2012-11-30 14:07:11

ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛና የድኾች ድምጽ፦ ድኻ የእግዚአብሔር መንግሥት ነቢይ ነው


RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ ስድስተኛ አስምቱን ክፍለ ዓለም የጎበኙ የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸው ሲገለጥ፣ ለድኾች ቅርብ መሆናቸውና በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ተልእኮ ድኾች ልዩ ስፍራ አላቸው በማለት ብቻ ሳይሆን “የእግዚአብሔር መንግሥት ነቢያቶች” በማለትም ይገልጥዋቸዋል።
ር.ሊ.ጳ. ሞንቲኒ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸው ለድኾች የሰጡት ትኩረት የላቀና ጥልቅ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ትላትና እዚህ በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው በጉሌልሞ ማርኮኒ የጉባኤ አዳራሽ የኤውሮጳ የራዲዮና የቴሌቪዥን ሥርጭት መስፋፋት ኅብረት “ድኽነት ለምን” በሚል ርእስ ሥር ባነቃቃው መርሃ ግብር መሠረት በማድረግ፣ ዓውደ ጥናት መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ድኽነት የፍቅር ሥራ-ግብረ ሠናይና ማኅበራዊ ፍትሕ የተሰኙት ቃላት ማእከል ያደረገው የር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ አስተምህሮ የዚያ የ 1970 ዓመታት የነበረው ማኅበራዊ ሰብአዊና ሊጨበጡ የማይችሉት ርእዮተ ዓለም ያስከተሉት ውጥረቶች ለማረም የሰጡት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ በተካሄደው ዓውደ ጥናት የተሰመረበት ሲሆን፣ እኚህ 261ኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እይታችን ወደ ክርስቶስና ወደ ወንጌሉ ማድረግ አንደሚያስፈልግ ካለ መታከት ያሳሰቡ ናቸው። ይኽም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 7 ቀን 1965 ዓ.ም. ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ‘ሓሴትና ተስፋ’ በተሰኘው ውሳኔው ሥር የሁሉም ደስታና ስቃይ የክርስቶስ ተከታዮች ስቃይና ደስታም ነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰብአዊ ክስተት በክርስቶስ ተከታዮች ልብ ዘንድ አለ ስፍራ አይቅርም” በማለት ከሚስጠው ጥልቅ አስተምህሮ ጋር የተቆራኘ መሆኑ የተካሄደው ዓውደ ጥናት እንዳሰመረበትም ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ አስታወቁ።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 1965 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ ስድስተኛ በተባብሩት መንግሥታት ሕንፃ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ “የድኾች የሚሰቃዩት የተናቁት የተጠሙት የዓለም ሃብት ተካፋይ የመሆን መብታቸው ለተነፈጉት ፍትሕ ሰብአዊ ክብር ነጻነት ለተነፈጋቸው ድምጽ እንሁን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስምምነት መድረክ ነው የሚለው የሕዝብ እማኔ እንዳይካድ አደራ…” እንዳሉም በተካሄደው ዓወደ ጥናት መዘከሩንም ካፐሊ ከገለጡ በኋላ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ “ማኅበራዊ ፍትህና ሰላም እንዲሁም የሁሉም አገሮች ልማት ለማነቃቃት የሚያገለግል ድርጅት እንዲቋቋም ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥሪ በማቅረብ፣ እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 1967 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የፍትና ሰላም ምክር ቤት ባላቸው ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሠረት እንዲቋቋም በማድረግ እንዲሁም ፍትህና ሰላም በሁሉም አገሮች እንዲረጋገጥ ባላቸው ጽኑ ፍላጎት መሠረት የተለያዩ ዓለም አቀፋው ሐዋርያዊ ጉብኝቶች እንዳከናወኑም በዓውደ ጥናት መዘከሩም አብራርተዋል።
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 23 ቀን 1968 ዓ.ም. በኮሎምቢያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ በቦጎታ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ፦ ድኮች “…የክርስቶስ ኅላዌ ምሥጢር ምልክት አምሳያ ናችው፣ ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምራ ድኾች የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳት ምሥጢራት ብላ እንደምትገልጣቸውና በዚህ አገላለጥ ሥር እነርሱን እንደምታገለግል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰቃየው በተጠማው በታመመው በተናቀው በሚሰደደው እንደሚገለጥ ካለ ምንም ማወላወል ተናግሮናል። ይኽ ደግሞ ወንጌላዊ ሥነ ማኅበራዊ እርሱም የጌታችን ክርስቶስ ሰብአዊነት መግለጫ ነው” በማለት የገለጡት ጥልቅ ሐሳብ በተካሄደው ዓውደ ጥናት መብራራቱና፣ ድኾች በቤተ ክርስትያን ጥሪ ማእከላዊ ሥፍራ እንዳላቸው በተለያየ ወቅት ባሰሙት አስተምህሮ ባካሄዱዋቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ወቅት ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮና ሰብከት ለየት ባለ መልኩ እንዳሰመሩበት በተካሄደው ዓወደ ጥናት በጥልቀት መታወሱ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.