2012-11-30 14:11:05

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፦ ስደተኞች በኤውሮጳ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሃብት


RealAudioMP3 ስደት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ያለ የሚኖር ማኅበራዊ ክስተት መሆኑ ትላትና በተጠናቀቀው የመላ ኤውሮጳ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ድርገቶች ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በማስታወስ ስደተኞች ለአስፍሆተ ወንጌል ሃብት ናቸው እንዳሉ ጉባኤውን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ሰዓት ጀምሮ ስደትን የሚያውቅ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ አሁንም በምንኖርበት ዓለም የሰውን ልጅ ለስደት ለመፈናቅል አደጋ የተጋለጠ መሆኑ ካብራሩ በኋላ ስደት የሚደጋገም የማህበራዊ ክስተት ታሪክ ነው። ይስደድ የነበረው ሕዝብ ዛሬ የስደተኛ አስተናግጅ ሆኖ ይገኛል። ስደተኛን የማስተናገዱ ጥሪ የሁሉም ኃላፊነት ነው እንዳሉ የገለጡት ሮበርታ ጂሶቲ አክለውም፣ ከተለያዩ አገሮች ካቶሊካውያን ምእመናን ወደ ኤውሮጳ መሰደዳቸውና በኤውሮጳ በካናዳ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የእነዚህ ስደተኞች መኖር ለቤተ ክርስትያን ለማኅበረ ክርስትያን ጭምር አቢይ ድጋፍ ሆነዋል። ስለዚህ ስደተኛው ማኅበረሰብ ለአስፍሆተ ወንጌል ሃብት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በኤውሮጳ 8 ሚሊዮን ካቶሊክ ምእመናን የሚገኙባቸው በጠቅላላ ከ 35 ሚሊዮን በላይ የሚገመተው ስደተኛ ግምት የሚሰጥ ነው። የስደተኛው እምነትና ባህል እውቅና በመስጠት የአስተናጋጁ አገር እምነትና ባህል በማስተዋወቅ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማነቃቃት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የመላ ኤውሮጳ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ህብረት የስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጃንካርሎ ፐረጎ በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር፣ ስደተኞች የሚያጋጥማቸው ዘርፈ ብዙ ችግር ለይቶ ለመቀረፍ በሚደረገው ጥረት ቤተ ክርስትያን በምትሰጠው አስተዋጽኦ አብነት መሆንዋና የስድተኛው ችግር ግምት የሰጠ የማስተናገድ ብቃት በኤውሮፓ እንዲስፋፋ ማሳሰባቸው ሮበርታ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.