2012-12-19 14:34:55

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ ሕፃንነትን (ጨቅላነት) መንከባከብ የሁሉም ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ሮማ የሚገኘው “Pediatrico Bambino Gesù ሕፃነት ኢየሱስ ‘የሕፃናት ቤተ ሕክምና’” የበዓለ ልደት ዘእግዚእነ መቃረብ ምክንያት በምድረግ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በለገሡት ምዕዳን፣ “ሕፃናት ደስታና ዋስትና” እንደሚያሻቸው ገልጠው፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ ቡራኬ ለሁሉም አድርሰው፣ ቅዱስነታቸው የዚህ የሕፃነ ኢየሱስ ትልቁ ሕክምና ቤት በቅርብ የሚከታተሉት መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ አረጋግጠዋል።
ብፁዕነታቸው በዚህ አጋጣሚም በቅርቡ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በኒውታውን ትምህርት ቤት በሕፃናት ላይ የተፈጸመው አሰቃቂው ቅትለት በማስታወስም፣ ስለ ሕፃናቱ እንዲጸለይም አደራ በማለት የዚህ ዓይነት ዘግናኝ የሞት ጥቃት እንዳይከሰት ሁሉም መንግሥታት የሕፃናት ሕይወት ጥበቃና ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ስኬታማ ደንብ እግብር ላይ እንዲያውሉ በዚህ አጋጣሚ ተማጥነዋል።
ሕፃናት የኅብረትሰብ ክፍል ለሚያቀርቡት ኅብረ ጥያቄ ለአቅመ አዳም ከደረሰው የኅብረተሰብ ክፍል ከወላጆች ተገቢ መልስ ማግኘት እንዲችሉ ሁሉም ከሕፃናት በመማመር የሕይወት ክቡር ዋጋ በመኖር በቃልና በሕይወት አብነት ሆነው መገኘት እንደሚገባቸው ከገለጡ በኋላ፣ ይህ ሮማ የሚገኘው ዓቢይ ሕክምና ቤት የሚሰጠው የተሟላ አገልግሎት ለተደናቂነቱ መሠረት መሆኑ አስታውሰው፣ ሐኪሞች ሠራተኞች የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች በጠቅላላ በሕክምና ቤቱ በተለያየ ሙያ የሚያገለግሉት አመስግነው፣ በእውነት የሚኖር ሕይወት ምስክር ለመሆን በሚወለደው መድኃኔ ዓለም ታምነን በእርሱ በመመራት አሮጌውን ስብእናችን ከሚያቀርብልን የራስ ወዳድነት ምርጫ ተገለን በመኖር በሚወለደው ኢየሱስ ለሚገለጠው እውነተኛው አዲስ ሕይወት ምስክሮች እንሁን እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.