2012-12-03 15:25:24

ሶማሊያ


RealAudioMP3 በጋልጋዱድ የሶማሊያ ማእከላዊ ክልል በተለያዩ የአገሩቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ 26 ሰዎች ለሞት ሌሎች 18 ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ሲነገር፣ የአገሪቱ የጸጥታ ኃይል ካሰራጨው ዜና ለመረዳት እንደተቻለውም የግጭቱ መነሾ የግጦሽ መሬትና እንዲሁም ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ያለበት ክልል ለመቆጣጠር የሚል መሆኑ ሲታወቅ፣ ሶማሊያ ከ 1991 ዓ.ም. የሲያድ ባሬ መንግሥት ከስልጣን መውረድ በኋላ የተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመንግሥት ሳይሆን በጎሳዎች ቁጥጥር ሥር የሚተዳደሩ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ አዲሱ የአገሪቱ የውስጥና ብሔራዊ የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ ሚኒ. ሑሰይን ጉለድ አብዲልካሪም በጎሳዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውም ተገልጠዋል።
በአገሪቱ ሰላም ለማረጋገጥና የአገሪቱ መንግሥት ሙሉ በሙሉ አገሪቱ ለመቆጣጠር ያለበት ችግር ለመቅረፍ ድጋፍ ለማቅረብ፣ የአገሪቱ ጸጥታና ደህንነት ለማረጋገጥ ከ 17 ሺሕ በላይ የሚገመቱት የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በሶማሊያ የአልቃይዳ የቀኝ እጅ ተብሎ የሚንገርለትን አል ሽባብ የአመጽያን ኃይል ለማጥፋት ተሰማርተው እያገለገሉ መሆናቸውም የሚታወቅ ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.