2012-11-28 13:37:31

ዓለም አቀፍ የተለያዩ ሃይማኖቶችና ባህሎች የውይይትና የግኑኝነት ማእከል


የሰውን ልጅ ተስፋው የሚያኖርበት ግኡዛዊ ግብረ ገባዊና ሃይማኖታዊ ምኞት-ዝምባሌ በተለያዩ መልኩ ለመደገፍና ይኽንን ሰብአዊ ፍላጎት በተገባና በትክክለኛው መንገድ የተመራ ለማድረግ በሚል አላማ በዚህ እቅድ መሠረት የተለያዩ ሃይማኖትና ባህሎች የውስጠ ግኑኝነት (ኅብረ- ሃይማኖቶችና ኅብረ-ባህሎች ግኑኝነት) RealAudioMP3 ማእከል በንጉሥ አብዱላህ በን አብዱላዚዝ ስም የሚጠራው በሳውዲ አረቢያ በስፐይንና በኦስትሪያ እንዲሁም በቅድስት መንበር የታዛቢ መሥራችነት የተቋቋመው ማኅበር መሠረት በቪየና ከትላትና በስትያ ተመርቆ መከፈቱ ሲገለጥ፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያንን ወክለው በምረቃው በዓል የተሳተፉት የተለያዩ ሃይማኖቶ የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን የሰው ልጅ የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ የሰው ልጅ ካለው ሃይማኖታዊ ዝምባሌ ወይንም በኑባሬ በሰው ዘንድ ካለው መንፈሳዊነት አቢይ ግምት መስጠት ከሚለው አመለካከት መጀመር እንዳለበት በተካሄው ግኑኝነት ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በተካሄደው ግኑኝነትም የተገኙት የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ባሰሙት ንግግርም፦ “የተለያዩ የአንዳንድ ሃይማኖቶች መሪዎች አለ መከባበርን አለ መቀባበልን አክራሪነትን ካንተ ለተለየው ጥላቻን የሰበኩ ያሉ ቢሆንም ቅሉ፣ ሌሎች በጣም ብዙ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች መቀራረብን መከባበርን ሰላማዊ የጋራ ኑሮ በማነቃቃት ሰላም የሰበኩ አሉ። የሃይማኖት መሪዎች በአንድ ኅብረተሰብ ዘንድ የሚኖራቸው ተጽዕኖ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ሃይማኖቶች የሰላም መሣሪያ መሆን ባህርያዊ መለያቸው ነው” እንዳሉ ተገልጠዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ታውራን በበኩላቸውም” “ቅድስት መንበር የሃይማኖት ነጻነት የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት መሆኑ በማስተጋባት በሁሉም አገሮች የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር ጥሪ ከማቅረብ ወደ ኋላ እንደማትል ነው። ስለዚህ ይህ የካኢቺድ ማእከል የኅብረ-ሃይማኖቶችና ኅብረ-ባህሎች ውስጠ ግኑኝነት ቅንነት ግልጽነትና ታማኝነት ላይ ያተኮረ ሊሆን ይግበዋል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.