2012-12-10 14:32:55

የር.ሊ.ጳ የመልአከ ጉባኤ አስተምህሮ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ሥርዓተ አምልኮአችን በምጽአት ዘመን ለመሲሁ መምጣት ጐዳና የሚያዘጋጁ ሁለት ታላላቅ ሰዎች ማለት እመቤታችን ድንግል ማርያምንና መጥምቁ ዮሐንስን ልዩ በሆነ መንገድ ያቀርብልናል፣ በዛሬው ቃለ ወንጌል ቅዱስ ሉቃስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ከሌሎች ወንጌላውያን ለየት ባለ መንገድ ያቀርብልናል፣ ይህንን በሚመለከት የኢየሱስ ሕጻንነት በሚለው ሶስተኛው መጽሓፌ ገጽ 23 ላይ “አራቱም ወንጌላውያን በኢየሱስ ተል እኮ መክፈቻ መጥምቁ ዮሐንስን ያቀርቡልናል እንደ የኢየሱስ ፊተውራሪም ያቀርቡታል፣ ቅዱስ ሉቃስ ግን የኢየሱስና የመጥምቁ ዮሐንስ ማንነትና ተለእኮ መተሳሰርን ከመጸነስ ጀምሮ ግኑንነት እንዳላቸው ያመልክታል” ይላል፣ ይህ አቀራረብ የዮሐንስ ሁኔታን ለመረዳት ያግዛል፣ መጥምቁ ዮሐንስ የክህነት ዘር ካላቸው ቤተ ሰቦች ከዘካርያስና ከኤልሳቤጥ ይወለዳል፣ ዘካርያስ የነቢያት መጨረሻ ብቻ ሳይሆን የብሉይ ኪዳን ክህነትን ባጠቃላይ ያመለክታል፣ ስለዚህም ልጁ ዮሐንስ የሰው ልጆች ወደ መንፈሳዊው የአዲስ ኪዳን አምልኮ ያዘጋጃል፣ ይህ የአዲስ ኪዳን መንፈሳዊ አምልኮም በኢየሱስ እውን ሆነ፣ ወንጌላዊው ሉቃስ ሌሎች ወንጌላውያን ከሚያቀርቡት ምሳልያዊ አቀራረብ ባሻገር የዮሐንስ ሕይወትን ከታሪካዊ ፍጻሜዎች ሊያስተሳስረው እንዲህ ይላል “ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥ ጴንጤናዊው ጲላጦስም በይሁዳ ሲገዛ፥ ሄሮድስም በገሊላ የአራተኛው ክፍል ገዥ፥ ወንድሙ ፊልጶስም በኢጡርያስ በጥራኮኒዶስም አገር የአራተኛው ክፍል ገዥ፥ ሊሳኒዮስም በሳቢላኒስ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሆነው ሳሉ፥ ሐናና ቀያፋም ሊቃነ ካህናት ሳሉ” (3፡1-2) ይላል፣ በዚሁ ታሪካዊ ፍጻሜ መካከል ታላቁ ፍጻሜ ማለትም የኢየሱስ ልደትም ይቈራኛል፣ ይህንን ታሪካዊ ትሥስር ሌሎቹ አልጠቀሱትም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የታሪክ ትላላቅ ሰዎች ለትናንሾቹ የታሪክ ከለላ ይሆናሉ፣
መጥምቁ የሐንስ እንደ በበረሃ የሚጮህ ድምጽ ይገለጣል፣ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤” (ሉቃ 3፡4)፣ ድምጽ ቃልን ይሰብካል ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ የእግዚአብሔር ቃል በመጀመርያ ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ ስለመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይቀድማል (ሉቃ 3፡2 ተመልከት)፡ ስለዚህ ዮሐንስ መጥምቅ ታላቅ ተራ አለው ሆኖም ግን ሁሌ በክርስቶስ ሥራ ነው፣ ይህንን በተመለከተ ቅዱስ አጎስጢኖስ እንዲህ ይላል፣ “ዮሐንስ ድምጽ ነው፣ ስለጌታችን ግን በመጀመርያ ቃል ነበር (ዮሐ 1፡1) ይባላል፣ ዮሐንስ የሚያልፍ ድምጽ ነው ክርስቶስ ግን የሁሉ ምንጭ የሆነው ዘለዓለማዊው ቃል ነው፣ ከድምጽ ቃልን ከወሰዱ ምን ይቀራል፧ ይዘት የሌለው ባዶ ድምጽ ይቀራል፣ ቃል የሌለው ድምጽ ጆሮን ያንኳኳል ልብን ግን አያንጽም” ይላል፣ እኛ ዛሬ ማድረግ ያለብን አዳኝ የሆነው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን በልባችን ቦታ እንድናዘጅና እንድንቀበለው ይህንን ድምጽ መስማት አለብን፣ በዚሁ የምጽአት ዘመን በቤተ ልሔሙ ዝቅተኛ ግርግም በእምነት ዓይነኖቻችን የእግዚአብሔር መዳንን ለማየት እንድንችል ዘንድ እንዘጋጅ፣ ባለነው ኅብረተሰብ በማተርያላዊ ነገሮች ደስታን ለማግኘት በምንፈተንበት ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ መሠረታዊ በሆነ መንገድ እንድንኖር ይጠራናል፣ የልደት በዓል በውጫዊ መብለጭ የሚከበር አይደለም ነገር ግን ለሰው ልጆች ሰላም ሕይወትና እውነተኛ ደስታን ለመስጠት የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ በዓል መሆን አለበት፣ አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ በመሆን የሚመጣውን ጌታ በልባችንና በመላው ሕይወታችን እንድንቀበለው ዝግጁዎች እንድኖኢሆን ዘንድ የዝመነ ምጽ አት ድንግል የሆነችው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እናታዊ አማላጅነት አይለየን ብለው ካስተማሩ በኋላ ጸሎተ መል አከ እግዚአብሔር ከም እመናን ጋር ደግመው በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታና ምስጋና በማቅረብ ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.