2012-12-14 13:41:32

ብፁዕ አቡነ ራስፓንቲ፦ በትዊተር አማካኝነት ቅዱስ አባታችን በሁሉም ዓለም አደባባይ መገኘት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትዊተር ማኅበራዊ መረብ ሱታፌ ሁሉም ምእመናን ይህ በአሁኑ ወቅት ስምተኛ ክፍለ ዓለም ተብሎ የሚጥራው በሥነ ቀመር የተራቀቀው ዕደ ጥበብ በወንጌል ለማስበክ መጠራታቸው የሚያሳውቅ ነው። ስለዚህ አስፍሆተ ወንጌል በሁሉም መስክ የሚል መሆኑ በሲቺሊያ ክፍለ ሃገር በካታኒያ አውራጃ የአቺረአለ ወረዳ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ራስፓንቲ ከራዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ ኤማኑኤላ ካምፓነሊ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ መልልስ ገልጠው፣ እሳቸው የትዊተር ማኅበራዊ መረብ ተሳታፊ እንደሆኑና ዓላማውም አስፍሆተ ወንጌል በሁሉም መስክ የሚል ነው ብለዋል።
ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን መልስ ለመስጠት የዘገየች በተለይ ደግሞ አንዳንድ አንገብጋቢ ጥያቄዎች በተመለከተ ፈጣንና ችኩል መልስ ለመሻት ግፊት እጅግ ለተዳረገው ወቅታዊው ሰው ደመ ነፍሳዊ መልስ በመስጠት ምርጫ ሳትደባለቅ ካላት ኃላፊነት አንጻር የተስተነተነ ሥልጣናዊ መልስ ለመስጠት የተገባ በመሆኑ ይኽ ጥሪዋ ዘገምተኛ ሊያስመስላት ይችል ይሆናል የምትሰጠው መስል ግን ዘላቂነቱ የተረጋገጠ ማንም የማይለይ ነው። በመሆኑም ይኽንን ችኩል መልስ የሚሰጥበት የሚቸረቸርበት በሥነ ቀመር የተራቀቀው ስምተኛው ክፍለ ዓለም ተብሎ ለሚጠራው ዓለም አስፍሆተ ወንጌል በማቅረብ በትክክል ለዚህ ዓለም ያነጣጠረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሠረት ዘወትር በሁሉም ዘመን በተረጋገጠው የዕደ ጥበብ ምንጣቄ በመጠቀም ለሁሉም ቅርብ ሆናለች። የቅድሱ ጴጥሮስ ተከታይ ቅድስት መንበር የተለያዩ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት ብፅዓን ጳጳሳትና አቡናት ካህናት በዚሁ ዓለም በመገኘት አስፍሆተ ወንጌል እየፈጸሙ ናቸው። ስለዚህ ቤት ክርስቲያን የተለየች የተገለለች በኋላቀሩ ዓለም የምትራመድ እንዳልሆነች የሚመስክር ሁነት ብለዋል።
ቅድስት መንበር የሁሉም ዓለም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ድረ ገድ በተለይ ደግሞ የማኅበራዊ መረብ ድረ ገጾች አማካኝነት ቀድሞ የተዘጋጀ መልእክት ሳይሆን በቀጥታ ከሁሉም ጋር በመገናኘት ይኽ የዕደ ጥበብ ግኝት መሣሪያ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ ሥፍራ በመመልከት በዚያው በመገኘት አስፍሆተ ወንጌል መፈጸም ያለው አስፈላጊነት ትኵረት እንደሰጡበት ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.