር መልካምነት እንዲያብብ ነጻነት በራስ ወዳድነትና በራስ መዘጋት ላይ ድል እንዲነሳ አድርጓል” በማለ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና በላቲን ሥርዓት በተከበረው ለበዓለ ልደት ዘእግዚእነ ካሳረጉት መሥዋዕተ ቀዳሴ በመቀጠል “Urbi et Orbi - ለከተማ ሮማና ዓለም አቀፍ” ሓዋርያዊ ቡራኬ ከመስጠታቸው ቀደም በማድረግ በሶሪያ በቅድስት መሬትና በአፍርቃ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ በማቅረብ፣ በተለያዩ 65 ቋንቋዎች የመልካም በዓለ ልደት መልእክት እንዳሰሙ የራዲዮ ቫቲካን ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ “በዓለማችን አደገኛና አሰቃቂ አመጽና ግጭት ጦርነት ቢታይም ቅሉ፣ የዛሬ ሁለተ ሺሕ ዓመት በፊት በዓለም ያበበው የትስብእቱ ዘእግዚእነ እውነት የሚያመነጨው ሰላምና ፍቅር በዓለም የተስፋ ህያውነት የክርስትናው እርግጠኛነት የሚመሰክረው ፈጽሞ ሊያወድመውም ሆነ ሊያደበዝዘው የሚቻለው አይደለም” በማለት በዚህ ጦርነት ግጭትና አመጽ በተሞላው ዓለም ጥንታዊው የመዝሙረ ዳዊት እርጋታ የተሞላው ቃል መሠረት በማድረግ፣ የመልካም በዓለ ልደት መግለጫ መልእክት በማሰማት፣ የበዓለ ልደት የተስፋ የፍቅር የእውነትና የሰላም መልእክታቸው በዓለም ሁሉ በማስተጋባት እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ያለው የሶርያው ግጭት እልባት እንዲያገኝ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው ደ ካሮሊስ ገለጡ።
“አሁንም ደግሜ ደም መፋሰስ ተወግዶ ለሚሰቃዩት ለሚፈናቀሉት ዜጎች ሁሉ ድጋፍ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት እንዳይሰናከል በውይይት የሚረጋገጥ ፖለቲካ አስፈላጊ ነው። በዚህች አዳኛችን በተወለደባት መሬት ሰላም እንዲያብብ፣ እርሱ ለፍስልጥኤማውያንና እስራኤላውያንም ሰላሙን እንዲያወርድ በመካከላቸው ያለው የረዥም ዓመት ግጭትና መከፋፈል እክትሞለት ቆራጥ የጋራው ውይይት እንዲነቃቃ ያድርግ” ካሉ በኋላ፦ “በዓለ ልደት ዘእግዚእነ በምድር በተለይ ደግሞ አሸባሪያን ኃይሎች አመጽና ጥቃት በመዝራት የብዙ ክርስትያኖችን ሕይወት በጠቅላላ የሰው ልጅ ሕይወት ለሞት በሚዳርጉባቸው አገሮች በማሊ በናይጀሪያ ሰላም፣ መምስራቅ ዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ያለው ውጥረት ተወግዶ ለተፈናቃዮች ሁሉ ድጋፍና መጽናናት እንዲረጋገጥ እማጠናለሁ” እስያንም በማሰብ “የሰላሙ ንጉሥ ለአዲሱ የቻይና ያመራር አካላት እይታውን በማኖር እዲመራቸው፣ ሁሉን ለማክበር በመተባበርና በመደጋገፍ ለሚጸናው ኅብረሰብና ሕዝበ ዓለም ለመደጋገፍ መሠረት ለሆነው ሃይማኖት አቢይ ግምት እንዲሰጡ ይደግፋቸው” ብለዋል።
ላቲን አመሪካንም በማሰብ “ሕፃነ ኢየሱስ ላቲን አመሪካንና ሕዝቧን ይባረክ፣ የዚያች ክፍለ አለም ስደተኞችን ይደግፍ፣ ልማትና ጸረ የወንጀል ቡድኖች ባህል እንዲረጋገጥ መንግሥታት እንዲተጉ” አሳስበው፣ በቤተ ልሔም ከማርያም የተወለደው መድኃኔ ዓለም፣ “የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓምት የተወለደባት መሬት እሁንም በ 2012 ዓ.ም. ሕያው ነው በዚያች ምድር በእርሱ መወለድ ምክንያት እውነት አብበዋል፣ ስለዚህ ተስፋ በምድር ህያው ነው፣ ይኽ ተስፋ መከራ ችግር ቢፈራረቅብንም ዘወትር ታማኝ ነው” ካሉ በኋላ የግእዝ ቋንቋ ያካተተ እንደተለመደው በተለያዩ ቋንቋዎች ለሁሉም መልካም የበዓለ ልደት ዘእግዚእነ መልእክት አስተላልፈዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.