2012-12-01 16:25:30

ር ሊ ጳ በነዲክት ቀሳፊ በሽታ ኤይድስ እንዲገታ ተማጽነዋል ፡


ታሕሳስ አንድ ቀን እኤአ በዓለም ደረጃ የሚካሄደው ጸረ ኤይድስ ትግል የሚካሄደው የትግል ቀን ታስብቦ ይውላል ። ቀሳፊ በሽታው በዓለም ዙርያ በተለይ በአዳጊ ሀገራት በሚልዮን የሚቁጠር ህዝብ ቀጥፈዋል እያሳቃየ እንደሚገኝም ተመልክተዋል።
ከትናትና ወድያ ሮቡዕ ዘወትር እንደሚሆነው ሁሉ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በጳውሎስ አዳራሽ ለምእመናን ትምህርተ ክርስቶስ በሰጡበት ግዜ ስለዚሁ ቀሳፊ እና ምሕረት የለሽ በሽታ መናገራቸው የማይዘነጋ ነው ።
በነዲክት አስራ ስድስተኛ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሕመሙ ለመጋታት ግምባር ቀደም በመሆን እንድትሰራ በእጽንኦት ከመጠየቃቸው ባሻገር በዓለም ዙርያ ሕመሙ ለመግታት ከሚሰሩ እና ሕሙማኑ ከሚንከባከቡ ተቋሞች ሃያ አምስት በመቶ የቤተክርትያን ተቋሞች መሆናቸው ገልጠዋል።
በቅድስት መንበር የጠና ጠበቃ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተቋቋመው ደጉ ሳምራዊ የተባለ የጤና ጥበቃ ቡድን ኤች አይ ቪ ኤይድስ ሕመም ለመግታት ያለሰለሰ ጥረት እያካሄደ መሆኑ ተዘግበዋል።
ይህ የደጉ ሳምራዊ የጤና ተንከባካቢ ቡድኑ በቃሳፊ ሕመሙ ለሚሰቃዩ ህዝቦች የተለያዩ መድኀኒቶች በማድረስ እንደሚገኝ ይታወቃል።
የጤና ተንከባካቢ ካቶሊካዊ ተቋሙ ለአስር የአፍሪቃ ሀገራት እነሱ ለአንጎላ ቡርኪና ፋሶ ካመሩን ኮንጎ ብራዛቪል ኮንጎ ረፓብሊክ ኒገር ሴራልዮን ሶማልያ ደቡብ ሱዳን እና ዚምባብወ የኤች አይ ቪ ኤይድስ መድኀኒቶች እያቀበለ መሆኑ ተነግረዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ሕመሙ በአዳጊ ሀገራት በተለይ ብሕጻናት እና እናቶች እያደረሰው ያለውን ሞት እና ስቃይ አስታውሰው ምዕራቡ ዓለም ለዚሁ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ቀሳፊ በሽታው ለመግታት እንዲተባበር አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።
በኢንዱስትሪ አድገዋል በተባሉ የምዕራም ሀገራት በኤች አይ ቪ ኤይድስ የታመሙ ሰዎች ሕመሙ የሚያስታግስ ወይም ደግሞ የሚገታ መድኀኒት ሲያገኙ የድሃ ሀገራት በሽተኞች መድኃኒቱ ውድ ሰለሆነ ለመፈወስ ባለመቻላቸው የሚያሳዝን እንደሆነ ቅድስነታቸው አመልክተዋል።
አያይዘው በዚሁ ምሕረት የለሽ የታመሙ እናቶች ለልጆቻቸው ሕመሙ እንዳያስተላልፉላቸው የሚገታ መድኀኒ በማጣታቸው ሕመሙ ሕጻናትን እያሰቃየ እንደሆን ገልጠዋል።ዓለም አቀፍ ማሕበረ ሰብ ሕመሙ ለመግታት ከአዳጊ ሀገራት በመተባበር እና አዳጊዎቹ የምዕራቡ የሳይንስ እና ተክኖሎጂ ተቋዳሽ በማድረግ ጥረት እንዲድረግም ቅድስነታቸው ተነግረዋል።ቅድስት ካትሊካዊት ቤተ ክረትያን የኤች አይ ቪ ኤይድስ ብቸኛ መድኀኒት በቃል ኪዳን መጽናት እና ሞራል የተከናነበ ሐላፊነት ያለው ሕይወት መምራት እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.