2012-12-17 14:54:30

ለዓለም አቀፍ የክህነት/ገዳማዊ ጥሪ ቀን
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሊገኙ ፈቃደኞች ለሆኑት ሁሉ እግዚአብሔር ቅርብ ይሆናል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. አራተኛው የፋሲካ ዕለተ ሰንበት ለሚከበረው 50ኛው ዓለም አቀፍ ለመናንያን ጥሪ የጸሎት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “የመናንያን ጥሪ በእምነት ላይ ለሚጸናው ተስፋ ምልክት” በሚል ርእስ ሥር የሚያስተላልፉት መልእክት ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ መውጣቱ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ “አንድ የኢየሱስ ሐዋርያ መላ ሕይወቱ በክህናታዊ ወይንም በገዳማዊና መናንያን ሕይወት ለመሠዋት የእግዚአብሔርን ጥሪ እሺ ብሎ ሲቀበል ለቤተ ክርስትያን መጻኢና ለቤተ ክርስያን የአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት በእማኔና በተስፋ ለመመልከት የሚደግፍ በማኅበረ ክርስትያን ለተደረሰው የእምነት ብስለት መግለጫ ነው” በማለት ለእምነት ዓመትና ለዝክረ 50ኛው ዓመት የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጅማሬ ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ላይ የገለጡት ሃሳብ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው የክህነትና የመናንያን ወይንም የገዳማዊ ሕይወት ጥሪ ያለው አስፈላጊነት ሲያስረዱ፦ “ክህነታዊ ገዳማዊ ጥሪ ከክርስቶስ ጋር ከሚጸናው ግላዊ ቅን በእርሱ ፈቃድ ለመግባት በእርሱ ላይ መተማመን ከሚያረጋግጠው የእምነት ገጠመኝ የሚወለድ መሆኑ” ባስተላለፉት መልእክት በማስመር፣ “በእምነት ተመክሮ ማደግ ይኽም ከኢየሱስ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት እጅግ አፍስፈላጊ ነው። “ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ለማነቃቃት በተለይ የማኅበረ ቤተ ክርስትያንና የካህናት ሚና ወሳኝ ነው። ስለዚህ ግላዊ አስተንትኖ የግልና የማኅበር ጸሎት የቤተ ክርስትያን የሁሉም ቅዱሳትና የሊጡርጊያ ጸሎት” ያለው አስፈላጊነት ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
“ቀጣይ ጽኑና ጥልቅ ጸሎት እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደማይተውና ዘወትር በዓለም ምልክት የሆነውን የክህነት የገዳማዊ ሕይወት የመናንያን ጥሪ የተስፋ ምልክት የሆነውን ልዩ ጥሪ በማነቃቃት እንደሚደግፈው ለሚያረጋግጠው የማኅበረ ክርስትያን እምነት የሚያሳድግ ነው። በተስፋ ለምንጠባበቀው መጻኢነትና በተለያየ እርካታ እጦትና አለ መሳካት በሚጎላበት በወቅታዊው ሁነትም አወንታዊ ገጽታውን የሚያጎላ ተስፋ ላይ የጸና እርሱም እግዚአብሔር ለብቻችን እንደማይተወን ለቃሉ ታማኝ መሆኑ የሁሉም ተስፋዎች መሰረት ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በአእምሮ ሊደረስ የማይቻለውን መንገድ በመከተል በእርሱ ሊገኙ ለሚፈቅዱለት ሁሉ የሚደርስ መሆኑ ያረጋግጥልናል። ይህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙላት የተገለጠው ፍቅር ኅልውናችንን የሚጠይቅ እያንዳንዱ ሕይወቱን በሙላት በግብር ለመተርጎም ምን ያክል ዝግጁ መሆኑ ከእያንዳንዱ በሕይወት ምን ማድረግ እንደሚሻ መልስ የሚጠባበቅም ነው። ወጣቶችን በጥንቃቄና በትጋት የሚሸኙ ብርቱ ቀናተኞች ካህናት” እንዳሉ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን አክልውም፣ “እነዚህ አባት ካህናት ጨለማ በሚጋረጥበት ሕይወት ለወጣቶች መንገድ እውነትና ሕይወት የሆነውን ክርስቶስ ለይተው ለሳማወቅ ድጋፍ ናቸው። ስለዚህ በዚህ ጥልቅ ያልሆነ ብልጭ ብሎ ለሚጠፋው መሠረት የለሽ ምርጫ በሚቀርብበት ዓለም የሚኖሩ ወጣቶች በእሴቶች የመማረክ የላቀው ፍጻሜ ላይ እንዲያተኩሩ የኢየሱስን ዱካ በመከተል ሌሎችን ለማገልገል የሚያብቃው ሥር ነቀል ለውጥ ለሚለው ምርጫ ይከተሉ ዘንድ አደራ” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.