2012-12-07 14:39:26

የሰላም ጥሪ በመካከለኛው ምስራቅ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን


RealAudioMP3 በሊባኖስ ሃሪሳ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ፓትሪያርኮችና ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ትላትና መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ በጉባኤው ፍጻሜ በወጣው የጋራ መግለጫ ሰነድ፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ፣ በአረብ አገሮች ክልል ያለው አንገብጋቢ ማኅበራዊ ፖለቲካውና ሰብአዊ ጉዳዮችን በመለየት ለመፍታት ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ በማኖርና የመላ መካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍጻሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምስራቅ የተሰየመው በሊባኖስ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ፈጽመው በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የለገሡት የድኅረ ሲንዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በግልና በማኅብራዊ ሕይወት እግብር ላይ ለማዋል ምን መደረግ እንደሚገባ መርህ ያኖረ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።
የመላ መካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ ደግሞ የፍልስጥኤም ጥያቄ የመካከለኛው ምስራቅ አለ መረጋጋት ምክንያት መሆኑ ለይተው በማብራራት፣ ተገቢና ሰላማዊ ምላሽ እንዲያገኝ በማድረጉ ጥረት እንዲበራታ ጥሪ በማቅረብ ፍትሃዊ መፍትሔ ለዘላቂ ሰላም በመካከለኛው ምስራቅ መሠረት ነው እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አያይዞ፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ በሶሪያ ያለው አሳሳቢው ሁኔታ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ የሁሉም መንግሥታት የተለያዩ ሃይማኖት ማኅበርሰብ ጥረት የሚያሻው መሆኑ በማሳሰብም፣ በአረብ አገሮች የሚገኙት የውሁዳን ማኅበረ ክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ በመዳሰስ የሁሉም የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ወሳኝ መሆኑና የምስልምና እምነት ተከታዮች የወንድሞቻቸው የክርስያን ማኅበርሰብ አባላት ሰብአዊ መብት እንዲከበር ድምጻቸው እንዲያሰሙ ጥሪ በማቅረብ፣ በመጨረሻም የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው የአንጽዮኪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንና የመላ መካከለኛው ምስራቅ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኢግናዚዩስ አራተኛ ሓዚም በ 91 ዓመት ዕድሚያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት የሰማቸው ኃዘን ይፋ በማድረግ እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸውና ለመላ መካከለኛው ምስራቅ ኦርቶዶሳዊት ቤተ ክርስትያን መጽናናት ከእግዚአብሔር መማጠናቸው አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.