2012-12-07 14:33:45

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የበዓለ ልደት ጥድ ከእግዚአብሔር ለሚመጣው ሕይወትና ሰላም ምልክት ነው


RealAudioMP3 በየዓመቱ ከተለያዩ አገሮች ለበዓለ ልደት ዘእግዚእነ ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚቆመው የበዓለ ልደት ምልክት ትልቅ ጥድ ዘንድሮ ከኢጣሊያ ከኢሰርኒያ አውራጃ ከሞሊሰ ክፍለ ሃገር የተለገሠ መሆኑ ሲገለጥ፣ ትላትና ይኽ 24 ሜትር ርዝመት ያለው ጥድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንዲቆም መደረጉ የገለጡት የቫቲካንር ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጀ ቸንቶፋንት አያይዘውም፣ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. የበዓለ ልደት መግለጫ ግርግም በይፋ እንደሚከፈት አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የልደት ጥድ የለገሱት የሞሊሰ ማኅበርሰብ ልኡካን እ.ኤ.አ. ጧት ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተቀብለው መሪ ቃል እንደሚለግሡ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፉት ዓመታት የበዓለ ልደት ምልክት ጥድ ርእስ በማድረግ ጥዱን የለገሱት ማኅበርሰብ አባላት ተቀብለው የሰጡት አስተምህሮ መለስ ብለው በመዳሰስ፣ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የቫል ዳ ቢያ ልኡካንን ተቀብለው ባሰሙት ቃል፦ “የበዓለ ልደት ጥድና እንዲሁም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መግለጫ ግርግም ምስል የክርስትያን ማኅበርሰብ የበዓለ ልደት መግለጫ የሚጠቀምበት የጥልቅ መንፈሳዊነት ክርስትያናዊ ባህል ምልክት ነው። ይህ መንፈሳዊ ባህል በአሁኑ ወቅት በዓለ ልደት የገጸ በረከት መለዋወጫ ብቻ የሚያደርገው በመስፋፋት ላይ ያለው የፍጆታና የጉዕዝነት ባህል አማካኝነት እንዳይታፈን አቅቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት ነው” እንዳሉ አስታውሰዋል።
እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በተመሳሳይ በዓል ምክንያት የበዓለ ልደት መግለጫ ጥድ የለገሰው በኢጣሊያ የደቡባዊ ቲሮሎ ከተማ ነዋሪዎች ማኅበር ልኡካንን ተቀብለው በለገሱት መሪ ቃል፦ “የበዓለ ልደት መግለጫ ጥድ የበዓለ ልደት መግለጫ ለሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርግም መወለድ ላለው ጥልቅ መንፈሳዊ ክብር የሚያደምቅ ምልክት ነው። የወንድማማችነት የአንድነት የሰላም ምልክት ነው። ፍቅሩን ለሚገልጥልን ሰው ሆኖ ለሚመጣው እግዚአብሔር የልባችን በር እንድንከፍትለት ለፍቅሩ ፍቅራዊ መልስ እንድንሰጥ የሚያነቃቃ መንፈሳዊነት የሚገለጥበት ሁነት ነው” ማለታቸውም የጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ዘገባ ይጠቁማል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘንድሮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የሚቀመጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መግለጫ ግርግም ከኢጣሊያ የባሲሊካታ ክፍለ ሃገር የተለገሰ በሐውልት ቅረጻ ቅርጽና የንድፍና ቅብ ባለ ሙያ መምህር ፍራንቸስኮ አርተሰ የተሰራ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.