2012-12-17 15:05:01

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ዓላማውን በመለየት ማንበብን ይጠይቃል


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ የሆነው የ 2013 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት በተመለከተ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መልእክቱ ዓለማችን የተጋረጠበት ወቅታዊው የኤኮኖሚው ቀውስ ለመቅረፍ ዓለም የሚከተለው እርሱም የካፒታሊዝም ሥነ ኤኮኖሚ ተጽእኖ የተሞላው የማኅበራዊ ሰበአዊ መብትና ክብር ጥበቃ አደጋ እያስከተለ ያለው በሃብታሙና በድኻው መካከል ያለው ልዩነት እጅግ እየሰፋ እንዲሄድ የሚያደረገው የኤኮኖሚው ስልት መለወጥ አስፈላጊ መሆኑ ያሰመሩበት ሃሳብ ላይ ሲያተኩሩ በኢጣሊያ በዚያ ጥልቅ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የ 2013 ዓ.ም. የሰላም መልእክት ውስጥ የተክሊል ምሥጢር በተመለከተ እርሱም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸና መሆኑና ይኽ ውሳኔና ይኽ ዓይነቱ ጋብቻ በሰብአዊ አመክንዮ ታዋቂነት ያለው ሆኖ ከዚህ ጋር በማያያዝም ሰብአዊና ማኅበራዊ እሴቶች ተገቢ ትኵረት እንዲሰጥባቸው ይኽም የሕይወት ባህል ማክበር ከሚለው በመንደርደር ያብራሩ ሆነው እያለ፣ ሰላም ለማረጋገጥ ይኸንን የሕይወት ባህል ማክበር ወሳኝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያመለከቱት ሃሳብ ለየት ባለ መልክ በማንበብ ቤተ ክርስትያን ሌሎች ዓይነት የጋብቻ ምርጫዎች ጸረ ሰላም ናቸው በሚል አገላለጥ እንዳስቀመጠች በሚያስመስል ዓይነት አገላለጥ በማንበብ የመልክእቱን ዓለማ የሳተ ትንተና ሲሰጡበት መታየቱ የሚገርም ነው ብለዋል።
ብዙዎች የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ወቅታዊነት ያለው ወቅታዊው ዓለም ሰብአዊ ማኅበራዊ ጉዳይ በጥልቀት የሚዳስስ ሆኖ እያለ፣ ቆንጸል እያንደረጉ በማንበብ የመልእክት ትክክለኛና እውነትኛውና ሙሉ መልእክቱን ለማንበብ የተሳናቸው ሆነው ይገኛሉ። ሥራ አጥነት እንዲቀረፍ ይኽም ሥራ የማግኘት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ውስጥ አንዱ መሆኑ የሚያረጋግጥ ዓለማችን የሚከተለው የልማት ስልት እንዲቀየር እርሱም ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ እንዲሆን ሥነ ምግባር የሚከተል መሆን እንዳለበት በዓማችን ያንሰራፋው የምግብ እጥረትና እርሃብ በቀላሉ ለመቅረፍ እየተቻል በቸልተኝንነት የሚታይ ጉዳይ እየሆነ ሰው በምግብ እጥረት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ማየቱ የሁሉም ኃላፊነት ነው የሚለው ቅዱስነታቸው እውነት በፍቅር የተሰየመው ዓዋዲ መልእክትና እንዲሁም ሰላም በምድር የተሰየመው በቅርቡ 50ኛው ዓመቱ የሚዘከረው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛው ዓዋዲ መልክት አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አስታውሰው፣ የቅድስት ቤተ ክርስትያን የሰላም መልእክት ዓላማውን በሚገባ መረዳት ይጠይቃል ካሉ በኋላ በሚሥጢረ ተክሊል የሚጸናው ውህደት ከሌሎች ዓይነት ውህደቶች ጋር ማደናገር አያስፈልግም በማለት ያቀረቡትን ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.