2012-11-28 16:23:25

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (28.11.2012)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧
ለዛሬ የምናቀርበው ዋና ጥያቄ ይህ ነው፣ ባለነው ዘመን ስለ እግዚአብሔር እንዴት አድርገን እንናገር፧ በኅብረተሰባችን ባሉ የሚያብለጨልጩ ነገሮች እንዲዘነጉ ለተደረጉ የዘመናችን ልቦችና አእምሮዎች ውስጥ ለደኅንነቱ እውነቶች መንገድ እንዲከፍትላቸው ወንጌልን እንዴት አድርገን እናስተላልፍ፧ ወንጌላውያን እንደሚሉን ኢየሱስ ራሱ የእግዚአብሔርን መንሥት ሲሰብክ ይህንን ጥያቄ አቅርበዋል፣ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን? (ማር 4፤30) ብለዋል፣ ዛሬ ስለ እግዚአብሔር እንዴት እንናገር ለሚለው ጥያቄ የመጀመርያው መልስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ተናገረ ስለ እግዚአብሔር መናገር እንችላለን የሚል ነው፣ ስለዚህ ስለእግዚአብሔር ለመናገር የመጀመርያው ዉል ራሱ እግዚአብሔር ያለውን ማዳመጥ ነው፣ ከእኛ ጋር ተናግረዋል፣ እግዚአብሔር በሰው አሳብ ብቻ ያለ ከዓለም የራቀ መላምንት ወይንም ከሰው ልጆች እጅግ የራቀ ረቂቅ ሒሳብ አይደለም፣ እግዚብሔር ስለ እኛ ያስባል፣ ያፈቅረናልም፣ በአካል ደግሞ በታርካችን ተሳትፈዋል፣ በምሥጢረ ሥጋዌ ሰው እስከ መሆን በመድረስ ራሱን ገለጠ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር የሕይወታችን ክፍል ነው፣ እግዚብሔር ይህን ያህል ታላቅ ነው፣ ለእኛ የሚሆን ጊዜ አለው፣ ስለ እኛ ያስባል፣ በናዝሬቱ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፊትን እናገኛለን፤ ይህም እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት ወደ የሰው ልጆች ዓለምና ዓለማችን ላይ ወርዶ፤ የኑሮ ዘዴንና ጥበብን እንዲያስተምር የደስታ መንገድን እንዲያሳይ ከኃጢአት ነጻ እንዲያወጣንና የእግዚአብሔር ልጆች እንዲያደርገን ዘንድ በሰው ልጆች ዓለም ገባ (ኤፈ 1፡5 ሮሜ 8፡14 ተመልከት)፣ ኢየሱስ እንዲያድነንና የወንጌል መልካም ሕይወትን እንዲያሳየን መጣ፣
ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር መናገር ማለት ለዘመናችን ሰዎችና ሴቶች መንገር ያለብንን ነገር አጣርተን ማወቅ አለብን፣ እግዚአብሔር የማይጨበጥ ወይንም የአሳብ ውጤት ሳይሆን ተጨባጭና የሚኖር አምላክ ነው፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የገባና ገናም በዚሁ ታሪክ ሁሌ የሚኖር አምላክ ነው፣ ለምን እንኖራለ፡ እንዴትስ እንኖራለን፤ ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን እንደ መልስ ማቅረብ አለብን፣ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር መናገር፤ ከኢየሱስና ከወንጌል ጋር ዝምድና ማድረግን ይጠይቃል፤ የገዛ ራሳችን የሆነ እውነተኛ የእግዚአብሔር እውቀት እና ለድኅነት እቅዱ ብርቱ ስሜት እንዲኖረን ይጠይቃል፤ በመጨረሻም የድል መቀዳጀት ፈተና ውስጥ ሳንወድቅ ነገር ግን የእግዚአብሔር ዘዴን መከተል እንዳለብን ያሳስባል፣ የእግዚአብሔር ዘዴ የትሕትና ዘዴ ነው፣ ይህም ዘዴ እግዚአብሔር እንደ እኛ ሰው በመሆኑ ነው፣ ዘዴውም በእውነት የተከናወነው የሰናፍጭዋ ታናሽ ዘር ምሳሌ በሆነው በናዝሬቱ ትንሽ ቤትና በቤተልሔሙ ግርግም በምሥጢረ ሥጋዌ ነው፣ የትናንሽ እርምጃዎች ትሕትናን አለመፍራትና በሊጥ ውስጥ በመግባት ቀስ ቀስ የሚያቦካው እርሾ መተማመን ያስፈልጋል፣ (ማቴ 13፡33 ተመልከት) በስብከተ ወንጌል ተግባር በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሥር ሆኖ ስለ እግዚአብሔር ለመናገር ገር መሆን ያስፈልጋ፣ ወደ መሠረታዊዉ የምሥራች ዜና መመለስ ያስፈልጋል፣ ይህ የምሥራች ዜና ስለ እውንና ተጨባጭ የሆነ እግዚአብሔር፤ ስለ እኛ የሚያስብ ፍቅር የሆነ እግዚአብሔር ያበሥራል፣ ቅርባችን በመሆን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና ትንሣኤ ተስፋ ይሰጠናል፤ መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማ ሕይወት ይከፍትልናል፣ ይህም እውነተኛ ሕይወት ነው፣ ልዩ የመልእክት አስተላላፊ የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ መናገር ይቻላል ለሚለው ጥያቄ በታላቅ ገርነት የእምነት አንኳር የሆነ ትምህርት ያቀርብልናል፣ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው አንደኛ መልእክቱ “ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።” (2፡1-2) የሚሉ ቃላትን ጽፈዋል፣ ስለዚህ የመጀመርያው እውነት እርሱ ራሱ በፈጠረው ፍልስፍና ወይንም ከሌሎች ባገኛቸው ሓሳቦች ወይም ፈጥሮ ባቀረባቸው ነገሮች አይናገረም፤ በሕይወቱ ስላጋጠመው ነገር ይናገራል፣ በሕይወቱ ስለገባው ስለእግዚአብሔር ይናገራል፤ ይህም እግዚአብሔር እውንና ሕያው ሆኖ ከእርሱ ጋር ተናግረዋል፣ ስለ ከሙታን ተለይቶ የተንሣው ክርስቶስ ስለ ተሰቀለውና ስለተነሣው ይናገረዋል፣ ሁለተኛው እውነት እንደሚናገር መግለጡ ነው፣ ራሱን አይፈልግም የሚያደንቁት ቡድን ለማቆምም አይጥርም በታሪክ ውስጥ እንደ የታላቅ እውቀት ትምህርት መግባት አይፈልግም፣ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስን ይሰብካል ሰዎችን ለእውነተኛና ለሚኖረው እግዚአብሔር እንዲያስረክብ ይጥራል፣ ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆስ መንገድ በሕይወቱ ውስጥ ገብቶ ስላሸነፈውና እውነተኛ ሕይወት ስለሰጠው ስለ ክርስቶስ ለመስበክ ስላለው ፍላጎት ብቻ ይናገራል፣ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር መናገር ማለት የፍቅር ገጽታውን ለገለጠልን እንድናዉቀው ላደረገን እግዚአብሔር ቦታ መስጠት ማለት ነው፣ ገዛ ራስን ትቶ ራስን ለክርስቶስ ማስረከብ ነው፣ እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ጉዳይ ደግሞ ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር የምናደርስ እኛ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ወደ እርሱ እንዲስባቸው መጠባበቅና እርሱን መለመን እንዳለብን ነው፣ ስለዚህ ስለእግዚአብሔር መናገር እግዚአብሔርን ከማዳመጥ ማለትም ጸሎት በማዘውተርና ትእዛዞቹን በመጠበቅ ከእርሱ ጋር ባለን ዝምድና እውን በሚሆነው የእግዚአብሔር እውቀት ይወለዳል፣
ለቅዱስ ጳውሎስ እምነትን ማስተላለፍ ማለት ገዛ ራስን ማስተዋወቅ ሳይሆን ግልጥና ይፋዊ በሆነ መንገድ ከክርስቶስ ጋር በተገናኘበት ወቅት ያየውንና የሰማውን መናገር ነው፣ በዚሁ ግኑኘት የተለወጠውን የሕይወቱ ተመኵሮን ያካፍላል፣ ሁሌ ሸኝቶት ከእርሱ ጋር የሚኖረውንና የሕይወቱ እውነተኛ መሪ የሆነውን ኢየሱስን ለሌሎች ለማዳረስ ሁላቸውም ኢየሱስ ለመላው ዓለም አስፈላጊና ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ነጻነት ወሳኝ መሆኑን መግለጥ ነው፣ ሐዋርያው በቃላት ብቻ በመስበክ አይረካም ነገር ግን በዛኛው ታላቅ የእምነት ሥራ መላው ሕይወቱን ይከታል፣ ስለ እግዚአብሔር ለመናገር በድካማችን የሚሰራ እርሱ መሆኑን በማወቅ ለእርሱ ቅድሚያ መስጠት ያስፈልጋል፣ ይህንንም ሲያደርጉ ገዛ ራሳችን ሳይሆን እርሱን የኑሮአችን አንኳር ባደረገነው ቁጥር ስለ እርሱ የምናስተላልፈው መል እክት ውጤታማ እንደሚሆን በመትማመን አለ ምንም ፍርሓት ገር በሆነ ልብና ደስታ በተሞላበት አኳሃን መሆን አለበት፣ ይህ ለሁሉም ማኅበረ ክርስትያን ይጠቅማል፣ ማኅበረ ክርስትያኖቹ በየግል ጉዳዮቻቸው መዘጋትንና እኔነት እንዲሁም ግድየለሽነትም በማሸነፍ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ፍቅር ያላቸውን ግኑኝነት በተግባር በመኖር የእግዚአብሔር ለዋጭ ጸጋ ሥራን ለመመስከር የተጠሩ ናቸው፣ ወደ ገዛ ራሳችን መለስ ብለን የእኛ ማኅበረ ክርስትያኖች እንደዛ ናቸውን፧ ብለን የጠየቅን እንደሆነ፤ ካሁኑ ጀምረን የክርስቶስ ሰባኪዎች እንጂ የገዛ ራሳችን ሰባኪዎች እንዳንሆን እንንቀሳቀስ፣
በዚሁ ነጥብ ላይ ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ራሱን ለሌሎች ያስተዋውቅ ነበር ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል፣ ኢየሱስ ወልድ ዋህድ በመሆኑ ስለ አባቱ አባ እያለ ስለ እግዚአዚብሔር መንግሥት ሲናገር በሰው ልጅ ኑሮ ያለውን አለመጣጣምና ችግር በሙሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ነው፣ እጅጉ እውን በሆነ መንገድ ይናገራል፣ ይህም ዓለማችንና ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር ግልጥ ያደርገዋል፣ በዚሁ ዓለም በፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔር ገጽታ እንደሚያንጸባርቅ ያሳየናል፣ እንዲሁም በዕለታዊ ሕይወት ታሪኮቻችን በተፈጥረአዊ ምሳሌዎችም ይሁን በሌሎች አነጋገሮች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለ ያሳየናል፣ ከሚያቀርባቸው ምሳሌዎች የታንሽዋ የሰናፍጭ ዘርና ሌሎች ምሳሌዎች ሕይወታችን የሚመለከቱ እንደ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ እና የአል አዛር ምሳሌዎችን መመልከት እንችላለን፣ ከወንጌሎች የምንረዳው ነገር ካለ ኢየሱስ ባጋጠመው እያንዳንዱ የሰው ልጅ ሁኔታ እንዴት እንደሚቆርቆር እና በጊዜው በነበሩ ሰዎችና ሴቶች ሁኔታ ውስጥ በመግባት አባቱ እንደሚረዳው በሙሉ ልቡ በመተማመን ይረዳ እንደበር እንመለከታለን፣ እነኚህን ታርኮች በጥንቃቄ የተመለከትን እንደሆነ እግዚአብሔር አብ ከእርሱ እንደነበርና በስውር ይሰራ እንደነበር እንረዳለን አሁንም እንደዛ ስለሆነ ልናገኘው እንችላለን፣ ከኢየሱስ ጋር ይኖሩ የነበሩ ሐዋርያት እና ይከተሉት የነበሩት ሰዎች አስጨናቂ በሆኑ ችግሮች እንዴት ይሰራ እንደነበረ ያዩታል፤ እንዴት እንደሚናገርና ሥራውን እንደሚጽምም ይታዘባሉ፤ በእርሱ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ሥራን እና የእግዚአብሔር አብ ሥራን ያያሉ፣ በኢየሱስ ላይ ስብከተ ወንጌልና ሕይወት ይተሳሰራሉ፣ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ካለው ጥልቅ ግኑኝነት በመነሣት ይሰራል ያስተምራልም፣ ለእኛ ክርስትያኖችም ዛሬ ይህ ዘዴ መምርያ ይሰጠናል፣ በዛሬው ዘመናችን በእምነት መኖርና ምግባረ ሠናይን ማዘውተር ስለ እግዚአብሔር መናገር ይሆናል፣ ምክንያቱም ከክርስቶስ ጋር በእምነት መኖርን ያመለክታልና፣ እንዲሁም በቃላት የምንናገረውን የቃል ነገር ብቻ ሆኖ ሳይቀር በተግባር እውነቱን ያሳያል፣ ስለዚህ በዘመናችን ለሚታዩ የግዝያት ምልክቶችን ጠንቅቀን መመልከት አለብን፣ በዚህም ማድረግ የምንችለውን እተግባር ላይ ለመዋል አስፈላጊነት ያላቸውን ነገሮች ለማወቅና ባለው ባህል ያሉትን እንቅፋቶች ለይተን ማወቅ ያስፈልጋል፣ ስለወዲያኛው ዓለም መኖር መጠራጠር ያለነውን ተፈጥሮ መጠበቅ እና በእግዚአብሔር ማመን የሚሰጠንን ግብረ መልስ አለፍርሃት መግለጥ ያስፈልጋል፣ የጀመርነው የእምነት ዓመት የሚለግስልን አጋጣሚ በእያንዳንዲ ቦታ የወንጌል ኃይል የሕይወት ዕውቀትና የኑሮ አችን መመሪያ እንዲሆን ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ተመርተን በግልና በማኅበር ደረጃ አዳዲስ መነሻዎች እንሻ፣
ቤተ ሰብ አሁን ባለንበት ጊዜም ስለ እግዚአብሔር የምንናገርበት ክቡር ቦታ ነው፣ ቤተ ሰብ እምነትን ወደ አዲስ ትውልድ ለማስተላለፍ የምንጠቀምበት አንደኛ ትምህርት ቤት ነው፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወላጆች የመጀመርያ የእግዚአብሔር መልእክቶኞች መሆናቸውን ይገልጣል (በብርሃነ አሕዛብ ቍ 11 እንዲሁም የም እመናን ግብረ ተል እኮ ቍ 11 ተመልከት)፣ የትናንሽ ኅልናዎች ለእግዚአብሔር ፍቅር ክፍት እንዲሆኑ ለማስተማር በኅላፊነት መንቀሳቀስ ያለባቸው ወላጆች ይህንን ተልእኮአቸው እንደ ሕይወታቸው መሠረታዊ አገልግሎት አድርገው በመውሰድ ለልጆቻቸው የመጀመርያ የትምህርተ ክርስቶስ መማህራንና የእምነት አስተማሪዎች መሆናቸውን ማወቅ አለባቸው፣ በዚህ ሥራ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ ይህም ማለት በቤተ ሰብ ውስጥ ስለ እምነት ለመናገርና ልጆቻቸውን የሚያስቸግሩ የተለያዩ ችግሮችን ለመቅረፍ አመቺ ግዜን ማየትና መጠቀም ያስፈልጋል፣ ይህ ዓይነት የወላጆች ጥንቃቄ በልጆቻቸው አእምሮ እየተመላለሱ የሚያስቸግሩት አንዳንዴ ግልጥ የሆኑ አንዳንዴ ደግሞ የተደበቁ እምነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ገልጦ ለመጠየቅ እና ለመወያየት ዕድል ይፈጥራል፣ የእምነት ማስተላለፍ ሁሌ የደስታ ቃና ሊኖረው ያስፈልጋል፣ ይህ ደስት የፋሲካ ደስታ ሆኖ በስቃይ በጭንቀት በድካምና ችግር እንዲሁም ባለመረዳትንና በሞትም ፊት ሳይቀር ማዳሰስ ዝም የማይል ነው፤ ነገር ግን ሁሉንም በክርስትያናዊ ተስፋ አመለካከት መፍትሔ ለመስጠት የሚችል ነው፣ የወንጌል መልካም ሕይወት ይህ አዲስ አመለካከት ነው፣ ማለትም ሁሉንም ሁኔታ በእግዚአብሔር ዓይን ለማየት መቻል ነው፣ ለሁሉም የቤተ ሰብ አባላት እምነት ሸክም አለመሆኑን እንዲረዱ መርዳት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን የጥልቅ ደስታ ምንጭ ሆኖ የእግዚአብሔር ሥራን ለመረዳትና ድምጽ አልባ የመልካም ነገር መኖርን ለማወቅ የሚረዳ ሆኖ ሕይወታችን በጥሩ ሁኔታ ለመኖር ክቡር የሆነ መምርያ ይሰጣል፣ በመጨረሻም ሰምቶ መቻልና ለውይይት ክፍት መሆን በቤተሰብ አስፈላጊ ነው፣ ቤተ ሰብ ሁሉም አብሮ የመኖር ሁኔት የሚማርበት መሆን አለበት፣ በዚህም በመካከላቸው ላለው አለመግባባት በውይይት ለመፍታት፤ ይህንን ለማዳረግ ደግሞ አንዱ ለሌላው የእግዚአብሔር መሐሪ ፍቅር ወካይ በመሆን በቃልና በመዳመጥ በመረዳዳት ይሆናል፣
ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር መናግር ማለት በቃልና በሕይወት እግዚአብሔር የህልውናችን ተወዳዳሪ አለመሆኑን መረዳት ነው፣ ነገር ግን የሕይወታችን እውነተኛ ዋስትና ነው፤ የሰው ልጅ ታላቅነት ዋስትና፣ በዚህም ወደ መጀመርያው ስለ እግዚአብሔር መናገር በገርነት በቃልና በአኗኗርህ እግዚአብሔር ለሌሎች ማሳወቅ ወዳልነው እንመለሳለን፣ ማለትም የኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር በምሥጢረ ሥጋዌ በሞቱና በትንሣኤው ያንን ያህል ታላቅ ፍቅር ያሳየን እግዚአብሔር ሕይወታችንና ከእርሱ ያለንን ግኑኝነት እንድናሳድስ ወደር በሌለው ፍቅር እንድንከተለው የሚጠራን እርሱ ነው፣ እግዚአብሔር አብረን እንድንጓዝና በቃሉና በምሥጢራቱ አማካኝነት መላው የሰው ልጆች ከተማችንን የእግዚአብሔር ከተማ እስክትሆን ድረስ አብረን እንድንሰራ ቤተ ክርስትያንን ሰጠን፣ እግዚአብሔር ይስጥልን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.