2012-12-21 16:30:11

ቅዱስ ኣባታችን .ር.ሊ.ጳ. አዲስ የቅድስና አዋጅ ድንጋጌ ፈረሙ


RealAudioMP3 በኦትራንቶ በ 1480 ዓ.ም. በቱርክ ወረራ ወቅት ስለ እምነታቸው የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት ኢጣሊያዊ አንቶኒዮ ፕሪማልዶ የሚገኝባቸው በጠቅላላ 800 እንዲሁም ሌሎች 40 ብፅዕና የሚታወጅላቸው በስፐይን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የእምነት ሰማዓት ለሆኑት በተጨማሪም ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የሚገኙባቸው ሌሎች 10 የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብለው እንዲሰየሙ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ላቀረበላቸው የድንጋጌ ሰነድ በማጤን አዋጁን ማጽደቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብለው እንደሚሰየሙና ብፅዕና ብሎም ቅድስና እንዲታወጅላቸው መሠረተ ሃሳብ አቅራቢ አባ አንቶኒዮ ማራዞ ከቫቲካን ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ር.ሊ.ጳ. ሞንቲኒ ወይንም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት መለያቸው ጳውሎስ ስድስተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብለው እንዲሰየሙ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በማወጃቸው በኢጣሊያና በውጭ አገር ለሚገኙት ለእግዚአብሔር አገልጋይ ለብፅዕና ለቅድስና እግዚአብሔር እንዲያበቃቸው ለሚጸልዩት ምእመናን ሁሉ በእውነቱ እጅግ ደስ የሚያሰኝ መልእክት ነው። ጳውሎስ ስድስተኛ በቅድስት አንዲት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን አንገብጋቢ እና ደምቆ የሚታይ አስደናቂ ታሪክ የፈጸሙ በተለይ ደግሞ ክርስትያን የሚያስብለን መሠረታዊ ጥልቅ መለያችን እንድናውቅና ለመኖር የሚያበቃ ሥልጣናዊ ትምህርት የለገሱ ወደ እውነተኛውና ሰብአዊው ክርስቶስ እንድንመለስ የመሩን ናቸው ብለዋል።
ስለ ር.ሊ.ጳ. ሞንቲኒ ብዙ ሲባል እንሰማለን ይህ ሕዝብ የሚለው ሁሉ የሳቸው ሰነድና ታሪክ የተመለከትን እንደሆነም የማይጋጭ እውነተኛ አባባል እንደሆነም እንረዳለን፣ ትተውሉን ያለፉት የቤተ ክርስትያን ሰነዶች ዓዋዲና ሐዋርያዊ መልእክቶቻቸው ጭምር የተመለከትን እንደሆን የኅዳሴ መንፈስ ያጎሉ እጅግ ተቆርቋሪ ለሌሎች አቢይ ሥፍራ መስጠት ለሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊ የሚባሉት ሁሉ እንዲቀርብ ማንም ከዚህ መሠረታዊ ጉዳይ እንዳይነጠል ለብዙዎች ችግር ቅርብ በመሆን ለውሳኔ ቁጡብ ችኩል አለ መሆን የሚያንጸባርቁ የሌሎች አሉታዊ ሳይሆን አወንታዊ ገጽታ መመልከት የሚወዱ፣ ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ያወጁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያሰሙት ንግግር፣ ከአበይት የመንግሥታት ተጠሪዎች ከተራ ሰዎች ጋር ያካሄዱት ግኑኝነቶች የሮማ ጳጳስ በመሆናቸውም በሮማ ሰበካ የጎበኙዋቸው ከክፍለ ከተማ ውጭ ለሚገኙት ቁምስናዎች ቅርብ በመሆን ያሳዩት ተግባር በእውነቱ በሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር ተቆርቋሪ ሰቂለ ኅሊና ወዳጅ አስተንታኝ ጥልቅ ተጨባጭ እምነት ስለ ሰላም ስለ ሰብአዊ ክብር ጥበቃና አክብሮት የሕይወት ባህል ጥበቃና መስፋፋት ለቤተሰብ አቢይ ትኵረት እንዲሰጥ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የምታጎላው የሕይወት ባህል ብጥልቀት በጽናት ያነቃቁና በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው እነዚህን ጉዳዮች ማእከልነት የሰጡት ናቸው ብለዋል።
ቤተ ክርስቲያን ገዛ እራስዋን እንድትመለከት ያነቃቁ እራስ ከመመልከት የመነጨ እራስን ማወቅ መሠረት ወደ ሌላ መቅረብ፣ ክርስቶስን ማቅረብ የሚል መርህ የተከተሉ ናቸው፣ አንዲት እናት በሳቸው አማላጅነት የተጸነሰው ልጃቸውና የእሳቸው ሕይወት ለአደጋ ተጋልጦ ለሞት አደጋ ሊዳረግ ሊዳረግ ነው ተብሎ ሲንገር ከዚህ አደጋ እንዲተርፉ እግዚአብሔር በሞንቲኒ አማላጅነት ያደለው የፈወስ ተአምር ጉዳይ በተለያዩ የስነ ሕክምናና የቲዮሎጊያ እንዲሁም የስነ ተአመራት ሊቃውነት ጥናት እያካሄዱበት መሆናቸው ገልጠው ይኽ ተአመር እሳቸው “Humanae Vitae-ሰብአዊ ሕይወት” የተሰየመው አዋዲ መልእክታቸው የሚያጎላ ነው። ስለ ሚሥጢረ ተክሊል ለቤተሰብ ጥበቃ፣ ስለ ሚወለዱት ሕፃናት ጥበቃ፣ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የማክበሩ ውሳኔ ጠለቅ አድርገው ምክንያቱን በማስገንዘብ ያስተላለፉት ሥልጣናዊ ትምህርት የሚያጎላ ተአመር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅድስና ከሚታወጅላቸው ውስጥ የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያምና የቅድስት ካተሪ የደናግል ልኡካን ማህበር መሥራች እ.ኤ.አ. ግንቦት 26 ቀን 1874 ዓ.ም. በኮሎምቢያ ተወልደው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 21 ቀን 1949 ዓ.ም. በተወለዱበት አገር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ብፅዕት ላውራ ዲሳንታ ካተሪና ዳ ሲየና፣ በመክሲኮ ዛፖፓና ከተማ ሚያዝያ 27 ቀን 1878 ዓ.ም. ተወልደው በመክሲኮ ጉዋዳላኻራ ሰነ 24 ቀን 1963 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቅድስት ማርገሪታ ማሪያና የድኾች አገልጋይ የድናግል ማኅበር ተባባሪ መሥራች ብፅዕት ማሪያ ጓዳሉፐ እንደሚገኙባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.