2012-12-14 13:39:09

ቅዱስ አባታችን Twitter-ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ሱታፌ
ደ በርቶሊ፦ “ለማኅበራዊ ድረ ገጾች ትርጉም የሚያሰጥ ቆራጥ እርምጃ ነው”


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን Twitter-ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ @Pontifex በሚል መለያ በስምንት አበይት ቋንቋዎች የሚተረጎም ሱታፌ ባስጀመሩበት 24 ሰዓት ውስጥ ብቻ የተከታታዮቻቸው ብዛት ወደ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺሕ መድረሱ ሲገለጥ፣ ይኽ አቢይ ዓለም አቀፋዊ ሁነት ተብሎ የተገለጠው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትዊተር ከሁሉም ጋር ለመገናኘት የጀመሩት ሱታፌ የብዙዎች ፍላጎት ትኩረት ጉጉት መስህብ ሆኖ መገኘቱ ሲገለጥ ማንም በቸልተኛነት የሚመለከተው ጉዳይ እንዳልሆነ ያረጋገጠ ሁኔታ መሆኑ በኢጣሊያ ኮረረ ደላ ሰራ በመባል ለሚጠራው ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፈሩቾ ደ በርቶሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኝ አለሳንድሮ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ ይህ የቅድሱ አባታችን በትዊተር መገኘቱ ታሪካዊ ሁነት በማለት ሰይመውታል።
የቅዱስነታቸው እርምጃ በእውነቱ ብርቱ ለማህበራዊ ድረ ገጽ ተገቢ ትርጉሙ የሚያሰጥ ነው። እንደ ማንም ተራ ሰው ድረ ገጹ ሊያስከትለው የሚችለው የተለያየ ጠንቅ ያለ ቢሆንም ቅሉ በድረ ገጹ በመገኘት ለሚቀርብላቸው ጥያቄ መልስ በመስጠት የሚሳተፉበት ሲሆን፣ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በማቀራረብ የሚያራርቅ እየሆነ የመቀራረብና መራራቅ መሠረታዊ ትርጉም እያዳከመ ነው። ስለዚህ በዚህ መረባዊ ግኑንኘት አማካኝነት በሰዎች መካከል የሚጸናው ግኑኝነት መረባዊ ወይንም ሃሳባዊ ሲሆን፣ መቀራረብ ብቸኝነት ወይንም የተገለለ ተጨባጭ ሕይወት እውን እንዲሆን እያደረገ ነው ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሱታፌ ይኸንን አሉታዊ ገጽታውን የሚያርም ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር ተቀብለዉት ትምህርቱን ለመካፈልና ለመኖር የሚያዳምጡት ሌሎችም ጉጉታቸው ገፋፍቶአቸው በማዳመጥ ብቻ ሲሳተፉና ሌሎችም በማፌዝ ከርቀት ሲመለከቱት እንደነበር ከወንጌል እንደረዳለን። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን በዚህ ማኅበራዊ መረባዊ ግኑኝነት አማካኝነት ለሚሰጡት መልስ ወይንም ለሚያስተላልፉት አጭር ትኵርና ንቁ መልእክታቸው ተምሳሳይ ለኢስየሱስ እንደተሰጠው ግብረ መልስ እንደሚያጋጥመው አያጠራጥርም፣ ሆኖም የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ቀዋሚ መልእክቱን ሳይስት ዓለም በሚጠቀምበት የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በመቅረብ ከዕደ ጥበብ ምንጣቄ ጋር ማዛመድ ያለው አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ ውሳኔ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.