2012-12-03 15:21:08

ናይጀሪያ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ናይጀሪያ ከካሜሩን ጋር በሚያዋስትናት ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ሶስት አቢያተ ክርስትያን በእሳት መጋየታቸው ሲገለጥ፣ የአይን ምስክሮች እንደሚሉትም ከሆነው ከ 40 በላይ የሚገመቱ መሣሪያ የታጠቁ ግለ ሰቦች በሰነዘሩት ጥቃት ሳቢያ የደረሰ አደጋ መሆኑም ሲታወቅ፣ ሆኖም የሞትና የመቁሰል አደጋ ማስከተሉም ብወኑ ባይታወቅም፣ የአደጋው ተጠያቂ ገዛ እራሱ ቦኮ ሃራም በማለት የሚጠራው በአገሪቱ የሚንቀሳቀሰው የምስልምና ሃይማኖት አክራያን የአሸባሪያን ኃይሎች መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. ህዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በካዱና በሚገኘው በአንድ የፕሮተስታንት ቤተ ርክስትያን የጦር መሣሪያ የታጠቁ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት ሳቢያ 17 ሰዎች ለሞት መዳርጋቸው ይታወሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.