2012-12-03 15:08:08

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስትያን በዚህ ምድር እንደ ማንኛውም ሰው ተጓዥ ነች


RealAudioMP3 ቅዳሜ ጧት ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አዘጋጅነት አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ከያንያንና ተጓዥ ከያንያን በጠቅላላ ከሰባት ሺሕ በላይ የሚገመቱ ከያንያን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
ከያንያኑን በቅዱስ አባታችን ፊት ንግግር በማሰማት በማቅረብ ያስተዋወቁት የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ መሆናቸው የገለጡት ጋዜጠኛ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለውም፣ አንዳንድ ከያንያን የእምነት መስክርነት አሰምተዋል።
ከያንያን በተለያየ መልኩ በሰው ልጅ ውስጥ ላለው የስነ ጥበብ ዝንባሌ የሚያረኩ የአስተናጋጅነትና የግልጽነት ባህርይ የሚያንጸባርቁ፣ እውነት የመሻቱ በሰው ልጅ ዘንድ በኑባሬ ያለው ዝንባሌ የሚያነቃቁ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባሰሙት ንግግር አብራርተው፣ ከያንያን በማኅብራዊ በባህላዊ ዘርፍ የሚሰጡት አቢይ አስተዋጽኦ ትኵረት እንዲደረግበት በማሳሰብም፣ በሁሉም ሥፍራ የከያንያን ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲጠበቅ ለመንግሥታትና ለክልሎች መሥተዳድር አባላት አደራ ብለዋል።
በመጨረሻም ከያንያን በሚሄዱበት ሥፍራ ሁሉ ተገቢ መስተንግዶ እንዲያገኙና ቤተ ክርስትያን የከያንያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነትም በእምነታቸው በማበረታታት መንፈሳዊ እንክብካቤ በማቅረቡ ረገድ የምትሰጠው አገልግሎት ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ሁሉም እንደየ ሙያውና ጥሪው መሠረት በቤተ ክርስትያን የተገባ ሥፍራ አለው እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቱ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.