2012-12-01 16:51:14

ድህነት ለምን ፣ ር ሊ ጳ በነዲክት ድህነትን ትኩረት ሰጥተው
ያደረጉት ንግግር እንመልከት ፡


ድኽነት ለምን ፣ በወንድማማችነት እና ትባት በማዘውተር እንዲሁም የሕይወት እና የእድገት ዘይቤ መቀየር የመሳሰሉት ዘዴዎች በመጠቀም የዓለም ህዝቦች በማሰቃየት ያለውን ድኽነት ለመግታት መሞከር እና መቻል የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ቃል ነው ፡ ክቡራት እና ክቡራን አድማጮች ይህ የቫቲካን ራድዮነው
ነገ ወርሀ ሕዳር 29 ቀን እኤአ የኤውሮጳ ሕብረት የራድዮ ስርጭት በኤውሮጳ አቀፍ ደረጃ ድህት ለምን በተሰኘ ርእስ የራድዮ ስርጭት እንደሚያከናውን ይታወቃል።በነገ ዕለት የኤውሮጳ ሕብረት የራድዮ ስርጭት ድህነት ለምን በተሰየመ ርእስ የሚያካሄደው ፕሮግራም ድህነትን ለመግታት ሰላማዊ የለውጥ እንቅሳቃሴ እንዲከሰት በማሰብ እንደሆነ ተመልክተዋል።
ስስት እና ፀብ ርእሰ ኀያላን በሆኑባት በዚች ዓለማችን በዓለም ዙርያ የሚገኙ ክርስትያኖች ለፍትሕ እንዲቆሙ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ አሳስበዋል።በማያያዝም በተለይ ክርስትያኖች የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች እንዲከበሩ የመመስከር ግዴታ እንዳላቸውም አመለክተዋል።
በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት አመለካከት የድህነት ዋነኛ ጠንቆች በዓለም ዙርያ የሰፈነው ራስ ወዳድነት የፋይናንስ ግምታዊ አስራር ናቸው ።የአኗኗር ዘዴ ካልተቀየረ እና ሰብአዊ መፈቃቀድ ፈጽሞ ከጠፋ የሰው ልጅ መነሻው እና መድረሻው ለማወቅ ከተደናበረ ሁኔታው ይሻሻላል ለማለት እንደማይስደፍርም ቅድስነታቸው ገልጠዋል።
የዓለም ሀብት በጥቂት ሰዎች ጅሆ ከተያዘ እና በሚልያርድ የሚቆጠር ህዝብ የሚላስ የሚቀመስ ካጣ አስጊ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችልም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ማስጠንቀቃቸው ተመልክተዋል።
ፍትሕ አልባነት የችግሮች ሁሉ መንስኤ ሰለሆነ ፍትህ ለማስፈን ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች ሁሉ ለፍትሕ እንዲቆሙም ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።
ባህላዊ ሞራላዊ እና ሥነ ሕይወታዊ ቀውሶች መከሰታቸው በማመን ቀውሶችን መፈወስ እንደሚጠበቅብንም በነዲክት 16ኛ አስታውቀዋል።
ለዓለም ህዝቦች የሚበቃ ምግብ መኖሩ በየኤኮኖሚ ጠበብቶች እየተመሰከረ በርሃብ የሚሰቃዩ እና የሚሞቱ ህዝቦች መኖራቸው የሚያሳዝን እና የሚያሳስብ ጉዳይ መሆኑም በማያዝዝ ገልጠዋል።
የእርሻ መስኮች በዓለም አቀፍ ደረጃ በማልማት ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም አመልክተዋል። ኃላ ቀርነት የሚከሰተው የዓልም ህዝቦች ርስ በርሳቸው መተባበር እና መረዳዳት ሳይችሉ ሲቀሩ መሆኑ ያመለከቱ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት
ግሎባላይዘሽን ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጥምረት የዓለም ህዝቦች ያቀራርባቸዋል እንጂ ወንድማሞች እንደማይደርጋቸው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ገልጠዋል።ኃላ ቀር ሀገራት እና በመደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን የዕዳ ጫና ራሱ ከባድ እና በእነሱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚንሰራፋ ብሰርዝላቸው የተሻለ መሆኑም በማያያዝ አስገንዝበዋል ።
በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት የዓለም አቀፉ ገበያ ተሳታፊ እንዲሆኑ የምዕራቡ ዓለም የተክኖሎጂ እና ሳያንስ እውቀት ተቃሚ እንዲሆኑ መድረግ እንደሚያስፈልግ በነዲክት 16ኛ ገልጠዋል።
በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት በጤና ጥበቃ በኩል ከአዳጊ ሀገራት ጋር እንዲተባበሩ የጠየቁ ቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ለታዳጊ ሀገራት የጦር መሳርያ ከመሸጥ እና ማቀበል እንዲቆጠቡ ተማጽንመዋል።
ሰብአውነት ተስፋ ያስፈልገዋል እውነተኛ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑም በማያያዝ ገልጠዋል። የእግዚአብሔር ፍቅር ዓለምን ይለወጣል እውነተኛ ተስፋም ይሰጣል እውነተኛ ተስፋው ዘላቂ ተስፋ ነው በነዲክት 16ኛ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.