2012-12-14 13:48:04

Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ፦ ብፁዕ ካርዲናል ኦለት፣ “በአሜሪካ አዲስ ወንጌላዊ ልኡክነት ማነቃቃት”


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጀምሮ ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በቅድስት ማርያም ዘትራስፖንቲና ቤተ ክርስትያን የጳጳሳዊ ቤተ ክርስቲያን በላቲን አመሪካ ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካዲናል ማርክ ኦሌት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተጠናቀቀው በአመሪካ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገትና ዓለም አቀፍ የኮሎምቦስ ፍረሰኞች ማኅበር በጋራ ያዘጋጁት Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ መካሄዱ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ፣ የጉባኤ የመዝጊያ መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ኦለት ባሰሙት ስብከት ላቲን አመሪካ የዛሬ 500 ዓመት በፊት የተቀበለችው እምነት ዳግም ለማደስ የተካሄደ ጉባኤ መሆኑና ይኽ የ500 ዓመት እድሜ ያለው ስብከተ ወንጌል የሁለቱ አመሪካዎች ማለትም የሰሜንና የደቡብ አመሪካዎችን የሚያስተሳስር የጋራ ክርስትያናዊ ባህል ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።
ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት አክለውም ሁሉም ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለው የክፍለ አለሙ ዜጋ እምነት የማስፋፋት ኃላፊነት እንዳለው በማሳሰብ፣ አስፍሆተ ወንጌል የሁሉም ማኅበረ ክርስትያን ጥሪ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲገለጥ፣ እምነት ለአዲስ ትውልድ የማስተላለፉ ኃላፊነት የሁሉም ክርስቲያን ቤተ ሰብ ተልእኮ ነው ተልእኮ ሲባል ኃላፊነትንም ጭምር ያሰማል ካሉ በኋላ የጉባኤው መዝጊያ ቀን ዓመታዊ በዓል የላቲን አመሪካ ጠብቂ ቅድስት ማርያም ዘጓዳሉፐ የተከበረበት ቀን በመሆኑም ጉባኤ ያላው የተልእኮ ኃላፊነት የቅድስት ማርያም ጥበቃ የሚያሻው መሆኑ ያረጋግጥልናል እንዳሉ አስታውቀዋል።
ይህ Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 1997 ዓ.ም. ያጠናቀቁት “ከኅያው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ለመለወጥ ለሱታፌና ለትብብር ጎዳና ነው” በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ሲኖዶስ ዝክረ 15 ኛው ዓመት ባስቆጠረበት ወቅት ሲሆን፣ በ 1999 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ በሚል ርእስ ሥር የለገሡት የዚያ የተካሄደው የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ማእከል ያደረገ ጉባኤ እንደነበርም ብፁዕ ካርዲናል ኦሌት ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኦሊቪየር ቶዘሪ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምስልል አብራርተዋው፦ “በአሁኑ ወቅት ያእጹብ ድንቅ የሆነው የክርስትናው ባህል ሥነ ምግባርና ሃይማኖት ከማኅበራዊ ህይወት ከሥነ ትምህርት የሚያገል ማመን አለ ማመን ያው ነው የሚለው በመሰራጨት ላይ ባለው ባህል እንዲሁም በተለያዩ አዳዲስ የሃይማኖቶች ቡድኖች መስፋፋት ጭምር ለአደጋ ተጋልጦ የሚገኝ በመሆኑ ያክርስትያናዊ ባህል ዳግም በአዲስ መንፈስ በማነቃቃትና ኅያው ለማድረግ” በተሰኘ ዓላማ የተመራ ጉባኤ እንደነበርም ብፁዕነታቸው ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.