2012-12-10 15:11:28

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “አዲስ የአስፍሆተ ወንጌል መሣሪያ”


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ታህሳስ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የማኅበራዊ የመገናኛ ድረ ገጾች ውስጥ አንዱ በሆነው እርሱም Twitter-ትዊተር በመባል የሚታወቀው ድረ ገጽ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በይፋ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ የቅዱስ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትዊተር የማኅበራዊ የመገናኛ ድረ ገጽ የግል እጦማር አድራሻቸው @Pontifex በሚል ስም በይፋ መክፈቱ ላይ በማተኮር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ጥሪ መሠረት ከሁሉም ጋር አለ ምንም ገደብ ለመገናኘት የሚያስችላቸው መሆኑና ዓላማውም አስፍሆተ ወንጌል ነው ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. በትዊተር ምን ያደርጋሉ? ምን ያክል ተከታዮች ሊኖራቸውም ነው? የሚሉ ሰዎች አስተያየት እየሰጡበትም ነው። እንደ ማንኛው ኮከብ ታዋቂ ዜጋ የሚሳተፉበት አይደለም። ስለዚህ የቅዱስ አባታችን በትዊተር ለተከታዮች ብዛት ያነጣጠረ አይደለም። ስለዚህ ጆሮ ያለው ልብ ያለው ያዳምጥ የሚል፣ የተከታይ ብዛት የማይል ሱታፌ ነው። ሱታፌውም የሰው ልጅ የተጠማው የተራበው ቃልና አስተምህሮ የሚቀርብበት መሆኑ አስገንዘበዋል።
በዚህ 140 ቃላት መጠቀም ብቻ በሚለው የማኅብራዊ የግኑኝነት ድረ ገጽ አማካኝነት ከወንጌል መልእክቶች ጋር በርግጥ የሚስማማ ነው ለማለት ይቻላል፣ ምክንያቱም የወንጌል ቁጥሮች ከ 140 ቃላት በታች ናቸውና። ዓላማው የእግዚአብሔር ቃል መዝራት የሚል ነው፣ ቃሉ በተለያየ የመሬት ዓይነት ሊወድቅ ይችላል፣ ሆኖም የቤተ ክርስትያን ኃላፊነት ቃሉ ማስፋፋት ነው ብለዋል።
በትዊተር አድራሻቸው በኩል ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡበት፣ ከቤተ ክርስትያን ርቆ ለሚገኘው ቅርብ በመሆን ለማወያየትና ለመደገፍ የሚያግዝ አገልግሎት መሆኑ አብራርተዋል፣ ለአስፍሆተ ወንጌል መገልገያ መሣሪያ ነው በማለት ያቀረቡትን ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.