2012-12-19 17:25:32

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ እመቤታችን ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነውን ኢየሱስን ለመለኮታዊው ፍቃድ በሙላት በመታዘዝ በእምነትና በሥጋ ተቀብላው ይሄው የእግዚአብሔር ተስፋ እውን እስኪሆን ድረስ ከማንኛው በላይ የተጠባበቀችው በመሆንዋ በዚሁ የዘመነ ምጽአት ጉዞአችን ልዩ ቦታ ትይዛለች፣ ዛሬ ከታላቁ ምሥጢር የሆነው ብሥራተ ገብርኤል በመነሣት አጠር ባለ መንገድ ከእናንተ ጋር ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም እምነት ለማሰላሰል እወዳለሁ፣
“ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምል እተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ - ደስ ይበልሽ! ጸጋ የሞላሽ ሆይ! እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው” (ሉቃ 1፤28)፣ እነኚህ ወንጌላዊው ሉቃስ የሚያቀርብልን ቃላት፤ ሊቀ መላእክቱ ገብርኤል ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ያቀረበላት ሰላምታን ይገልጣሉ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ስትሰማው “ተፈሥሒ - ደስ ይበልሽ” የሚለው ቃል የሆነ የሰላምታ ቃል ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ ቃል በቅዱስ መጽሐፍ ቋንቋ ገብቶ በጥንቃቄ ሲነበብ እጅግ ጥልቅ የሆነ ትርጉም አለው፣ ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን የግሪክ ቋንቋ ትርጉም አራት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፤ ሁሌ ደግሞ በመሲሁ መምጣት የሚገኝ ደስታ የምሥራች ብሥራት ያመለክታል (ሶፎ 3፤14 ዮኤ 2፤21 ዘካ 9፤9 ሰቆ 4፤21)፣ ስለዚህ የመልአኩ ሰላምታ ለማርያም የሚቀርብ የደስታ ጥሪ ነው፤ ደስታውም በዓለማችን በሕይወት ውሱንነት በስቃይ በሞት በመጥፎ ነገሮች የሚከሰተው መለኮታዊው ብርሃንን የሚያደበዝዝ በሚመስለው ጨለማ የከበበው ኅዘን እንዳበቃለት የሚያበስር እጅግ ጥልቅ የሆነ ደስታ ነው፣ የምሥራች ዜና የሆነውን የወንጌል ስብከት መጀመርን የሚያመለክት ሰላምታ ነው፣
ለመሆኑ ለምንድር ነው እመቤታችን ድንግል ማርያም እንዲህ ባለ ሁኔታ ደስ እንዲላት ጥሪ የሚቀርብላት፧ ብለን የጠየቅን እንድሆነ መልሱ በሰላምታው ሁለተኛ ክፍል እናገኘዋለን፤ “እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው” ይላል፣ እዚህም የዚሁ ሐረግ ትርጉም ለመረዳት እንደገና ወደ ብሉይ ኪዳን መለስ ብለን መመልከት አለብን፣ በትንቢተ ጾፎንያስ (3፤14-17) “የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ … የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም። … አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤” ይላል፣ በእነዚህ ቃላት ውስጥ ለጽዮን ልጅ ለእስራኤል ሁለት ተስፋዎች እንደተሰጡ ያመለክታል፣ እግዚአብሔር እንደ አዳኝ ይመጣል መኖርያውም በሕዝቡ መካከል በጽዮን ልጅ ማህጸን ያደርጋል፣ በገብር ኤል መል አክና በእመቤታችን ድንግል ማርያም በተካሄደው ውይይት ይህ ትንቢት እውን ይሆናል፣ ሕዝብን በመወከል የእግዚአብሔር ሙሽራ የምትሆነው እውነተኛው የጽዮን ልጅ እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፤ በእርሷም ወሳኙ የእግዚአብሔር መምጣት መጠባበቅ እውን ይሆናል፤ ሕያው እግዚአብሔር በእርሷ ማደርያ ያገኛል፣
በመልአኩ ሰላምታ እመቤታችን ድንግል ማርያም “ጸጋ የተሞላሽ” ተባለች፤ በግሪክ ቋንቋ የጸጋ ሥርወ ቃል ደስታ ከሚለው ሥርወ ቃል ጋር አንድ ነው፣ በዚሁ መግለጫም የእመቤታችን ድንግል ማርያም ደስታ ከጸጋ ደስታ እንደሚመጣ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር በመወሃህድ የሚገኝና ከእርሱ ጋር የሕይወት ትሥስር እንዳላት በማመለከት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሁለመናው በእግዚአብሔር የታነጸችና የመንፈስ ቅዱስ ማኅደር መሆንዋን ያመለክታል፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ልዩና አንድያ በሆነ መንገድ ለፈጣሪዋ በርዋን በርግዳ የከፈተች እና አለምንም ገደብ ሁለመናዋን በእጆቹ ያኖረች ፍጡር ናት፣ እርሷ በሙላት ከጌታና በጌታ ጋር ባላት ግኑኝነት ትኖራለች፤ እግዚአብሔር በሕዝቡ ጉዞ የሚሰጣቸውን ምልክቶች በልብዋ ለማኖር በማዳመጥ ሁኔታ ትኖር ነበር፣ እንዲህ በማድረግዋም በአንድ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የእምነትና የተስፋ ታሪክ ገባች፣ ይህም የአጠቃላይ የሕይወትዋ ኑሮ ያቋቁማል፣ በሰማችው ቃልም ለመለኮታዊው ፍቃድ በእምነት ትታዘዛለች፣
ወንጌላዊው ሉቃስ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሁኔታ ከአብርሃም ሁኔታ ጋር በማነጻጸር ይተርከዋል፣ አብርሃም እንደ ታልቅ አባታችንና የአማኞች አባት ከሚኖርበት አገሩ ዋስትና ካለው ኑሮው እንዲወጣ እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ አዲስ ሕይወት ለመጀመር መለኮታዊ ተስፋን ብቻ ይዞ ወደ ማያውቀው አገር ይጓዛል፤ እመቤታችን ድንግል ማርያምም በእግዚአብሔር መልእክተኛ በተነገራት ቃል በሙላት በመተማመን የእምነት ምሳሌና የአማኞች ሁሉ እናት ሆነች፣
ሌላ አስፈላጊ ነጥብ ለማጕላት እፈልጋለሁ፤ ነፍስህን ለእግዚአብሔርና ለተግባሩ በእምነት ክፍት ማድረግ የጨለማ ነገርም ይገኝበታል፣ በሰው ልጅና በእግዚአብሔር መካከል የሚደረገው ግኑኝነት በፈጣሪና በፍጡር መሃከል ያለውን ርቀት አይደመሥሰውም፤ ሐዋርያ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ጥበብ ጥልቀትን አስመልክቶ “የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤” (ሮሜ 11፤33) ብሎ የሚገልጠውን ጥልቀት አይደምሠውም፣ ነገር ግን መለኮታዊው ፍቃድ ምሥጢራዊ ሆኖ እንደ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስምዖን ነቢይ ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ለማግባት በሄዱበት ጊዜ በትንቢት ሰይፍ ልብሽን ይሰነጥቃል እንዳለው ከግል ፍቃድ ጋር ሊስማማም ባይችል እንደ እመቤታችን ድንግል ማርያም በልበ ሙሉነት ለእግዚአብሔር ክፍት በሆነ መንገድ የሚቀርብ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቃድን ለመቀበል እሚችልበት ደረጃ ይደርሳል፣ የአባታችን አብርሃም የእምነት ጉዞን የተመለከትን እንደሆነ የልጅ ስጦታ አግኝቶ ልጁን ይስሓቅን ባገኘ ጊዜ የተሰማው ደስታ ታላቅ ነበር ሆኖም ግን የጨለማ ጊዜም አለ ማለት እግዚአብሔር ያኔ የሰጠው ልጁ ይስሓቅን በሞርያ ተራራ መስዋዕት እንዲያቀርብለት በጠየቀበት ጊዜ የተሰማውን ኃዘን እንዳለም እንረዳለን፣ በሞርያ ተራራ ላይ ልጁን መሥዋዕት ለማደረግ ሲዘጋጅ መል አኩ፤ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ።” (ዘፍ 22፤12) አብርሃም ሁኔታው ምሥጢራዊና ከባድ እንዲያው ልትቀበለው የማይቻል በሚመስልበትም ጊዜ ሳይቀር በታማኙ እግዚአብሔር ተስፋ የነበረው ሙሉ መተማመን አልጎደለም፣ ለማርያምም ልክ እንዲሁ ነበር፣ እምነትዋ የምሥራች ዜና በተቀበለችበት ጊዜ ደስ የሚያሰኝ ነበር ሆኖም ግን ለትንሣኤው ብርሃን እንድትደርስ የልጅዋ መስቀል ጨለማን መሻገር ነበራት፣ (ይቀጥላል)








All the contents on this site are copyrighted ©.