2012-12-05 14:13:40

Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ፦ ብፁዕ ካርዲናል ኦለት፣ “አለ እውነተኛ አንድነት ለወንጌላዊ ልኡክነት ኃይል አይኖርም”


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከፊታችን እሁድ ታህሳስ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ቤተ ክርስትያን በአመሪካ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገትና ዓለም አቀፍ የኮሎምቦስ ፍረሰኞች ማኅበር በጋራ ያዘጋጁት Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ እንደሚካሄድ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ Internazionale Congresso Ecclesia in America - ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በአመሪካ የሚያካሄደው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ በማስመልከት በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንጻ ባለው የጉባኤ አዳራሽ የቤተ ክርስትያን በአመሪካ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ይህ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 1997 ዓ.ም. ያጠናቀቁት “ከኅያው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ለመለወጥ ለሱታፌና ለትብብር ጎዳና ነው” በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው ሲኖዶስ ዝክረ 15 ኛው ዓመት ባስቆጠረበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ጠቅሰው፣ ልክ በ 1999 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤተ ክርስትያን በአመሪካ በሚል ርእስ ሥር የለገሡት የዚያ የተካሄደው የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ማእከል በማድረግ የሚካሄድ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ነው እንዳሉ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶታ አስታወቁ።
“በአሁኑ ወቅት ያእጹብ ድንቅ የሆነው የክርስትናው ባህል ሥነ ምግባርና ሃይማኖት ከማኅበራዊ ህይወት ከሥነ ትምህርት የሚያገል ማመን አለ ማመን ያው ነው የሚለው በመሰራጨት ላይ ባለው ባህል እንዲሁም በተለያዩ አዳዲስ የሃሰት ሃይማኖቶች መስፋፋት ጭምር ለአደጋ ተጋልጦ የሚገኝ በመሆኑ ያክርስትያናዊ ባህል ዳግም በአዲስ መንፈስ ማነቃቃትና ኅያው ለማድረግ” በተሰኘ ዓላማ የሚመራ ጉባኤ መሆኑ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ ይኽ ደግሞ በላቲን አመሪካና በካሪቢያን የሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው የሱታፌና የትብብር ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ማብራራታቸው ጂሶቲ ጠቅሰው፣ “ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ውስጥ የተከሰቱት ተጋርጦዎችና ችግሮች እርሱም ስደተኞች፣ የአደንዛዥ እጸዋት የማዘዋወሩ ጸረ ሰብአዊ ተግባር፣ የአደንዛዥ እጸዋት ሱሰኝነት በተለይ ደግሞ በወጣቱ ትውልድ ዘንድ እየተስፋፋ ያለው ልምድ፣ ይኸንን ችግር ለመቀረፍ የሚወጠኑት የፖለቲካ ሥልቶች የቤተሰብ ወቅታዊ ሁኔታ የካቶሊክ ሥነ ትምህርት፣ ድኽነት ተመጽዋችነት የሃይማኖት ነጻነት የመሳሰሉትን አንገብጋቢ ችግሮች በማጤን መፍትሄ የሚያስተጋባ፣ በላቲን አመሪካ በሰሜን አመሪካና በካናዳ መካከል የሚጸናው ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና ባህላዊ ግንኙነት መግባባት መከባበር መተባበርና ፍትህ ላይ የጸና እንዲሆን የሚያነቃቃ ጉባኤ ነው” እንዳሉ አመልክተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ በላቲን አመሪካ በሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስትያን መካከል ወንድማማችነት በማረጋገጥ የክፍለ ዓለሙን ችግር በጋራ ለመቅረፍ ማበረታታት ብሎም ምእመናን የቤተ ክርስትያን ኅያው አባላት መሆናቸው እንዲገነዘቡ ለመደገፍ ምን መደረግ እንዳለበት መንገድ የሚቀይስ ጉባኤ ነው። በዓለም ካለው የካቶሊክ ምእመናን ብዛት ውስጥ 50 በመቶ በላቲን አመሪካ በሚገኘው ካቶሊክ ምእመን የሚሸፈን መሆኑ” ገልጠው፦ “አለ እውነተኛና ጽኑ አንድነት በምንም ተአምር ጠንካራ አስፍሆተ ወንጌል በቤተ ክርስትያንና በተልእኮ ወንጌል ንቁ ተወናያንነት ብሎም ማኅበራዊነት ለማረጋገጥ የማይቻል ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጁሴቲ አያይዘውም በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመላ አመሪካ የሮማዊት ቤተ ክርስትያን አበይት ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናላትና ብፁዓን ጳጳሳት፣ የተለያዩ የካህናትና የደናግል ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች፣ በሮማ የሚገኙት የተለያዩ ጳጳሳዊ የዘርአ ክህነት ተቋሞች የተወጣጡ በጠቅላላ 200 ተጋባእያን በማሳተፍ ዓመታዊ የቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ጓዳሉፔ በዓል በሚከበርበት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 6 ሰዓት ተኩል በቅዱስት ማርያም ዘ ትራስፖንቲና ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት በማድረግ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.