2012-12-21 16:37:08

የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ቢሮ አዲስ መመሪያ


RealAudioMP3 ትላትና ጧት በቫቲካን የዜናና ማኅተም ክፍል በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ቢሮ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ ቨርሳልዲና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ሉቾ አንገል ቫለኾ ቫልዳና የሂሳብ ክፍል ጠቅላይ ተጠሪ ስተፋኖ ፍራለዮኒ፣ መቆጣጠርና መከታተል ብቻ ሳይሆን አዲስ መንገድ የሚያመላክትና መርሃ ግብሮችን የሚጠቁምና እዲወጠን የማድረግ ኃላፊነት የሚያሰጠው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ያጸደቁት የመመሪያ ሰነድ ርእስ ሥር ጋዜጣዊ መገልጫ መስጠታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።
ብፁዕ ካርዲናል ቨርሳልዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ “በቅድሚያ ጋዜጣዊ መገልጫ የመስጠቱ ውሳኔ ይኽ የቅድስት መንበር የኤኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው የባላይ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ከጠቅላላ የቅድስት መንበርና የቫቲካን የኤኮኖሚ ጉዳይ ቢሮዎች ጋር አዲሱ የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ቢሮ የሚከተለው አዲስ መመሪያ ይፋ ለማቅረብ የተካሄደው ግኑኝነትና ቀጥሎ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ቅድስት መንበር በኤኮኖሚ ዘርፍ የምትከተለው የግልጽነት አሰራር የሚያጎላ ነው። ስለዚህ ግልጽነትና ግኑኝነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥና ከውጭ ዓለም ጋር ጭምር የሚያነቃቃ ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ ጠቁመው አያይዘውም “አዲሱ መመሪያ ይኽ የቅድስት መንበር የኤክኖሚ ጉዳይ ተከታታይ የበላይ ቢሮ መዋቅራዊነቱን አቢይ ግምት የሚያሰጥ መሆኑም አንቀጽ አንድ እንደሚያመለክተው፦ ‘የኤኮኖሚ ሂደት አተኩሮውና መርሃ ግብሮችን የሚጠቁም፣ ይኽ የበላይ ቢሮ ለመቆጣጠርና ለግልጽነት አሰራር ቀርቦ የመከታተል ሚናውን የሚደግፍ ሓሳብ’ ሥር ተመልክቶ ይገኛል። ስለዚህ ወጪና ገቢ መቆጣጠር ከሚለው የግልጽነት የተለመደ አሰራር ከሚያካተው ኃላፊነቱ ባሻገር የኤኮኖሚ ሂደት መጠቆምና መርሃ ግብር የማቅረብ መዋቅራዊ ሥልጣን አልነበረውም ስለዚህ አዲሱ መመሪያ፣ ይኽ የቅድስት መንበር መዋቅር ይኸን አዲስ ሥልጣን ይመለከተዋል የሚል ነው” ካሉ በኋላ “ይኽ የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ የበላይ ቢሮ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አስፈልጊነቱ ከላተራነንሰ ስምምነት የቅድስት መንበር ሉኣላዊነት በትክክል መረጋገጥ በኋላ፣ የስምምነቱ ታሪካዊ ሂደቱና ምክንያቱንም ጭምር በመከለስ ታሪካዊ ለውጦችንም ጭምር ግምት በመስጠት እውን የሆነ የቅድስት መንበር ቢሮ ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ወቅታዊው የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ በተመለከተ ትንተና በመስጠት አሉታዊ ጎኑን ካብራሩ በኋላ፣ ቤተ ክርስትያን የዓለም ባትሆንም በዓለም የምትገኝ ነች። ስለዚህ ገዛ እራሷን በመመልከት ከምእመናን የሚሰጠው ምጽዋት ድጋፍ በጥበብ መጠቀምና ማስተዳደር የሚለው ውሳኔ የሚያጎለብትና ከጠቅላላ የኤኮኖሚ ጉዳይ ከሚከታተሉ መዋቅሮችና ከቅድስት መንበር መዋቅሮች ጋር የሚደረገው መተባበር የሚያጸና መሆኑ ሲያመለክቱ፦ “ግልጸነት ታማኝነት እውነት በግንኙነት የሚል፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረታውያን የማይለወጡ የእምነት ድንጋጌዎች የሚከተል በመሆኑም የአዳም ኃጢአት ለፈተና እንድንጋለጥ ዳርጎናል ስለዚህ ይህ መዋቅር በዚህ ሰብአዊ ግደፈት በተያያዘ መልኩ ሊጋባ የሚችለው ጉድለት እንዳይኖር በቅድስት መንበር የኮኖሚ ጉዳይ በተመለከተ የተለያዩ የውስጥ መዋቅሮች የኤኮኖሚ ጉዳይ የመቆጣጠርና የመከታተል ኃላፊነት አለው” በማለት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳጠናቀቁ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.