2012-12-12 13:48:38

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ሥልት ተጠቃሚ፣ አዳዲስ የዕደ ጥበብ መሳሪያዎች ለአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 Twitter-ትዊተር በመባል በሚጠራው በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ ድረ ገጽ አማካኝነት የግል ጦርማር @Pontifex በሚል አድራሻ መሠራቱ ቀደም ተብሎ የቅድስት መንበር መግልጫ አመልክቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ዛሬ የዕለተ ረቡዕ አስተምህሮ ትምህርተ ክርስቶስ ባቀረቡበት ቀን በይፋ አድራሻቸውን ያስተዋወቁም ሲሆን፣ ልክ እንደ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥራ አንደኛ የቫቲካን ረዲዮ ያስጀመሩበት ቤተ ክርስትያን አዲስ የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ ለአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ተጠቃሚ ትሆን ዘንድ ያነቃቁት መንፈስ የሚከተል የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍላጎት መሆኑ “La Civiltà Cattolica” ለተሰኘው በኢየሱሳውያን ማኅበር በ 1850 ዓ.ም. ቀዳሜ ኅትመቱን በማቅረብ የተመሠረተው በዚሁ ልኡካነ ወንጌል ማኅበር የሚተዳደረው በየአሥራ አምስት ቀን የሚታተመው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መጽሔት ዋና አስተዳዳሪ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውሰው፦ “ቅዱስ አባታችን በትዊተር መገኘት ተጋኖ የሌለው አወንታዊ ተግባር ነው፣ በተለይ ደግሞ መልእክት ለማስተላለፍ ልሙድ የሆነው የመገናኛ ብዙኃን መገልገያ መሣሪያ መጠቀም ለብቻው በቂ አለ መሆኑ የዕደ ጥበብ እድገት ያረጋግጠዋል። ስለዚህ አዳዲስ የማኅበራዊ ድረ ገጾች መጠቀም ጊዜው የሚያቀርበው መጠይቅ ነው። በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ይኸንን መጠይቅ በአወንታ በመመልከት ከሁሉም ጋር አለ ምንም የቦታና የጊዜ ገደብ በመገናኘት ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ጥሪያቸው የሚኖርበት አንዱ የመገልገያ መሣሪያ ነው” ብለዋል።
“በዚህ ሕዝብ እያንዳንዱ ሰው ሕይወቱ የሚቋደስበት ፍላጎቱን አስተያየቱን ግንዛቤው ጥያቄዎቹ እና መልሶች የሚገልጽበት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ቅዱስ አባታችን በመሳተፍ ወንጌላዊ መልስ ሕንጸት ይለግሳሉ፣ ምንም’ኳ ማኅበራዊ ድረ ገጽ ለገዛ እራሱ የቻል ጠንቅ ያለው ቢሆንም ቅሉ ይኸንን ግምት በመስጠት ይኸንን ጠንቅ በአስፍሆተ ወንጌል አማካኝነት በመቅረፍ ቃለ ወንጌል ማስፋፋት አስፈላጊ ነው። በርግጥ ጸረ ር.ሊ.ጳ. የሆኑ መልእክቶች ሊገኙባቸው እንደሚችሉ ቀድሞ ማወቅ አወንታዊ ነው። ብዙ ጥያቄዎች ለቅዱስነታቸው የሚቀርብበት በሳቸው የሚሰጠው መልስ የሚዘረዘርበት ለሁሉም ሙሉ ሕንጸት የሚበጅ ውሳኔ ነው” ብለዋል።
በትዊተር የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሳተፍ ሁሉም ካቶሊክ ምእመናን የሚያበረታታና በተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ሱታፌአቸው እንዴት መሆን እንደሚገባውና ዓላማውም ምን መሆኑ ወይንም ምን እንደሚመስል ፈር የሚያስዝ መሆኑ ያስረዱት አባ ስፓዳሮ አያይዘውም ካቶሊካዊነትህን በሁሉም ሥፍራ የሚል ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሕዝብ በሚገኝበት ሥፍራ ሁሉ በመገኘት ገዛ እራሳችውም በማሳተፍ የሚሰጡት አገልግሎት የሚደነቅ ነው። የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ድረ ገጽ መገኘት ቅድስት ቤተ ክርስቲያና ለሰብአዊ ያላት ቅርበት የሚያረጋግጥ ነው። መለያዋም ነው። ስለዚህ በዚህ ድረ ገጽ በኩል ሰብአዊ ማኅበራዊ የመሳሰሉት የተለያዩ ተጋርጦዎች በመለየት መልሱ ምን መሆኑ በአስፍሆተ ወንጌል ሥር በማመላከት አስተምህሮ የሚለግሱበት ምርጫ መሆኑ አስረድተው የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.