2012-12-17 15:02:01

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መግለጫ ግርግም ለሚቀመጡት የሕፃን ኢየሱስ ቅዱስ ምስል ባረኩ


RealAudioMP3 ትላትና እሁድ እኩለ ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሐዋርያዊ መስኮታችው ሆነው በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው እንዳበቁ እንደ ተለመደው ለበዓለ ልደት መግለጫ ግርግም ውስጥ ለሚቀመጠው የሕፃን ኢየሱስ ምስሎችን መባረካቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የዚህ ጳጳሳዊ ባዚሊካ ሊቀ ካህናት በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ከተሳተፉት ከሮማ የተለያዩ ቁምስናዎች የወጣቶች ማእከል አባላት የተወጣጡት ታዳጊ ወጣቶችና ወላጆቻቸው ጋር እንደተገናኙ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።
ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ ባሰሙት ስብከት እግዚአብሔር ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ለመገናኘት የሚፈልግ ከሆነ ልባችን ይለወጥ ዘንድ ያለው አስፈላጊነት የሚያረጋግጡልን ሰዎች እግዚአብሔር ይልክልናል” በማለት “ከእነርሱም ውስጥ እናቴ ብፅዕት ተረዛን ዘካልኩታ የቅርብ ትውስት ናቸው፣ እኚህ በቅድስት ቤተ ክርስትያን ብፅዕና የታወጀላቸው ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበተ ዕለት በካልኩታ ኃይለኛ መብረቅና ነጎድጓድ ተከስቶ እንደነበርና በዚህ የጨለማ ምልክት የክርስቶስ ብርሃንን በመመስከር ይኽ ምልክት እያንዳንዳችን ወደ ቤተ ልሔም የሚመራ ብርሃን እንድንሆን የሚጠራ እግዝአብሔር ያወረደው ምልክት መሆኑ፣ እናቴ ብፅዕት ተረዛ በጣረ ሞት ላይ እያሉ ከጎናቸው የነበሩት በሳቸው ለተመሠረተው የደናግሎም ማኅበር አባል በማለት የሰጡት መግለጫ አስታውሰው፣ የእናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘካልኩታ አብነት እንከተል እንዳሉ” ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.