2012-12-03 15:11:25

ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ጉዳይ ምክር ቤት ይፋዊ ጉባኤ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሁሉም ጥቅም ላይ ያተኮረ “ዓለም አቀፋዊ የፖከቲካ ሥልጣን” ያለው አስፈላጊነት መሠረት የሰጡት መሪ ቃል መርህ በማድረግ “ዓለም አቀፋዊ የፖከቲካ ሥልጣን” ርእሰ ጉዳይ ያተኮረ ጳጳሳዊ የፍትህና የሰላም ምክር ቤት ያነቃቃው ይፋዊ ጉባኤ በማስመልከት የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ኮድዎ አፒያህ ቱርክሶን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ሥልጣን የሚለው አስተሳሰብ ሊጨበጥ የማይቻል ሃሳብ ብቻ አድርገው የሚመለከቱት ብዙ ናቸው። ቤተ ክርስትያን ግን ዓለም አቀፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኽንን ሥልጣን የሚኖር ድርጅት እንዲሆን በትክክል ለዚህ አገልግሎት የሚያበቃው ኅዳሴ ያስፈልገዋል ብላ እንደምታምን ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ዓለማዊ ትሥሥር በሁሉም መስኩ እየተረጋገጠ ነው። የተለያዩ አገሮችና መንግሥታት ለብቻቸው እንዳሻቸው ሊመለከትዋቸውና ምላሽ ሊሰጡባቸው የሚገባቸውና የሚቻላቸውም ጉዳዮች እንዳሉ ብፁዕነታቸው ሲገለጡ፣ ለምሳሌ ሰላም የተፈጥሮ እንክብካቤ የተፈጥሮ የአየር ንብርት ጥበቃ የመሳሰሉት አበይትና አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ጠቅሰው፣ የተባበሩት መንግሥታት እነዚህን አንገብጋቢ ጥያቄዎች የምላሽ ውሳኔ ለመስጠት ጥረት ቢያደረግም ውሳኔው በተለያዩ አገሮች ሲከበር አይታይም። ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ሥልጣን መዋቅር ሲባል ለማኅበራዊ ጥቅም መረጋገጥ ላይ ያተኮረ ፖለቲካ የሚከተል ሆኖ በአገሮች ሉአላዊነት ላይ ጫና ሳይሆን እያንዳንዱ አገር ለማህበራዊ ጥቅም ላይ በማተኮር በዚህ አማካኝነት የአገሮች ሉአላዊነት ለጋር ጥቅም መረጋገጥ ላይ የጸና መሆን እንዳለበት የሚያሳስብ፣ ለዚህ ዓላማ መረጋገጥ አገሮችን የሚደግፍ ማለት ሲሆን፣ ለማኅበራዊ ጥቅም መረጋገጥ አህጉራት አንዳንድ ዓለም አቀፍ ነክ የሆኑት ጉዳዮች በዚህ መዋቅር ሥር ምላሽ እንዲያገኝ የሉአላዊነት ክፍለ ሥልጣናቸውን ለዚህ መዋቅራዊ የጋራ ጥቅም ማስረክብ የሚጠይቅ ውሳኔ ነው። ሰለዚህ ይኽ መዋቅር እንዲረጋገጥ የሁሉም አገሮች ፍላጎት እንጂ ጫና ሆኖ የሚቀርብ መዋቅር መሆን የለበትም፣ የእያናንዱ አገር ነጻ ምርጫ የሚያሻው ውሳኔ መሆኑ እንዳለበት አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.