2012-12-17 17:28:16

የር.ሊ.ጳ የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ትምህርት አቅርበው ከጸሎት በኋላ ደግሞ ባለፉት ዕለታት በተባበሩት መንግሥታት አመሪካ በኒውቶን ትምህርት ቤት በከነቲከት ከተማ 20 ሕጻናት የሚገኙባቸው የ27 ሰዎች ሕይወት ያጠፋ አረሜናዊ ፍጻሜ ዜና በታላቅ ሓዘን እንደሰሙት የዚሁ ታላቅ ጥፋት ሰላባ ለሆኑት ደግሞ በጸሎታቸው እንደሚያስብዋቸውና የእግዚአብሔር ቡራኬ እንደለመኑላቸው ገልጠዋል፣
በላቲኑ ሥርዓት ትናንትና የተነበበው ወንጌል መጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲያጠምቅ ይህንን የንስሐ ጥምቀት የተቀበሉ አይሁዳውያን ለመዳን ምን እንዳርግ ብለው ሲጠይቁት እውነተኛ ለውጥ በቅንነት በመጓዝና ሌሎችን እንደራስ አድርጎ በመንከባከብ እንደሚጀምር ይግልጣል፣ ቅዱስነታቸውን የዮሐንስን ጥሪ እንደገና በመድገም ፍትሕና የፍቅር ሥራ አስፈላጊዎች መሆናቸውን ገልጠዋል፣
ወንጌላዊው ሉቃስ እንደሚተርከው ዮሐንስ ከተለያዩ ሰዎች ይወያያል፣ “ሕዝቡም። እንግዲህ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። መልሶም። ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር። ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው። መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት። ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው። ጭፍሮችም ደግሞ። እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም። በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው።” (3፤10-14) ይህንን ውይይት ቅዱስነታቸው አጠር ባሉ ቃላት ሲገልጡት ፍትሕ በምግባረ ሠናይ እንድሚጐልበት ያመለክተናል ብለዋል፣
“ፍትሕ ምንም ከሌለው ድኃና ከአስፈላጊ በላይ ካለው ሃብታም መካከል ያለው ልዩነትን ለመሻገርና ለማመዛዘን ይጠይቃል፣ የፍቅር ምግባረ ሠናይ ያለህን ሃብት ከማከማቸትና ከመከላከል የጓደኛን ችግር በመመልከት ጓደኛን ለመርዳት ያስችላል፣ ፍትሕና የፍቅር ምግባረ ሠናይ አይቃረኑም ሆኖም ግን ሁለታቸው አንዱ ለአንዱ ያስፈልጋል ይሟሟላሉም፣
መጥምቁ ዮሐንስ ለቀረጥ ሰብሳቢዎች “ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ” ይላቸዋል።
በእግዚአብሔር ስም የተላከው ነቢዩ ልዩ ወይም ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮች አይጠይቅም ሆኖም ግን ግዴታህን በቅንነት መፈጸም እንዳለባቸው ይነግራቸዋል፣ ለዘለዓለማዊ ሕይወት የመጀመርያው እርምጃ የእግዚአብሔር ትእዛዛትን መጠበቅ ነው፤ እላይ በተጠቀሰው የቀራጮች ጉዳይ አትስረቅ የሚለው ሰባተኛውን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ያሳስባል፣
ለወታደሮቹም “በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ “ ይላቸዋል፣
እዚህ ላይም እውነተኛ የልብ ለውጥ በቅንነት በመሥራትና ሌሎችን በማክበር ይጀምራል፣ ይህ ለሁሉም የሚሆን ነው በተለይ ግን ታላቅ ኃላፊነት ላላቸው ሰዎች ይመለከታል፣
ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.