2012-12-10 15:14:03

ብራዚል፦ ኮምቦናውያን ልኡካን ማኅበር ከድኾች ጎን


RealAudioMP3 በአሁኑ ወቅት በራዚል በብልጽግና ከሚገኙትና የኤኮኖሚ እድገት ከሚታይባቸው አገሮች ውስጥ በቀደምት የምትጠቀስ አገር ስትሆን፣ ሆኖም በአገሪቱ ያለው ማኅብራዊ ልዩነት እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር፣ በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙት የአገሪቱ ዜጋ አሁንም በከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ነው። ስለዚህ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ የኮምቦኒ ልኡካነ ወንጌል አባላት አቢይ ሐዋርያዊ የሰብአዊ ሕንጸት አገልግሎት በማቅረብ ድኽነት ለመቀረፍና ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ የሚሰጡት አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑ ይነገራል።
በዚህ ተልእኮ አያገለገሉ የሚገኙት የኮምቢኒ ማኅበር አባል አባ ሳቨሪዮ ፓውሊሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ድኽነት ለወንጀል ቡድኖች ለም መሬት ነው። ድኽነት ጸረ የሰብአዊ መብትና ክብርም ነው። ስለዚህ ድኽነትን መዋጋት ከዚህ ጋር በተቆራኘ መልኩ የተለያዩ ጸረ ስብአዊ ችግሮችን መዋጋትና ማጥፋት ማለት ነው። ድኽነት ለመዋጋት ዓላማ የሚሰጠው አገልግሎት በመሆኑም በተያያዘ መልኩ የተለያዩ እክሎች ሲያጋጥሙ ይታያል። የኮምቦኒ ማኅበር አባላት በዚህ የጸረ ድኽነት አገልግሎት መስክ ለየት ባለ መልኩ ወጣቱን በቀላሉ ለወንጅለ ቡድኖች የመስህብ ምክንያት የሆነው ወጣቱ የኅብረሰብ ክፍል ከዚህ አደጋ ለማዳን የሚሰጡት የሕንጸት አገልግሎት ሰፊና ጥልቅ ነው ብለዋል።
እ.ኤ.አ. በ 1977 ዓ.ም. በሳን ፓውሎ ሊቀ ጳጳሳት ረዳት ብፁዕ አቡነ ሉቻኖ መንደዝ አማካኝነት ለየት ባለ መልኩ ከ18 ዓመት እድሜ በታች ለሆኑት ወጣቶች የሚከታተል ልዩ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ድርገት በማቋቋም ከዚህ የኅብረሰብ ክፍል ጋር ቀርቦ በመገናኘት መንፈሳዊ ሰብአዊ ሕንጸት በማቅረብ ከወዲሁ በማነጽ የአመጽ መሣሪያ እንዳይሆን በተለያየ ችግር ምክንያት ለተለያየ አደጋ ተጋልጦ የሚገኝና በተለያየ ወንጀል ምክንያት በወህኒ ቤት የሚገኘውንም ለተለያዩ አደንዛዥ እጸዋት የተጋለጠውን ሁሉ በማነጽ ከወደቀበት ችግር ለማላቀቅ በሐዋርያዊ አገልግሎት ዘርፍ የሰብአዊ ተሃድሶና ሕንጸት በመስጠት በዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት ጭምር ወጣቱ ትውልድ ተሳታፊ ማድረግ እየቀጠለ መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.